cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ካሊድ አቅሉ

"ከባባድ ጥያቄዎች በቀላል መልሶች ይረታሉ" ሀሳብ ለማስፈንጠር.... @kalu30

Show more
Advertising posts
11 817
Subscribers
-1124 hours
+267 days
-10730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ነፍሷን የረሳች ሴት (ክፍል ፫) ———————— ሀኑ ወደ ቤት እንደገባች ወደ ክፍልዋ በመግባት መሳቢያዉን ከፍታ ፖስፓርትዋን ይዛ ከቤት ልትወጣ ስትል እናትዋ አይሻ “ልጄ በዚህ ፍጥነት ወደ የት ነዉ ? ምሳሽንስ አትበዪም? ደግሞ ወጤት ወጥተዋል አሉ አየሽ ? የጋሽ ነጋ ልጅ እኮ አለፍኩኝ አለኝ ከገበያ ስመለስ አጊንቼዉ እስኪ እዪ ፈጣሪ የፈቀደዉ ይሆናል አልዋት ሰማይ ሰማዩን በትካዜ እያዩ ( ደብተር በእጅዋ ይዛ ስታነብ አይተዋት ስለማያዉቁ) “ እሺ ማሚ “ ብላ መሬት መሬት እያየች በሩን ከፍታ ወጣች ። የዉጪ ስራ አገናኝ አጀንሲ ሄደችና መሄድ ምትፈልግበትን ሀገር እና የእሷን አድራሻ የሚነግር ቅፅ ሞልታ ደዉለን የትኬቱን ዋጋ እና ሙሉ መረጃ ቀድመን እናሳዉቅሻለን ብለዋት ወደ ቤትዋ ተመለሰች ። በሩን ከፍታ ስትገባ እናትዋ በረንዳ ላይ ተቀምጠዉ ምስር ይለቅማሉ ፣ “ እንዴት ሆንሽ ልጄ ?” አልዋት የምስራች እየጠበቁ “ማሚ አልሆነም !” አለቻት እና የእናትዋን አይን ለመሸሽ ይመስል ሀይል ጨምራ ወደ ዉስጥ ገባች ሁለት ታናሽ እህቶች አልዋት ዉዴታቸዉ ከሀገር የገዘፈ እሷም በነሱ አትደራደርም ፣ አባታቸዉ የከባድ መኪና ሹፌር ስለሆነ በበአላት ወቅት ብቻ ነዉ ወደ ቤቱ ጎራ የሚለዉ ። ክፍልዋ ገብታ ከመቀመጥዋ የስሜትዋን መረበሽ የተረዱት እህትዎችዋ ያቅማቸዉን ማፅናኛ ቃል አሻገሩ ሰፈር ዉስጥ የመዉደቅዋ ዜና በሹክሹታ ሲወራ ሰምተዋል ። እንዳይከፋቸዉ የከፋት ሳትመስል አቀፈቻቸዉና ምሽቱን በጫወታ ሰብሰብ ብለዉ አሳለፉት ። ለካንስ መዉደቅ መቆዘምን መከናነቡ ነዉ። ለመንሸራተት እድል ካልሰጡ ምን መሬት ቢገኙ ዘመን ጥልዋቹ ቢሄድ ደስታና ተስፋን ከሸመቃቹ የአሸናፊዎች አሸናፊ ናቹ። ከሁለት ሳምንት ቡኃላ ኤጀንሲዉ እንደ ደወለላት ለመሄጃም ወደ ሀያ ሺህ ብር ገደማ እንደሚያስፈለግ ለእናትዋ ነገረቻት። እናትየዉ ሀዘን ባጠመቀዉ አተያይ “ ማን ይቸገርልን ይሆን እኔ ጋር ለሀዘንም ለደስታም ከሆነ ብዪ የቆጠርኳት አስር ሺህ ብር ገደማ ምትሆን ፍራክ አለች የቀረዉን አባትሽን ፈልግ እለዋለዉ ጎረቤታችንም እነ አካሉም ከጠየኳቸዉ አያሳፍሩኝም ደህነት በሽታ ብሎ ብሎ ከምወዳት ልጄ ሊነጥለኝ ነው ይሁና አንድ ቀን እናሸንፈዉ ይሆናል “ አሉና ያቀረረዉን እንባቸዉን በሺቲያቸዉ ጫፍ እየጠረገች አላህ ብቻ ልጅዎቼን አይቀንስብኝ” አለች እጅዋን ዘርግታ ተማፅኖዋን ለፈጣሪዋ እያሰማች ። አባትዋ በስልክ ተነገረዉ ሆደ ቡቡ አባት ነዉ ያላት መሄድ መወሰንዋን የትምህርትዋን ዉጤት ሲሰማ ስቅስቅ ብሎ ማልቀሱን ደብቃ ደወልላታለዉ ብሎኛል ብላ እናትዋ ነገረቻት። በማግስቱም ድውሎ በርቺ የኔ አለም ፈጣሪ የወደደዉን መንገድ ነዉ የመረጠልሽ ብሎ በፍቅር ቃላት የማፅናኛ ስንኞች አቀበላት ። አስራ ሁለት ሺህ ብር ለእናትዋ እንደ ላከ በቅርብም እንደ ሚመጣ ነግርዋት ስልኩን ዘጋዉ ። ይቀጥላል …………………………..
Show all...
👍 15👏 1
ነፍሷን የረሳች ሴት (ክፍል ፪) - - - - - — - - - - - ሀናን አዘዉትራ ክፍል ማትገባ ብትገባም ከኃላ ምትቀመጥ አስተማሪዎች በፀባይዋ ደጋግመዉ ሚማረሩባት የግቢዉ ቆንጆ እንስት ነበረች ። የፍቅር ደብዳቤ እንደ ጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ በአይነት በአይነቱ የሚጎርፍላት የክፍሉ ሰብለ ወንጌል ተብላ የምትጠራ ሀያዎቹን እድሜ በቅርበት ምታይ ታዳጊ ወጣት ነበረች ። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ዉጤት ተለቆ ለማየት ኢንተርኔት ካፌ ከጓደኞችዋ ጋር ሰልፍ ይዘዋል የጨነቀዉ ፊት ፣ የሚንቆራጠጡ ተማሪዎች ዝምታ ዉጧዋቸዉ እርስ በእርስ ይተያያሉ ። በተራቸዉ መሰረት ኢንተርኔት ካፌ ዉስጥ ያለዉ ልጅ ባሰለፋት አይዲ ቁጥር መሰረት ዉጤት እያየ ስማቸዉን እየጠራ ያስገባል። ሜሮን ሙሉጌታ ናት ከአራት ጓደኛሞች መሀል መጀመርያ የተጠራችዉ በፍጥነት ወደ ወስጥ አቀናች “አቤት!” ሚለዉን ቃል አስቀድማ ከሁለት ደቂቃ ቡኃላ “ ወላዲትዋ ከጉድ አወጣቺኝ አለፍኩላቹ”ብላ ሀናን, ትዝታ እና ሀያት ላይ ተጠመጠመችባቸዉ ። እሰይ ብለው ተቃቀፉ ተረኛዋ ትዝታ ወለዴ ገባችና እሷም ሳቅ ባፈነዉ ድምፅ የመስከረም ፀሀይ መስላ መጣች “እረዳኝ እኮ “ ብላ መጥታ ተደፍታ ምስጋናዋን አደረሰች በቅድሙ ድምፀት እንኳን እረዳሽ እያሉ አቀፏት ተረኛዋ ተጠሪ ሀናን አብዱ ወደ ዉስጥ ዘለቀች ። በለዘበ ሳቅ ተመለሰች ፣ ያልዘራዉ እህል እንደ ማይበቅል ያወቀ ገበሬ ይመስል ብዙ አላስደመማትመ‍ም ። ጓደኞችዋ አልፍያለዉ የሚለዉን ቃል ጥበቃ ሊያቅፏት ለመንደርደር ቃል ከአፍዋ ጠበቁ እጅዋን ዘርግታ “ I’m sorry አልሆነም” አለቻቸዉ ። እርስ በእርስ ተያዩ እሷን ማየት ትተዉ ፣ ማዘናቸዉን በሚናገር ድምፅ ተይዉ ላንቺ ያለዉ የትም አይሄድም አልዋትና ስምዋ የተጠራዉን ሀያት በድሩን በአይናቸዉ ወደ ዉስጥ ሸኝዋት ከደቂቃዎች ቡኃላ በማይታወቅ ግራ የገባዉ ገፅታ ወደነሱ ተመለሰች በሀናን መዉሰቅ አዝና እንጂ አልፉለች ተያይዘዉ ወደ ሰፈራቸዉ አቀኑ ። ይቀጥላል ……………………..
Show all...
👍 33 6🤔 2
ነፍሷን የረሳች ሴት (ካሊድ አቅሉ) ክፍል ፩ ———————————————- ዕለቱ ረቡዕ ነዉ ። የካቲት 28. 2008 በኛ አቆጣጠር ፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የፅኑ ህሙማን ክፍል በርከት ባሉ ሰዎች የዬዬ ድምፅ ተጨናንቅዋል። ጭንቅላቱን ይዞ እንባዉን የሚያራግፍ ከፅኑ ህሙማን ክፍል ወደ ዉጪ እየተመላለሰ የሟችዋን ስም እየጠራ“አመለጥሺን” የሚል ሲቃ ሚያወጣዉ ድምፅ በካንሰር ህመም በ አርባ አመትዋ ለተለየችዉ ጎልማሳ ይዠጎደጎዳል። ቅን ሰዉ ናት ያለፈችዉ ። ለራሷ ጠግባ ሳታድር የሰፈሩን አዛዉንቶች ለማጥገቡ ምትታትር ሰዉነትን አቡዝታ የያዘች ከየት መጣ ሳይሆን ምን አጥቶ መጣ ሚለዉ ሚገዛት ዉብ ፀዳል እናት ዛሬ አረፈች፣ ሞት የማይቀረዉ ዕጣ እቺን ቆሻሻ አለም ጥላት ኮበለለች ። ለአመት ጥቁር አንበሳ በተኛችባቸዉ ወቅቶች ለደቂቃ ከአጠገብዋ ሳትርቅ ያስታመመቻት የመጀመርያ ልጅዋ ሀናን እራስዋን ስታ አስተኝተዋታል ። አንዳንዴ ሞት ዘላለም ጋር የሚገኝ ማንደርስበት እሩቅ ሀገር ይመስለናል ፣ አንዳንዴ ሞት መጣዉ ሳይል ስለሚከሰት በሩን ሲያንኳኳ ያዋክበናል ። ከተኛችበት አልጋ ሆና በቀስታ አይንዋን ገለጠች ። “ ሀኑ ነቃሽ?” አልዋት አይንዋ ሲስለመለም ያዩ ቤተ ዘመዶች እየተጠባበቅዋት ነበር። ህልም በሆነ ተመኘች ከእናትዋ “ሀኒዬ ደህና አደርሺልኝ?”የሚል ድምፅ ለመስማት ጓጉታ ጆሮዋን ቀሰረች ምንም የለም ! ለካ ፍፃሜዉ ሲበሰር መለያየት ግድ ሲሆን ነገር አለሙ ዉሉን ያቆርጣል ( ከትዝታ በቀር) ። እጅዋ ላይ ግልኮስ ተሰክትዋል ደም ማነስ ስላለባት እና እናትዋን በምታስታምምበት ወቅት በአግባቡ ትመገብ ስላልነበር አቅም አጥታለች በሚል ነበር ዶክተሮቹ የሰጥዋት ሀኑ በተኛችበት ወደ ኃላ በትዝታ ነጎደች ወደ አስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪነት ዘመንዋ ሄደች ወደ የካቲት አስራ ሁለት ትምህርት ቤት ቆይታዋ ስለ እፍላ ዘመን ትኩሳትዋ በሀዘን ፈረስ ወደ ትናንትዋ ጋለበች ።
Show all...
👍 30😢 17
አወረዳቸዉ። (ካሊድ አቅሉ) ተከሰቱ በዛ ድቅድቅ ያንን ፅልመት ለመሰንጠቅ በስራቸዉ የጠለቁ በምግባርም የደነቁ የረጉ የጠዋት ፀሀይ እኛን ከእድፍ ተከላካይ ያዝናሉ ያሳዝናሉም እንደ ሰዉ ደርሰዉ አይቀሉም ምስለ ትዕግስት ያልቸኮሉ ቂምን ሽረዉ ያን ይቅርታ የተከሉ ቁረይሾች ቢሉት ደርሶ ድግመተኛ መሀመድ ንጋት ነዉ ደኑ ላይ ያልተኛ ! አወረዳቸዉ ስንጨቀይበት ሽርክ መንደር ስንከርምበት አመጣቸዉ ምድርን ሊያፀዳ ሊቀንስ የኛዉን እዳ ፣ በጉዞ ሳሉ የፀሀይ ንዳድ እንዳይነካቸዉ ደመና ባቅሙ ዛፍ ጥላ ሆኖ የከለላቸዉ ፣ ፍጥረት አለሙን አስተነተኑ ሰርክ ከትመዉ ከሄራ ዋሻ ምስኪኑ ድንጋይ የካደማቸዉ ምግብ አኑሮ የርሀብ መርሻ ፤ አንብብ ተባሉ ካሉበት ወርዶ የቁርአን ሱራ ጅብሪል ሲያቅፏቸዉ ዉቡ መለአክ ይባሱን ጠራ አቡኪ ወዳጁም ለአላህ ጥሪ አጎበደደ ሌት ተቀን ሳይል በረሱል መንገድ ለአላህ ሰገደ፣ ነቢማ ጣር ተናንቋቸዉ አፋቸዉ ልባቸዉ መርቶት ኡመቴ ነበር ቃላቸዉ !
Show all...
42👍 11
መዳን እንዳይርቀህ ህመምህ እንዳይጠና ችግርህን አጢን ክፍተትህን አጥና ። ወትሮስ ….. እራስን ሳይነኩ ሌላዉን መመርመር የራስን አንድዶ ከሰዉ ጎጆ ማደር! ( ካሊድ አቅሉ)
Show all...
56👍 16👏 13🫡 1
ስጋዋን እየፈተገች ነፍስዋን እረሳችዉ ። ከአስር የዘለሉ ዉድ ሽቶዎች እያርከፈከፈች ለነፍስዋ ጥቂት የፈጣሪ ቃል መመገብ ተሳናት ። ሰዉም ወረተኛ አይደል “ዉይ ቤትሽ ፣ ዉይ መልክሽ ፣ እያለ በጭብጨባ ደፈጠጣት ። አምራ አላማረችም ሳቅዋ ደርሶ እያርስም እተኩሬ ሳያት ሚያምር እቃ ግን በድን ነፈስ አልባ መስላለች ። አሁንም ከፈጣሪዋ ለመራቅ በሀይል እየሮጠች ነው ፣ ብርሀንን በወጉ ያላየ ጨለማን መልመድ ይቀለዉ ይሆን ? እኔንጀ (ካሊድ አቅሉ) “ነፍስዋን የረሳች ሴት “ በሚል ርዕስ ወደ እናንተ ለማቅረብ ካሰናዳዋት ልብ ወለድ የተቀነጨበ ።
Show all...
👏 67 23👍 8🥰 1
Repost from ካሊድ አቅሉ
" ከእብዶች መሀል የተገኘ ጤነኛ ከእብዶቹ በላይ ይታዘንለታል ። " (ካሊድ አቅሉ ) ስህተታችን የሚጀምረው ጓደኛዬ አይደል እህቴ አይደለች ባሌ እኮ ነው በደንብ አውቀዋለው በደንብ አውቃታለው ብለን የማወቅን ልኬት መጎናፀፋችን ነው ። የሰው ልጅ አንብበን ጨረስን ስንለው ያላነበብነው እልፍ አእላፍ ምዕራፍ ምናገኝበት ሁሌ አዲስ የሆነ ፍጥረት ነው። ይሄን ደግሞ የተገፉ የተረሱ እና አታስፈልጉም ተብለው ጥግ የተጣሉትን ሰዎችን ጠይቅ። ስለተሳሳትክ ብቻ አትገፋም ። ልክነትን ተላብሰህ በስህተተኞች መነፅር ጥራትህን በእድፋቸው አንፀባርቀውት ገለል በል ልትባል ትችላለህ። እብደት እኮ ትርጓሜው እንደያለህብት ቦታ ነው ። ከእብዶች መንደር ጤነኛ ሆነህ ብትገኝ ከእብዶቹ በላይ ይታዘንልሀል ፣ አረ እንደውም " ወይ ሲያሳዝን " ብለው ከንፈራቸውን ይመጠብሀል ። @kalidakelu
Show all...
👍 58 24
እንድተኛ ሲዳብሱኝ ( ካሊድ አቅሉ) ስጀምር ህልሜን ለመኖር ስቀልስ የራሴን                   መንገድ   ብዙ ጎርፍ አስቸግሮኛል ከመክሊቴ ጋር                 እንዳልሰደድ እሳቴን ስጭር አዛኝ መስለው እፍፍ                እያሉብኝ ምጡን ስሻገር ንጋት ሲወርሰኝ ጀንበር ቀኔ             ላይ አቃሰቱብኝ ብሻገርም ብዙ ፅልመት እሩጫዬን             መቼ አበቃው ግን አውቃለው አንድ ሚስጥር እንድተኛ    ሲዳብሱኝ ይበልጡኑ እንደነቃው !
Show all...
36👏 8🤗 4🔥 3
እድሜዬን ቀጣኝ ( ካሊድ አቅሉ) ፍዝ ነበርኩኝ የት ነኝ ማልል ምኖርበትን ምክንያት ማላውቅ ከመጣው ጋራ እየተራመድኩ ያለ ምክንያት ቦታዬን ምለቅ ፤ ቃሉን በተግባር ሳልገልጥ ከአምላኬ ጋር ተኳርፌ አቅሙን ማን ሊሰጠኝ ነው ወደ ገነት አለም ሀገር የምሻገረው ቀዝፌ ? መኖሬ ላይ ስግደረደር እንደ መናቅ ሲቃጣኝ ትንፋሼ ችሎት አቁሞ መቆሜ እድሜዬን ቀጣኝ !
Show all...
👍 42 16👏 11
Repost from ባይራ |Bayra
ባይራ ዲጂታል መጽሔት ባይራ ቅጽ 1 ቁጥር 8 በእነዚህ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ቤተሰባችን ይሁኑ! ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/ ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital ለማንኛውም አስተያየት ብሎም ጽሑፍ ለመላክ ኢ-ሜይል- [email protected] ኑኒ ባይራክ! ታላላቆች ነን!
Show all...
ባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 8.pdf5.10 MB
4👍 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.