cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

AMN-Addis Media Network

This is an official Telegram channal for Addis Media Network (AMN) We trive to be the prime informer of issues. Hence, our motto says so, 'first to inform' ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ !! contact us via:- E-mail:- [email protected] twitter.com/AmnAddis

Show more
Advertising posts
33 585
Subscribers
-1924 hours
-1167 days
-61530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲሱ የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮና ሆነው ተመረጡ AMN- መስከረም 9/2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ3 ዓመታት የሚቆይ አዲሱ የኢጋድ የቱሪዝም ሻምፒዮና ሆነው ተመርጠዋል፡፡ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ባወጣው መረጃ ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢጋድ አባል ሀገራት ዘላቂ የቱሪዝምና ኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት እንዲሁም በባህል እና በአካባቢ ጥበቃ ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይጠበቃል ብሏል። #Addisababa #Ethiopia ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን! https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
Show all...
👍 20 8😁 4
ህፃን ቅዱስ ተ/ማርያም መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ AMN - መስከረም 9/2017 ዓ.ም የ4 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያለው ቅዱስ ተ/ማርያም የተባለ ህፃን መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ ራስ አበበ አረጋይ ት/ቤት ለትምህርት እንደሄደ በዚያው መጥፋቱን የተመለከተ አዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ማሰራጨቱ ይታወሳል፡፡ ህፃኑ በዚያው እለት ናይጄሪያ ኤምባሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መገኘቱ እና በህብረተሰቡ ትብብር ወደ ፖሊስ መምጣቱ ታውቋል፡፡ ለህፃኑ መጥፋት ምክንያት የሆነውን ክፍተት የጠየቅናቸው የራስ አበበ አረጋይ የቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ፍቃዱ ሃተኡ እንዳስረዱት መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ/ም ትምህርት ሲጀመር ለተማሪ ወላጆች ስለ አጠቃላይ ሁኔታ ኦረንቴሽን የተሰጠ ቢሆንም የህፃኑ ወላጆች በዕለቱ አለመገኘታቸው ነው፡፡ … ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ማስፈጠንሪያውን (ሊንክን) ይጣኑ https://www.facebook.com/Amnaddistv/posts/pfbid0dwFtXm2zt4oMrz9EBpednN4GUswAJkfmZgLqk1HK3UoUoHjK6NZ4dGsc1qNB5Biil
Show all...
AMN-Addis Media Network

ህፃን ቅዱስ ተ/ማርያም መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ AMN- መስከረም 9/2017 ዓ.ም የ4 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያለው ቅዱስ ተ/ማርያም የተባለ ህፃን መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ ራስ አበበ አረጋይ ት/ቤት ለትምህርት እንደሄደ በዚያው መጥፋቱን የተመለከተ አዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ማሰራጨቱ...

👍 9
Photo unavailableShow in Telegram
ህፃን ቅዱስ ተ/ማርያምን ያየ ወይም ያለበትን የሚያውቅ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠየቀ AMN - መስከረም 8/2017 ዓ.ም ቅዱስ ተ/ማርያም ዕድሜው 4 ዓመት ከ8 ወር ሲሆን መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ ትምህርት ቤት እንደሄደ በዚያው መጥፋቱን የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመልክቷል፡፡ ህፃን ቅዱስ ተ/ማርያም የሚማረው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የሚገኘው ራስ አበበ አረጋይ ት/ቤት ሲሆን ወላጆቹ ጠዋት ወደ ት/ቤት አስገብተውት ከሰዓት በኋላ ለማውጣት ሲሄዱ እንዳላገኙት በመግለፅ ለክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አመልክተዋል፡፡ በመሆኑም ህፃን ቅዱስ ተ/ማርያምን ያየ ወይም ያለበትን የሚያውቅ በስልክ ቁጥር 011-1-57 34 26 ለአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ደውሎ በማሳወቅ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግ መጠየቁን ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
Show all...
👍 18 3
የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን የሚጠቀምባቸው የመገናኛ መሳርያዎች ፈንድተው ቢያንስ 9 ሰዎች ሞቱ AMN - መስከረም 8/2017 ዓ.ም በመቶዎች የሚቆጠሩ የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን አባላት የሚጠቀሙባቸው የመገናኛ መሳሪያዎች በሊባኖስ እና በሶሪያ በተመሳሳይ ጊዜ ፈንድተው የ8 ዓመት ህጻንን ጨምሮ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን እና በብዙ ሺዎች መቁሰላቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል። ሂዝቦላህ እና የሊባኖስ መንግሥት የተራቀቀ ላሉት ጥቃት እስራኤልን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን ከእስራኤል በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡ የኢራን የሊባኖስ አምባሳደር በተመሳሳይ ፍንዳታዎች ከቆሰሉት 2 ሺ 800 ሰዎች መካከል ይገኙበታል። ምስጢራዊው ፍንዳታ በእሥራኤል እና በኢራን በሚደገፈው ሂዝቦላህ መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የተከሰተ ነው። የቡድኑ መሪ ባላፈው የካቲት ወር አባላቱ ከዚህ ቀደም ይጠቀሙበት የነበረውን ተንቀሳቃሽ ስልክ በእስራኤል ሊጠለፉ ይችላሉ በሚል ስጋት መጠቀማቸውን እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ካስተላለፉ በኋላ ነበር አሁን ፍንዳታ ያስከተሉት የመገናኛ መሳርያዎች ጥቅም ላይ የዋሉት፡፡ አንድ የሂዝቦላህ ባለሥልጣን የመገናኛ መሳርያዎቹ አዲስ እንደሆኑ ለአሶሲዬትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 3፡30 ገደማ መሳርያዎቹን የያዙ እና በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ የነበሩ ሰዎች በእጃቸው ወይም በኪሳቸው ውስጥ የነበሩት የመገናኛ መሳርያዎች ሙቀት መፍጠራቸው እና መፈንዳታቸው ነው የተነገረው፡፡ መሳርያውን ከያዙ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ የሂዝቦላህ አባላት ሲሆኑ የቡድኑ አባላት ያልሆኑ ሰዎችም የፈነዱትን መሳርያዎች ይዘው ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
Show all...
👍 8 4💩 1
የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን የሚጠቀምባቸው የመገናኛ መሳርያዎች ፈንድተው ቢያንስ 9 ሰዎች ሞቱ AMN - መስከረም 8/2017 ዓ.ም በመቶዎች የሚቆጠሩ የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን አባላት የሚጠቀሙባቸው የመገናኛ መሳሪያዎች በሊባኖስ እና በሶሪያ በተመሳሳይ ጊዜ ፈንድተው የ8 ዓመት ህጻንን ጨምሮ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን እና በብዙ ሺዎች መቁሰላቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል። ሂዝቦላህ እና የሊባኖስ መንግሥት የተራቀቀ ላሉት ጥቃት እስራኤልን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን ከእስራኤል በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡ የኢራን የሊባኖስ አምባሳደር በተመሳሳይ ፍንዳታዎች ከቆሰሉት 2 ሺ 800 ሰዎች መካከል ይገኙበታል። ምስጢራዊው ፍንዳታ በእሥራኤል እና በኢራን በሚደገፈው ሂዝቦላህ መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የተከሰተ ነው። የቡድኑ መሪ ባላፈው የካቲት ወር አባላቱ ከዚህ ቀደም ይጠቀሙበት የነበረውን ተንቀሳቃሽ ስልክ በእስራኤል ሊጠለፉ ይችላሉ በሚል ስጋት መጠቀማቸውን እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ካስተላለፉ በኋላ ነበር አሁን ፍንዳታ ያስከተሉት የመገናኛ መሳርያዎች ጥቅም ላይ የዋሉት፡፡ አንድ የሂዝቦላህ ባለሥልጣን የመገናኛ መሳርያዎቹ አዲስ እንደሆኑ ለአሶሲዬትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 3፡30 ገደማ መሳርያዎቹን የያዙ እና በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ የነበሩ ሰዎች በእጃቸው ወይም በኪሳቸው ውስጥ የነበሩት የመገናኛ መሳርያዎች ሙቀት መፍጠራቸው እና መፈንዳታቸው ነው የተነገረው፡፡ መሳርያውን ከያዙ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ የሂዝቦላህ አባላት ሲሆኑ የቡድኑ አባላት ያልሆኑ ሰዎችም የፈነዱትን መሳርያዎች ይዘው ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
Show all...
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeJaHPcwzUaUKluXU8EVKILOqT6XZ6l9LEpgQs6WGEyqADKUQ/viewform?usp=sf_link ውድ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችን፣ ኤ ኤም ኤን ከቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ እና ዲጂታል ሚዲያ በተጨማሪ የይዘት ውጤቶቹን ለረዥም ዓመታት በጋዜጣም (አዲስ ልሳን) ወደ እናንተ በማድረስ ላይ ይገኛል። 📃 አዲስ ልሳን ጋዜጣ በይዘቷ፣ በአቀራረቧ እና በስያሜዋ በአዲስ መልክ እንድትመጣ ጥናት እያደረግን ሲሆን እናንተም ለጥናቱ ግብዓት ይሆነን ዘንድ ከላይ የቀረበውን መጠይቅ በመሙላት እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን። አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የትውልድ ድምፅ! መስከረም 07/2017 ዓ.ም
Show all...
የአዲስ ልሳን ጋዜጣ ስያሜን በተመለከተ የአንባቢያንን ምርጫ ለመዳሰስ የተዘጋጀ ጥናት

👍 5 3
በ12ኛ ክፍል ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡት ጓደኛማቾች AMN - መስከረም 6/2017 ዓ.ም እያሱ ሰለሞን እና ፍራኦል ጥበቡ ይባላሉ፡፡ በ2016 የትምህርት ዘመን በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ተፈትነዋል፡፡ እያሱ ሰለሞን በተፈጥሮ ሳይንስ 541 ውጤት ያመጣ ሲሆን ፍራኦል ጥበቡ ደግሞ 539 ያመጣ የእያሱ የቅርብ ጓደኛ እና የክፍል አጋር ነው፡፡ ሞገስ አክሊሉ እና ቦንሳ ሌንጂሳም በዚሁ ትምህርት ቤት የ2016 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ባለከፍተኛ ውጤት ተማሪዎች መካከል የጠበቀ ወዳጅነት ለዓመታት የተገነባ ወንድማማችነት ደግሞም ነገን መሰረት ያደረገ ህልምና ራዕይ ያፀናው ጓደኝነት ይስተዋላል፡፡ በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ለአራት ዓመታት በጓደኝነት ያሳለፉና በጋራ በማጥናት ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችም ናቸው ፡፡ በጋራ ማጥናት ፤ መረዳዳትና የአስተማሪዎቻቸው ጥረት ለውጤት እንዳበቃቸው ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡ ባለከፍተኛ ውጤት ተማሪዎች ተመሳሳይ ህልምን ሰንቀው ወደ ከፍተኛ ትምህርት የመግባት ዝግጅታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡ በህክምናው እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የመሰማራት የጋራ ውጥንም ይዘዋል፡፡ ገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት በ2016 የትምህርት ዘመን ያስፈተናቸውን 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሁሉንም አሳልፏል፡፡ ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን መቀበል የጀመረው ገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 88 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ በካሳሁን አንዱዓለም
Show all...
👍 9 3
በጃፓን በዕድሜ የገፉ ሰዎች ቁጥር ከ36 ሚሊዮን መብለጡ ተገለጸ በጃፓን ዕድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ዜጎች ከ36 ሚሊዮን መብለጡ እና ይህም ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ሕዝብ ቁጥር ወደ 30 በመቶ የሚደርሰውን እንደሚሸፍኑ መንግሥት ያወጣው መረጃ አመላከተ። በሀገሪቱ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ከሀገሪቱ ሕዝብ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት 65 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ እንደሆኑ የመንግሥት መረጃ ያመላክታል። የጃፓን የሀገር ውስጥ ጉዳይ እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሀገሪቱ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ወደ 29.3 በመቶ የሚሆነውን የሕዝብ ብዛት ያቀፉ ሲሆን፤ ይህም ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ካሉበት ማንኛውም ሌላ ሀገር የበለጠ ነው ብሏል። ዕድሜያቸው 65 ዓመት እና ከዚያ በላይ ከሆናቸው ሰዎች መካከል 20.53 ሚሊዮን የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ፣ 15.72 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አያይዞ ገልጿል። ጃፓን ከጊዜ ወደ ጊዜ የወጣቶች ቁጥር መቀነስ እና በዕድሜ የገፉ ሰዎች ቁጥር መጨመር የጤናና የደኅንነት ወጪያቸው እየጨመረ ከመሄዱ ጋር ተዳምሮ ከገጠማት ቀውስ ጋር እየታገለች ነው ተብሏል። የጃፓን ሕዝብ ቁጥር ለ13ኛ ተከታታይ ዓመት እየቀነሰ የመጣ ሲሆን፣ በፈረንጆቹ ጥቅምት ወር ላይ በ595 ሺህ ዝቅ ማለቱም ተጠቁሟል። በቶኪዮ የሚገኘው ብሔራዊ የሕዝብ ቁጥርና ማኅበራዊ ደኅንነት ምርምር ተቋም በጃፓን በ2040 34.8 በመቶ የሚሆነውን የሕዝብ ቁጥር የሚይዙት አረጋውያን እንደሚሆኑ መግለፁን አልጀዚራ ዘግቧል። በቶኪዮ የሚገኝ አንድ የምርምር ተቋም ባለፈው ዓመት ባወጣው ጥናት፤ ጃፓን እያሽቆለቆለ ያለውን የሕዝብ ቁጥር ተከትሎ በ2040 ከ11 ሚሊዮን የሚልቅ የሠራተኞች እጥረት ሊገጥማት እንደሚችል ገልጿል።
Show all...
👍 7 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል AMN-መስከረም 6/2017 ዓ.ም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ እንዲካሄድ ወስኗል። ጉባዔው በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሊከናወን ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ሀገሪቱ ማስተናገድ እንደማትችል ማሳወቋን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ጉባዔውን ለማካሄድ ጥያቄ አቅርቦ ካፍ የኢትዮጵያን ጥያቄ ተቀብሏል። በዚህም መሰረት የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በጥቅምት ወር በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚከናወን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Show all...
👍 7
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.