cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ ማኅበር

ይህ ገፅ የማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ ማኅበር official የቴሌግራም ገፅ ነው። Links Youtube፦https://youtube.com/@abekemikael Telegram : - https://t.me/abekemikael Facebook: - https://www.facebook.com/abekemikael ለ አስተያየት እና ጥያቄዎ፦ @abekemikael12

Show more
Advertising posts
337
Subscribers
No data24 hours
+27 days
+630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

01:51
Video unavailableShow in Telegram
ለ2017 ዓ.ም. ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ.mp445.93 MB
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዳር ኤኖ ነጌ ይመረቃል!!! የማኅበራችን አባል እንዲሁም ኮሚቴ የሆነው የወንድማችን ዘማሪ ደመቀ ቦንጌ ስራ የሆነው ሙሉ ለሙሉ በጉራግኛ ቋንቋ የተዘጋጀው ቁጥር 1 አልበም ሊመረቅ ነው!!! የፊታችን እሑድ ማለትም መስከረም 5፣ ቀን 2017 ዓ.ም በ ልኳንዳ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ሰዋሰወ ብርሀን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከ ጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ይመረቃል። በዕለቱም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የአድባራት አስተዳዳሪ አባቶች እና ፀጋው የበዛላቸው መምህራን እና ዘማሪያን ተጋብዘዋል። እርስዎም ይህን ማዕድ ይካፈሉ ዘንድ ተጋብዘዋል። መደበኛ የማኅበራችን ጉባዔ ስለማይኖር ሁላችንም ከ5 ሰዓት ጀምሮ በቦታው ተገኝተም መዝሙሩን እንድናስመርቅ ይሁን። ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ ማኅበር youtube: - https://youtube.com/@abekemikael Telegram : - https://t.me/abekemikael Facebook: - https://www.facebook.com/abekemikael ለ አስተያየት እና ጥያቄዎ፦ https://t.me/abekemikael12
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
  🌼  ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ  🌼  እንኳን ለቅዱስ እና ታማኝ ሐዋርያ ዮሐንስ ወንጌላዊ የልደቱ መታሰቢያ አደረሳችሁ። [ መስከረም ፬ [ 4 ] ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ልደቱ ] ካህናቱ በሰዓታት ምስጋናቸው የአምደ ሃይማኖት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን ቃል አንደበታቸው በማድረግ እንዲህ ያመሰግኑታል። [ ዮሐንስ እንደ መላእክት ንጹሕ ነው ፤ ድንግል ዮሐንስ የቅዱሳን መመኪያ ነው ፤ ዮሐንስ በብርሃን መጎናጸፊያ ሐር የተጌጠ ነው ፤ ዮሐንስ የቤተክርስቲያን አርጋኖን ነው በኤፌሶን የአዋጅ ነጋሪ ዮሐንስ ኃጥአን ለምንሆን ለእኛ ይቅርታን ይለምንልን።] [ መከራ ተቀብሎ በመስቀል ላይ ደሙ በፈሰሰ ጊዜ ዮሐንስ ፍቅሩን አላጎደለም። ] [ በወዳጁህ በዮሐንስ ድንግልና በንጽሐ ሥጋውም አቤቱ ይቅር በለን።] † በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ ማርያም ባውፍልያ: ከአባቱ ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች:: የግፍና የመከራ ጽዋዕ በመላባት ዓለማችን… ትዕግሥቱ ፤ ጥላቻና መገፋፋት በነገሠባት ምድራችን… ፍቅሩ ፤ ኃጢአትና መተላለፍ በሠለጠነባት ሕይወታችን… በረከቱ ፤ እርሱ በተወለደባት በዚህች ዕለት በእኛም ልቡና ይወለድ ዘንድ ምልጃው አይለየን። ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ ማኅበር youtube: - https://youtube.com/@abekemikael Telegram : - https://t.me/abekemikael Facebook: - https://www.facebook.com/abekemikael ለ አስተያየት እና ጥያቄዎ፦ https://t.me/abekemikael12
Show all...
👍 1
[  † እንኳን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ   † ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ሉቃ.፩፥፮] (1:6) የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ [አድናቆት] ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ [90] የዘካርያስ ደግሞ ፻ [100] ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫] (40:3), ሚል.፫፥፩] (3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው:: ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ [26] ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ [6] ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ [6] ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው:: የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ [ሰገደ]:: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ ፴ [30] ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ ፪ [2] ዓመት ከ፮ [6] ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ:: እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ ፫ [3] ፭ [5] ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ፭ [5] ፯ [7] ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት:: ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ:: ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ፳፭ [25] ፳፫ [23] ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም:: ከዚህ በሁዋላ ፴ [30] ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጄን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: [ኢሳ.፵፥፫] (40:3), [ሚል.፫፥፩] (3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" [ሉቃ.፩፥፸፮] (1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና:: ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና:: ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ "አጥምቀኝ" ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው:: "እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው:: ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: [ማቴ.፫፥፩] (3:1), ማር.፮፥፲፬ (6:14), [ሉቃ.፫፥፩] (3:1), [ዮሐ.፩፥፮] (1:6)*ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት:: ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ፲፭ [15] ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች:: ††† አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ [የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች] ፩. ነቢይ ፪. ሐዋርያ ፫. ሰማዕት ፬. ጻድቅ ፭. ካሕን ፮. ባሕታዊ/ገዳማዊ ፯. መጥምቀ መለኮት ፰. ጸያሔ ፍኖት [መንገድ ጠራጊ] ፱. ድንግል ፲. ተንከተም [የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ] ፲፩. ቃለ አዋዲ [አዋጅ ነጋሪ] ፲፪. መምሕር ወመገሥጽ ፲፫. ዘየዐቢ እምኩሉ [ከሁሉ የሚበልጥ] ††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም መጥምቁ ዮሐንስን አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን:: [  † መስከረም ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ [መጥምቀ መለኮት " ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" [ማቴ.፲፩፥፯] ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ ማኅበር youtube: - https://youtube.com/@abekemikael Telegram : - https://t.me/abekemikael Facebook: - https://www.facebook.com/abekemikael ለ አስተያየት እና ጥያቄዎ፦ https://t.me/abekemikael12
Show all...
ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘ አበኬ መንፈሳዊ ማኅበር

ይህ የ ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘ አበኬ መንፈሳዊ ማኅበር official የ ዩትዩብ ገፅ ነው።

👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
ዳር ኤኖ ሊመረቅ ነው!!! የማኅበራችን አባል እንዲሁም ኮሚቴ የሆነው የወንድማችን ዘማሪ ደመቀ ቦንጌ ስራ የሆነው ሙሉ ለሙሉ በጉራግኛ ቋንቋ የተዘጋጀው ቁጥር 1 አልበም ሊመረቅ ነው!!! የፊታችን እሑድ ማለትም መስከረም 5፣ ቀን 2017 ዓ.ም በ ልኳንዳ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ሰዋሰወ ብርሀን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከ ጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ይመረቃል። በዕለቱም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የአድባራት አስተዳዳሪ አባቶች እና ፀጋው የበዛላቸው መምህራን እና ዘማሪያን ተጋብዘዋል። እርስዎም ይህን ማዕድ ይካፈሉ ዘንድ ተጋብዘዋል። 5 ቀን ብቻ ቀረው ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ ማኅበር youtube: - https://youtube.com/@abekemikael Telegram : - https://t.me/abekemikael Facebook: - https://www.facebook.com/abekemikael ለ አስተያየት እና ጥያቄዎ፦ https://t.me/abekemikael12
Show all...
👍 3 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
"እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ በሰላም አደረሰን!!" አዲሱ ዓመት የሰላምና  የፍቅር  እግዚአብሔርን  በቅንነት የምናገለግልበት ዓመት እንዲሆንልን እንመኛለን።        🌻🌻🌻ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ🌻🌻🌻 ማኅበር youtube: - https://youtube.com/@abekemikael Telegram : - https://t.me/abekemikael Facebook: - https://www.facebook.com/abekemikael ለ አስተያየት እና ጥያቄዎ፦ https://t.me/abekemikael12
Show all...
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡- ፍጥረታትን በማደስ ሕይወትን የማስቀጠል ሥልጣን በዋናነት የእግዚአብሔር ብቻ መሆኑ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ሰውም ሥነ ፍጥረትን በማደስና በማጐስቈል ረገድ ያለው ሚና ቀላል አይደለም፤ ይህም ሰው በምድር ላይ እንዲሠለጥን ወይም ፍጥረትን እንዲገዛና እንዲመራ በፈጣሪ ከተሰጠው ሥልጣን የሚመነጭ ነው፤ ዛሬም ዓለማችን በመታደስ ያይደለ በማርጀት ላይ የምትገኘው ከሰዎች ድርጊት የተነሣ እንደሆነ እንገነዘባለን፤ የአየሩ መለወጥ፣ የበረዶው መቅለጥ፣ የሙቀቱ ማሻቀብ፣ የዝናሙ ማጥለቅለቅ፣ የባሕሩ መናወጥ ወዘተ. እየተፈጠረ ያለው ኃላፊነት ከጐደለው የሰው አጠቃቀም የተነሣ እንደሆነም ተደጋግሞ እየተነገረን ነው፤ እኛም በዓይናችን እያየን ነው፤ ከዚህ በተለየ ደግሞ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሰው ምድረ በዳውን ወደ ሐመልማለ ገነት ሲቀይር የሚስተዋልበት ሌላ ገጽታ አለ፤ ይህ የሚያሳየው ሰው በሥነ ፍጥረት ላይ የማደስና የማጐስቈል ብሎም የማጥፋት ሚና ያለው መሆኑን ነው፤ ሰውም እንደሌላው ሥነ ፍጥረት የሚያረጅም የሚታደስም ነው፤ ይህም በብዙ አቅጣጫ ሊከሠት ይችላል፤ ሰዎች በተናጠልም ሆነ በጋራ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሁለቱንም ማለትም ማርጀትና መታደስን ሊያስተናግዱ ይችላሉ፤ ሰዎች በመንፈሳዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በማኅበራዊና በመልካም አስተዳደር ወዘተ. የላቀ ዕድገትን ሲያስመዘግቡ በመታደስ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፤ የዚህ ተቃራኒ የሆነውን ይዘው እየተጓዙ ከሆነ ደግሞ ተቃራኒውን ወይም ማርጀትን እያስተናገዱ እንደሆነ ይታወቃል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች በመንፈሳቸውም ሆነ በአእምሮአቸው፣ በነፍሳቸውም ሆነ በአካላቸው በመታደስ እንዲኖሩ እንጂ እርጅና እንዲጫጫናቸው አይፈልግምና “የልባችሁን መንፈስ አድሱ” በማለት ያስተምረናል፤ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት! የክርስትና ሃይማኖት የመጨረሻው ግብ የፍጥረት መታደስ ነው፤ ይህም ማለት የሃይማኖቱ አስተምህሮ መዳረሻ ከሞት በኋላ ትንሣኤ ከዚያም ፍጻሜና እንከን የሌለው ጣዕመ ሕይወት አለ ብሎ ሰውን ለዘላለማዊ ሕዳሴ ማብቃት ነው ማለት ነው፤ ከዚህ አንጻር የሰው የመጨረሻ ዕድሉ ማርጀት ሳይሆን መታደስ እንደሆነ እንገነዘባለን፤ እግዚአብሔር የሰውንና የፍጥረታትን መታደስ የሚሻው በሰማያዊው ዓለም ብቻ ሳይሆን በምድራዊው ዓለምም ጭምር ነው፤ ለዚህም ነው በየወቅቱ የሥነ ፍጥረትን ውበት እያደሰ የሚመግበን፤ አሁን ትልቁ ጥያቄ የሚሆነው እኛስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመታደስ ተዘጋጅተናል ወይ? የሚለው ነው፤ ዛሬ እያንዳንዳችን ይህንን ጥያቄ አንሥተን ኅሊናችንን በጥልቀት መጠየቅ አለብን፤ በዚህም ሳናበቃ መልሱን በትክክል ማግኘት አለብን፤ በሁለንተናችን ለመታደስም ቈራጥ ውሳኔ በራሳችን ላይ ማሳለፍ አለብን፤ አዲሱ ዘመን አዲስና ብሩህ የሆነ የደስታ ሕይወት ሊያጐናጽፈን የሚችለው በዚህ መንፈስ ተቀብለን ስንጠቀምበት ነው፤ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት! እኛ ኢትዮጵያውያን ለብዙ ዘመናት የታደሱ ያይደሉ በርካታ ዓመታት ተጭነውን አልፈዋል፤ ቀድሞ እንበልጣቸው ከነበሩ አህጉር በታች ሆነንም በርካታ ዓመታትን አስቈጥረናል፤ የእርስ በርስ ግጭት፣ ረኃብ፣ ጦርነት፣ ድህነት፣ ኋላ ቀርነት የመልካም አስተዳደር እጦት በዓለም ፊት ልዩ መለያችን ሆኖአል፤ ዛሬም ከዚህ አልተላቀቅንም ብቻ ሳይሆን እንዲያውም አጠናክረን ለማስቀጠል ውል የገባን እስክንመስል ድረስ እየቀጠልንበት እንገኛለን፤ በእውነቱ እንዲህ የመሰለ ልምድ ልናፍርበትና ንስሐ ልንገባበት እንጂ ልናስቀጥለው አይገባም፤ በተፈጥሮ የታደለች ሁሉንም አሟልታ የምትገኝ ኢትዮጵያን የመሰለች ሀገር ይዘን ከሰው በታች ሆነን ስንገኝ በስንፍናችሁ ከምንባል በቀር የሀብተ ጸጋ እጥረት አለባችሁ የሚለን አናገኝም፤ ስለዚህ አሁንም ለኢትዮጵያውያን ልጆቻችን በአጽንዖት የምናስተላልፈው መልእክት ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውን አይደለም ለዓለም የሚተርፍ ሀብተ ጸጋ አላትና ለኔ ለኔ በመባባል የሕዝባችንን ሰቆቃው አናስረዝም፤ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ናት የሚለውን ጥሬ ሓቅ በደምብ አላምጠን መዋጥ አለብን፣ ከዚያም በእኩልነትና በአንድነት ሀገራችንን እናድስ፤ ከሌሎች በደባል የሚመጡ ነገሮችን ሳይሆን የሀገሪቱ በሆኑ ዕሤቶች እንመራ፤ ለበርካታ ዓመታት የተሸከምነው ደባል የአስተዳደር ስልት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚጣጣም ሆኖ አልተገኘም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምንም ከማንም በላይ በፈጣሪው እንደሚመካ እሱንም አጥብቆ እንደሚያምን ልኂቃኖቻችን ተገንዘቡልን፤ እኛ ኢትዮጵያውያን ከሦስት ሺሕ ዓመታት በላይ ባስቆጠረ ታሪካችን ከእግዚአብሔር ተለይተን አናውቅም፤ በዚህም ተጠቃሚዎች እንጂ ተጐጂዎች የሆንበት ጊዜ የለም፤ በለመደው እምነት ባህልና ዕሤት ሕዝቡን ብንመራው ሁሉም ነገር ቀላል ይሆንልናል፤ ከዚህ ውጭ እንምራህ ብንለው ግን ያጋጠመንን ችግር ማስቀጠል ነው የሚሆነው፤ ስለዚህ የሁሉም መነሻ ማለትም የክፋትም ሆነ የደግነት መነሻ ውሳጣዊ አእምሮአችን ነውና እሱን በማደስ በአዲሱ ዓመት አገራችንን እንድናድስ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ በመጨረሻም አዲሱ ዘመን በሃይማኖት መንፈስ ግጭትን በውይይት፤ መለያየትን በአንድነት፤ አለመግባባትን በዕርቅ ፈትተን በመታደስ ማማ ላይ የቆመ ማኅበረ ሰብን ለመገንባት ሁላችንም ጥረት እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ አዲሱ ዓመት የሰላም የዕርቅ የእኩልነትና የአንድነት ያድርግልን፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!! አሜን:: አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 🌻🌻🌻ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ🌻🌻🌻 ማኅበር youtube: - https://youtube.com/@abekemikael Telegram : - https://t.me/abekemikael Facebook: - https://www.facebook.com/abekemikael ለ አስተያየት እና ጥያቄዎ፦ https://t.me/abekemikael12
Show all...
ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘ አበኬ መንፈሳዊ ማኅበር

ይህ የ ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘ አበኬ መንፈሳዊ ማኅበር official የ ዩትዩብ ገፅ ነው።

2🙏 1
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወሰብዓቱ ዓመተ ምሕረት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤  በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፡፡ ሁለመናችንን በሐዲስ ምግብና እየመገበ የሚጠብቀን አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2016 ዓ.ም. ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2017 ዓ.ም. በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!! ‹‹ሐድሱ መንፈሰ ልብክሙ፤ የልባችሁን መንፈሳዊ አእምሮ አድሱ›› (ኤፌ. ፬÷፳፫)፤ በገሃዱ ዓለም በግልጽ እንደምናስተውለው ከሞላ ጎደል የማያረጅ የለም የማይታደስም የለም፤ መታደስ ባይኖር ኖሮ ሕይወታውያን ፍጡራን በሕይወት መቀጠል አይችሉም ነበር፤ የዘመን መታደስም የሥነ ፍጥረት አንዱ አካል ነው፤ እኛ ሰዎችም የሕዳሴው መሪዎች ሆነን የተሾምንባትን ምድር በየጊዜው በልማት እንድናድሳት እግዚብሔር አዞናል፤ የሃይማኖት ትልቁ ተስፋም መታደስ ላይ የተመሠረተ ነው፤ ዘመንም እንደ ሌላው ያረጃል፤ ይታደሳልም፤ “ወናሁ እገብር ኵሎ ሐዲሰ እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” የሚለው የእግዚአብሔር ቃልም የዚህ አስረጅ ነው፤ በዚህ ሕገ እግዚአብሔር መሠረት እነሆ አሮጌውን ዘመን የምንሸኝበት አዲሱን ዘመን ደግሞ የምንቀበልበት ምዕራፍ ላይ ነን፤
Show all...
ጳጉሜን በጸሎት ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ ማኅበር ጳጉሜን በጸሎት እያሳለፈ ይገኛል። 5ቱም ቀናት የጸሎት መርሀግብር በማኅበሩ ፅ/ቤት ተዘርግቷል። ዛሬ ቅዳሜ እና ሌሎች ቀናት ከ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ፣ ነጌ እሁድ በመደበኛ የጉባዔ ሰዓት (ጠዋት 4ሰዓት) ተገኝተን ስለ ሀገራችን እንዲሁም ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ። 🌻🌻🌻ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘአበኬ መንፈሳዊ🌻🌻🌻 ማኅበር youtube: - https://youtube.com/@abekemikael Telegram : - https://t.me/abekemikael Facebook: - https://www.facebook.com/abekemikael ለ አስተያየት እና ጥያቄዎ፦ https://t.me/abekemikael12
Show all...
ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘ አበኬ መንፈሳዊ ማኅበር

ይህ የ ማኅበረ ቅዱስ ሚካኤል ዘ አበኬ መንፈሳዊ ማኅበር official የ ዩትዩብ ገፅ ነው።

👍 10
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.