cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TIKVAH-MAGAZINE

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Show more
Advertising posts
198 197
Subscribers
-3124 hours
+1647 days
+9030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮ ቴሌኮም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ በዋናነት፦ - ገቢውን በ74.7 በመቶ ለማሳደግ፤ - 4.7 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞች ለመሳብ፤ - የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ቁጥር በ19.1 በመቶ ለማሳደግ፤ - 7.45 ሚሊዮን አዳዲስ የቴሌብር ደንበኞች ለማፍራት፤ - ተጨማሪ በ15 ከተሞች የ5G አገልግሎት ለመጀመር አቅዷል። #መነሻ: ኢትዮ ቴሌኮም “ሊድ” የተሰኘ የሦስት ዓመት ስትራቴጂውን በ2015 በጀት ዓመት ማስተዋወቁ ይታወሳል። አዲሱ የ2017 በጀት ዓመት የስትራቴጂ ዘመኑ 3ኛውና የመጨረሻው ይሆናል። 🔗 የኢትዮ ቴሌኮም የ3 በጀት ዓመታት ንጽጽርን ከላይ ባለው ምስል ተመልክተው ኃሳቦትን ያካፍሉን።
Show all...
26😡 11👏 4🕊 4🤔 2😢 1
#እንድታውቁት ከጋንቤላ አዲስ አበባ የሚወስደው የአስፋልት መንገድ በቡኖ ቡኖ በደሌ ዞን ደዴሳ ወረዳ፣ ማሳራ ቀበሌ የመሬት መንሸራረት በማጋጠሙ አስፓልቱ ተቆርጧል። በዚህም ምክንያት የትራፊክ እንቅስቃሴ መቋረጡን ኦቢኤን ዘግቧል።
Show all...
🤔 17 6😢 4🕊 4
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ እናት በ42 ዓመት ዕድሜያቸው አራት ህፃናትን በሰላም ተገላገሉ። ወይዘሮ አደባባይ የሺነህ 42 ዓመት ዕድሜያቸው በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል አራት ህፃናትን በሠላም ተገላግለዋል። ሶስት ወንድና አንድ ሴት በድምሩ አራት ህፃናትን በሰላም የተገላገሉት እናት የአሁኑን ጨምሮ ለስድስተኛ ጊዜ ነው የወለዱት። የተወለዱት አራት ህፃናትም በአሁኑ ሰዓት ሰባት ወራት ጊዜያቸው ሳይደርስ የተወለዱ ስለሆነ በህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ ተበልሏል። በአሁኑ ስዓት በሙሉ ጤንነት እንደሚገኙ የገለጹት ወላጅ እናት በሰላም እንድትገላገል ለረዷት ለሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎችና የፓዊ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ላደረጉላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ዘገባው የፓዊ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።
Show all...
83🤔 14👏 7😢 5😡 3
#CRRSA የመታወቂያ ህትመት ለደረሰላቸው ተገልጋዮችን ለማሳወቅ የአጭር መልዕክት አገልግሎት በሙከራ ላይ ነው ተባለ። የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የመታወቂያ ስርጭት ክፍተቶችን ማረም የሚያስችል የአጭር መልዕክት አሰራር በይፋ ወደ ሙከራ አስገብቷል። ነዋሪዎች የነዋሪነት መታወቂያዎን ይውሰዱ መልዕክት ሲደርሳቸው የነዋሪነት መታወቂያ ታትሞ ዝግጁ የሚሆን በመሆኑ ወደ ተመዘገቡበት ጽ/ቤት ሄደው መረከብ የሚችሉበት አሰራር እንደሆነም ነው የተገለፀው።
Show all...
👏 35 10🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቴሌብር ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት የቴሌብር ደንበኞችን ቁጥር በ15.7% በመጨመር 55 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ እና የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የቢዝነስ ዕቅድ መግለጫ ላይ ጠቅሷል። ኩባንያው፥ የቴሌብር ወኪሎችን ቁጥር በ28% በማሳደግም 275 ሺህ ለማድረስ እንዲሁም በቴሌብር ግብይት የሚፈጽሙ ነጋዴዎችን (Merchant) ቁጥር በ102% በማሳደግ 367 ሺህ ለማድረስ በእቅዱ እንደተቀመጠም ጠቅሷል። በተጨማሪም፥ የኤሌክትሮኒክ ንግድ ክፍያዎችን፣ አለም አቀፍ የኦንላይን ክፍያዎችን፣ ተጨማሪ አጋሮችን በማሳተፍ የሃዋላ አገልግሎቶችን ለማሳደግ እንደሚሰራም ነው የገለጸው። ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል።
Show all...
20🤔 7
Photo unavailableShow in Telegram
አርብቶ አደሩ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የእንስሳት ኢንሹራንስ ግዢ እንዲያከናውን ጥሪ ቀረበ የእንስሳት ኢንሹራንሱ ሽያጭ በአርብቶ አደር አካባቢዎች ነሀሴ 26 ቀን 2016 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ በሚከናወነው የኢንሹራንስ ሽያጭ በዚህ ዓመት ለ80 ሺህ አርብቶ አደሮች ኢንሹራንስን ለመሸጥ አቅድ መያዙ ተገልጿል። በመሆኑም በመጀመሪያው ዙር ለ35 ሺህ አርብቶ አደሮች ኢንሹራንስ ለመሸጥ መታቀዱ ተጠቁሟል፡፡ አርብቶ አደሩ በድርቅ ምክንያት እንስሳቱን እንዳያጣ አስቀድሞ አካባቢዎቹ በሳተላይት ከተለዩ በኋላ በአንድ ወር ውስጥ ውሀ፣ ሳር እና መድኃኒትን ለእንስሳት ለመግዛት እንዲቻል ኢንሹራንሱ ይከፈላል ተብሏል። ኢንሹራንሱ ተግባራዊ የሚደረገው ዝናብ ሲመጣ አረንጓዴ ሆነው በተቃራኒው ደግሞ ዝናብ ሲጠፋ ደረቅ የሚሆኑት አካባቢዎች ላይ መሆኑ ተገልጿል። ኢንሹራንሱ የሚተገበረው በዓለም ባንክ ድጋፍ እና በግብርና ሚኒስቴር አማካኝነት በተቋቋመው የአርብቶ አደሮች የአደጋ ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት አማካኝነትና በአጋር ድርጅቶች እገዛ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ በዚህ አመት በሚሸጠው ኢንሹራንስ 30 በመቶውን አርብቶ አደሩ ሲከፍል 70 በመቶው ደግሞ በፕሮጀክቱ ይሸፍናል ተብሏል። Credit : FBC
Show all...
🤔 9 4🕊 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለቢዝነሶ ወይም ለግሎ ዌብሳይት ይፈልጋሉ? እኛ ዛየን ዌብ (Zion Web) እንሰኛለን። ደረጃውን የጠበቀ ዌብሳይት ዲዛይን አድርገን በአጭር ጊዜ ውስጥ በተመጣጣኝ ዋጋ እናስረክባለን። አሁኑኑ ደዉለዉ 📞0922501644 or @muzika23 1. ከአንድ አመት ዌብ ሆስቲንግ 2. እስከፈለጉት ድረስ የድርጅቶ ኢሜል አድሬስ ለእርሶ እና ለሰራተኞቾች አሁኑኑ ደዉለዉ የድርጅቶን ዌብሳይት ያስጀምሩ 📞 0922501644 or @muzika23 🏢 SarBet Beside Effoi Pizza 📥 https://t.me/zionwebs
Show all...
1
Photo unavailableShow in Telegram
° " የኮሌራ ወረርሽኝ በአጭር ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ በመሠራጨት ላይ ነው " - የወልዲያ ከተማ  ጤና መምርያ ° በወረርሽኙ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 85 ሰዎች ታመዋል፡፡ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ፣ እስከ ማክሰኞ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ በወረርሽኙ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 85 መድረሱ ተገለጸ፡፡ ወረርሽኙ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም. በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ክፍለ ከተማ አድማስ ባሻገር ተክለ ሃይማኖት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መከሰቱን፣ የወልዲያ ከተማ ጤና መምርያ ሜዲካል ኦፊሰር ሲስተር ዘሬ በቀለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ የሁለት ሰዎችን ናሙና ወደ ደሴ ሆስፒታል ላቦራቶሪ በመላክ ወረርሽኙ መከሰቱ ተረጋግጧል ያሉት ሲስተር ዘሬ፣ ሁለቱ ሰዎች በበሽታው ተጠቅተው እንደነበር አክለዋል፡፡ ወረርሽኙ በፍጥነት በመዛመቱ 85 ሰዎች ታመው በሦስት ጤና ተቋማት ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ከታማሚዎቹ መካከል 11 ያህሉ በፅኑ መታከሚያ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ሲስተር ዘሬ አክለዋል፡፡ በሕክምና መስጫዎች የመድኃኒት፣ የአልጋና የብርድ ልብስ እጥረት እንዳለ የተናገሩት ሲስተር ዘሬ፣ በሚመለከተው አካል ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Show all...
😢 20 8😡 3😨 2🤔 1
ፔጀርስ የተሰኘው የመገናኛ መሳሪያ እና ዛሬ የተከሰተው ፍንዳታ አንድ አመት ሊደፍን ቀናት በቀሩት እንደ አዲስ የተቀሰቀሰው የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነት እንደ ሂዝቦላ ያሉ ኃይሎችን ጭምር ወደ ጦርነቱ በመሳቡ ምክንያት በቀጠናው ያለውን ውጥረት እየተባባሰ መጥቷል። ዛሬ ከወደ ሊባኖስ የተሰማው ዜና ግን ምን ያህል የጦርነት አድማሱ መስፋቱን የሚያመለክት ነው። ይህም በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰው የሂዝቦላ ጦር አመራሮች እና አባላት የሚጠቀሙበት የግንኙት መስመር በድንገት ፈንድቶ በርካቶችን በጽኑ አቁስሏል ተብሏል። የሂዝቦላ ኃይሎች ለመገናኘትና መረጃ ለመለዋወጥ ይጠቀሙታል የተባለው ይኸው ፔጀርስ (Pagers) የተሰኘው ቁስ ባልተጠበቀ ሁኔታ በተከታታይ ወቅት በሊባኖስና በሶርያ በከፊል በመፈንዳት ከ2,800 በላይ ይህንን ይዘው የነበሩ ሰዎችን አቁስሏል ነው የተባለው። ይህ የርቀት ጥቃት (Remote Attack) የሂዝቦላ አባላትን እንዲሁም በኢራን ይደገፋሉ የተባሉ ታጣቂ ቡድኖች ላይ ያነጣጠረ ነው የተባለ ሲሆን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር በሰዎች ላይ የደረሰው ጥቃት ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል። የሂዝቦላ ኃይሎች ለዚህ ውስብስብ ለሆነ ጥቃት እስራኤል ተጠያቂ ቢያደርጉም በእስራኤል በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ለመሆኑ ፔጀር ምንድን ነው? ፔጀር የሬዲዮ ዌቭ የሚጠቀም የመገናኛ ዘዴ ነው። ሰዎች መረጃ ሲልኩ የሚተላለፈውም የሬዲዮ ፍሪክዌንሲ በመጠቀም ነው። መልዕክት የተላከለት ሰው መልዕክቱ እንደደረሰው በንዝረት መልዕክት መስጠት የሚችል ሲሆን አጭር የጽሑፍ ወይም የድምፅ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ይችላል። እ.አ.አ 1980ዎቹ እንዲሁም 90ዎቹ በስፋት ጥቅም ላይ ይውል የነበረ የግንኙነት መሳሪያ ነው። ይህ መሳሪያ በሞባይል ስልክ ቢተካም አሁንም ድረስ በተለያዩ ቦታዎች ጥቅም ላይ ይውላል። አሁን ፍንዳታው ያጋጠማቸው ፔጀሮች በቅርቡ በሂዝቦላ ግዢ የተፈጸመባቸው እንደሆነ የሊባኖስ የደኅንነት አባል ለCNN የገለጹ ሲሆን ዝርዝር ነገር ከመናገር ተቆጥበዋል። ይህ ፍንዳታ እንዴት እንደተከሰተ የሚያስረዱ መላምልቶች እየተነገሩ ሲሆን ለአብነትም የተገዙት ፔጀሮች ለዚሁ የተሰሩ ናቸው የሚሉና በባትሪያቸው ከፍተኛ ሙቀት በመፍጠር ፍንፈንዳታው እንዲደርስ ተደርጓል የሚሉ መላምልቶች ይጠቀሳሉ። ሁሉም የሚስማማበት ነገር ግን ምንም እንኳን እስራኤል ለዚህ ጥቃት ምላሽ ባትሰጥም ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥቃቶችን መፈጸሟን የሚያሳዩ በርካታ ማስረጃዎች አሉ። #ማሳሰቢያ: ከላይ የተያያዙት ቪዲዮዎች በCCTV ካሜራ የተቀረጹ እና ይህንን የመገናኛ ዘዴ የያዙ ሰዎች የደረሰባቸውን አደጋ የሚያሳይ ነው።
Show all...
4.11 KB
1.21 MB
🤔 44 19👏 16😢 8😡 8😨 7🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ማብራሪያ አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ፈረንሳይኛ ቋንቋን ለማስተማር የኦንላይን ምዝገባ መጀመሩን ጥቆማ መስጠታችን ይታወሳል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀዋል። የኮርሱ አስተባባሪ ሜሌና ሳሙኤል ተጨማሪውን ማብራሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል። ምን አሉ ? - ትምህርቱ በተለያየ የፈረቃ አማራጭ  በሳምንት ለ 6 ሰዓት የሚሰጥ ነው። የአንድ ተርም ኮርሶችን ለመጨረስ 2 ወር ተኩል ይፈጃል። አጠቃላይ ትምህርቱን ለመጨረስም 3 አመት እንደሚፈጅና በ4 ደረጃዎች (level) መከፈሉንም አስተባባሪዋ ገልፀዋል። - ትምህርቱ ጧት፣ ከሰዓት፣ ማታ እንዲሁም በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት #ማንኛውም ቋንቋውን መማር ለሚፈልግ ሰው የሚሰጥ ነው ተብሏል። - ትምህርቱ በፒያሳ እና ቦሌ ኦሎምፒያ የሚሰጥ ሲሆን በኦንላይን የሚሰጥበት አማራጭም መኖሩ ተጠቁሟል። - ተማሪዎች ከአንድ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ለመሻገር ከፈረንሳይ ሀገር የሚመጣ አለማቀፍ ፈተና በፒያሳ እንደሚፈተኑ ተገልጿል። ቋንቋውን ለመቻልም የተማሪ ጥረት ወሳኝ መሆኑና እንደተማሪው አቅም የሚወሰን መሆኑ ተገልጿል። ክፍያው ምን ይመስላል? - በመደበኛ ቀናት ለመማር የአንድ ተርም ክፍያ 4ሺ ብር ሲሆን መመዝገቢያው 500 ብር ነው። - በእረፍት ቀናት ለአንድ ተርም 4ሺ 500 ብር ነው ተብሏል። በቦሌ ኦሎምፒያ ለመማር ክፍያው 5ሺ ብር መሆኑም ተነግሯል። - ተማሪዎች ለ1 ደረጃ  (level) ለሚገለገሉበት መማሪያ መጻሕፍት 1800 ብር ክፍያ እንደሚከፍሉም ተገልጿል።
Show all...
47👏 11😡 10🤔 6😨 3
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.