cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ministry of innovation and technology (MinT)

Ministry of innovation and Technology (MinT) is a governmental institution ...

Show more
Advertising posts
7 802
Subscribers
+1524 hours
+1077 days
+92730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደር ኢኒሼቲቭ ኦንላይን የኮዲንግ ስልጠናዎች በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች በመሰጠት ላይ ናቸው።በዚህ ሊንክ https://www.ethiocoders.et/ በመመዝገብ የእድሉ ተካፋይ ይሁኑ!
Show all...
👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግስት መለኪያ መሰረት ደረጃዋን አሻሻለች፡፡ በየሁለት አመቱ የሚወጣው የተባበሩት መንግስታት አለማቀፋዊ የኢ-መንግስት መለኪያ ትናንት በኒዮርክ ከመንግስታቱ ስብሰባ ጎን ለጎን ይፋ ሆኗል።ይህ አለማቀፋዊ የኤሌክትሮኒክ መንግስት መለኪያ የአለም ሀገራት በየ ሁለት አመቱ ከሌሎች ሀገራት አንጻር እና በራሳቸው ካሳዩት እድገት ጋር በማነጻጸር ሀገራቱ በዘርፉ ያደረጉትን መሻሻሎች ያስመዘገቧቸውን ለውጦች የሚያሳይ ነው። በአለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ መንግስት ሪፖርት መሰርት ኢትዮጵያ ከነበረችበት ደረጃ በ2024 አስር ደረጃዎችን አሻሽላለች፡፡ የተባበሩት መንግስታት የኤሌክትሮኒክ መንግስት መለኪያ በሀገራቱ ያለውን ለዜጎች የሚሰጡ የኦንላይን አገልግሎቶች፣ የቴሌኮሚኒኪሽን መሰረተ ልማት እድገቶች እና የሰው ሃይል ልማት እድገቶችን በአንድ ላይ አጣምሮ የሚለካ ነው። https://publicadministration.un.org/egovkb/en-us/Reports/UN-E-Government-Survey-2024
Show all...
👍 11👎 3
Photo unavailableShow in Telegram
በአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች መርሀግብር እየተሰጡ የሚገኙ የኦንላይን ኮዲንግ ስልጠናዎችን በመውሰድ የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ። የመመዝገቢያ ሊንክ https://www.ethiocoders.et/
Show all...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው የእስምና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለነቢዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) 1499ኛው የልደት በዓል/መውሊድ/ በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ። መልካም በዓል።                                                                               በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር
Show all...
👍 8 2
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) ልደት የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
Show all...
5
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ 2017 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ።አዲሱ አመት የሰላም፣የጤና እና የእድገት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር
Show all...
👍 6🍾 5😁 1
የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ መቄዶንያን በመጎብኘት ድጋፍም አበረከቱ።  ============ የዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት የመቄዶንያ የሀረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማንን ማዕከል በመጎብኘት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አካሂዷል። የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በውጪ ሆነን ስንሰማ በልባችን ሁሌም ብናደንቅም በአካል ተገኝተን ስናይ ግን ሁላችንም እራሳችንን እንድናይና ከተቋሙ ጎን ሆነን እንድንደግፍ ሁኔታዎች ያስገድዱናል ብለዋል፡፡ የሰው ልጅ በጉብዝና ህይወቱ አቅመ ደካማዎችን ሊደግፍ ይገባል ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ እንደ ቢኒያም በለጠ ያሉ እድለኛ የሆኑ ወጣቶች መብዛት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ትላንት በብዙ ችግር ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ከጎዳና ላይ በማንሳት ዛሬ በመልካም ህይወት እንዲኖሩ ማስቻልና መደገፍ መታደል ስለሆነ ሁሉም መቄዶንያ እንዲደግፍ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል። የክብር ዶ/ር ቢኒያም በለጠ ሰለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ድርጅቱ በ33 ቅርንጫፍ ውስጥ ከ7500 በላይ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማንን በመንከባከብ ላይ መሆኑንና እስከ 20,000 ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ 2017 ዓ.ም ወደ 60 ቅርንጫፍ እንደሚያሳድጉም ገልፀዋል። እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ለማሳካት ይረዳን ዘንድ ሁሉም በቻለው አቅም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል፡፡
Show all...
4👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጳጉሜን 5፤ 2016 - የነገ ቀን “የዛሬ ትጋት፤ ለነገ ትሩፋት”
Show all...
👍 1
በአዲሱ አመት ኢኖቬሽን እና ዲጂታላይዜሽን ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ተናገሩ፡፡ =========================== የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የማዓድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡ በማዓድ ማጋራት ፕሮግራሙ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ 2016 በጀት አመት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ አሻራ እንደነበራቸው ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ለተመዘገቡ ሀገራዊ ውጤቶች ሰራተኞች ለነበራቸው ሚና እና የላቀ አፈፃፀም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በአዲሱ አመትም ኢኖቬሽን እና ዲጂታላይዜሽን ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የተናገሩት ሚኒስትሩ ሀገራችንን በተሰማራንበት ዘርፍ ፣በሰላም እና በልማትም ጭምር ለመለወጥ ልንረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡ ሀገራችንን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ብዙ ስራ ይጠበቅብናል ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ በመተሳሰብ፣ በፍቅርና በአንድነት በ2017 በጀት አመት ያቀድናቸውን እቅዶቻችን ለማሳካት ሁሉም ዝግጁ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዘመን መለወጫ ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ላይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰራተኞች የበዓል መዋያ ስጦታም ተበርክቶላቸዋል፡፡ ማዕድ ማጋራቱ በተቋሙ ያሉ ሰራተኞች የነበራቸውን የቤተሰባዊ ስሜት ይበልጥ ለማጠናከር እና መጨውን አዲስ አመት በመተሳሰብና በመቀራረብ ይበልጥ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ እንዲህ መሰል ዝግጅቶች የተቋሙን ግብ ለማሳካት የሰራተኞችን ተነሳሽነት ለመጨመር እና ያሉ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እንደሚረዳ የዝግጅቱ ተሳታፊ ሰራተኞች ተናግረዋል።
Show all...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ጳጉሜን 4፤ 2016 - የኅብር ቀን “ኅብረት ለሰላማችን"
Show all...
👍 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.