cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ትምህርት መረጃ( academic info)

ትምህርትነክ እና ትክክለኛ መረጃዎች ይስተናገዱበታል።

Show more
Advertising posts
4 941
Subscribers
+1124 hours
+87 days
+31730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል። በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል። ተማሪዎች ውጤታችሁን በተከታዩ ሊንክ አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። 👇👇👇👇👇 https://result.ethernet.edu.et/
Show all...
👍 2
#AAU የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል (ሶኮላርሺፕ) ሊሰጥ እንደሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን የመጀመርያው ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን ተወስኖ ተማሪዎችን በራሱ የቅበላ ስርዓት ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ እያከናወነ ነው። ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ያዘጋጀውን የተማሪዎች መግቢያ ፈተና ይሰጣል። በዚህም ብቃትን፣ ብዝሃነትንና ፍትሐዊነትን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ገልጿል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ፈተና ወስደው 500 እና ከዚያ በላይ ላስመዘገቡ 200 ተማሪዎችን በውድድር ነፃ የትምህርት እድል ከዶርሚታሪና የካፌ አገልግሎት ጋር እንደሚሰጥ አሳውቋል። አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ " ብቃትና ተሰጥዖ ያላቸው ተማሪዎች መዳረሻ ለመሆን ያለኝን ቁርጠኝነት እገልጻለሁ " ብሏል። @minster_of_education
Show all...
👍 4
የገፁ አስተዳደር ወደፊት እንዴት ይቀጥል?Anonymous voting
  • በዚሁ ይቀጥል
  • ማሻሻያወችን ያድርግ
  • አያስፈልግም ይዘጋ
0 votes
ከትምህርት መረጃ ገፅ የሚያገኙት መረጃ ምን ያህል ጠቃሚ ነው ብለው ያስባሉ?Anonymous voting
  • እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው
  • በጣም ጠቃሚ ነው
  • በመጠኑ ጠቃሚ ነው
  • ምንም አይጠቅም
0 votes
የዚህ ገፅ ትክክለኛ መረጃወችን በማድረስ ረገድ ምን የሚሉ ላሉ?Anonymous voting
  • እጅግ በጣም ጥሩ
  • በጣም ጥሩ
  • ጥሩ
  • መካካለኛ
  • ዝቅተኛ
  • ምንም አልጠቀመኝ
0 votes
Update
Show all...
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለድኅረ ምረቃ መርሃግብር (Postgraduate) በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተፈተኑትን ተማሪዎች #እንደማይቀበል ገለጸ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል በመጀመሪያ ዲግሪ በ2017 ዓ/ም መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው  የሚያወጣውን የመግቢያ ፈተና (UAT) እንዲሁም ሌሎች መስፈርቶች እንደሚጠበቅባቸው መግለጹ ይታወሳል፡፡ ራስ ገዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ለድህረ ምረቃ መርሃግብር መግቢያ ፈተና የትምህርት ሚኒስቴር የጋት (GAT) ፈተና ያስፈተናቸዉን እንደማይቀበል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጄሉ ዑመር ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልፀዋል። ዩኒቨርሲቲው ራስ-ገዝ መሆኑን ተከትሎ ራሱን በራሱ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የማስተዳደር መብት የተሰጠው በመሆኑ የራሱን የመመዘኛ ፈተና እንደሚፈትን የገለፁ ሲሆን፤ተቋሙ በግሉ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና  በቀን መርሃ ግብር ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ እና በርቀት መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር የመጀመሪያ ዙር GAT ፈተና ማጠናቀቃቸውን ሃላፊው አክለው ገልፀዋል። #መናኸሪያሬዲዮ የተራዘመው የሁለተኛ ዙር GAT ፈተና የማመልከቻ ግዜ ዛሬ መስከረም 8/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል፡፡ እስካሁን ካላመለከቱ በቀሩት ሰዓታት በኦንላይን https://portal.aau.edu.et ያመልክቱ።
Show all...
👍 1
በ2017 ዓ/ም መማር ለምትፈልጉ  አመልካቾች በሙሉ በአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል በመጀመሪያ ዲግሪ በ2017 ዓ/ም መማር ለምትፈልጉ  አመልካቾች በሙሉ፤ በ2017 ዓ/ም በቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሃ ግብር በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  የተማሪዎች ምደባ እንደማይኖር  ይታወቃል። በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍላችሁ በዩኒቨርሲቲያችን መማር ለምትፈልጉ በሙሉ የአ.አ.ዩ  የሚያወጣውን የመግቢያ ፈተና (UAT) እንዲሁም ሌሎች መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡ በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲያችን ድረ ገጾች (www.aau.edu.et ወይም https://portal.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ • የመመዝገቢያ ቀናት እስከ መስከረም 8/ 2017 ዓ.ም ድረስ ይሆናል • የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት በ ዩኒቨርሲቲያችን ዌብ ሳይት፤  የምዝገባ ፖርታል እንዲሁም በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚገለጽ ይሆናል::
Show all...
👍 5
Assossa University Job Vacancy
Show all...
👍 4👎 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.