cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል። ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ ስልክ- 0935439820 ኢሜይል- [email protected]

Show more
Advertising posts
1 334
Subscribers
+524 hours
+57 days
-130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አሽከርካሪ በተሽከርካሪዉ አነዳድ አልያም ተሸከርካሪዉን ከመቆጣጠር አንፃር በሙያዉ ሊያደርገዉ ሲገባ ያላደረገዉ የጥንቃቄዉ ጉድለት አለመኖሩን ካልተረጋገጠ አደጋ በደረሰበት ሰዓት መንጃ ፈቃድን ይዞ ያለመገኘት ከደረሰዉ አደጋ ጋር የሚያገናኘዉ ጉዳይ የለዉም፡፡ በአርግጥ ማንኛዉም አሽከርካሪ ተሸከርካሪን ለማንቀሳቀስ የሚያስችለዉ ፈቃድ ያለዉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥለትን ምስክር ወረቀት ይዞ መገኘት ያለበት ቢሆንም በዚህ መልኩ ፈፅሞ ያለመገኘት አግባብ በሆነዉ የትራፊክ ደንብ መሰረት ከሚያስቀጣ በቀር በቸልተኝነት ከሚፈፀም ወንጀል ጋር የሚያገናኘዉ ነገር የለም፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ አሽከርካሪው አደጋ በደረሰበት እለት ተገቢን መንጃ ፈቃድ ይዞ ያለመገኘቱ ለአደጋዉ መንስኤ እንደሆነ ወስዶ ዉሳኔ መስጠት አግባብ ከህጉ መንፈስ የወጣ እና መሰረታዊ የህግ አረዳድ እና አተረጓጎም ስህተት የፈፀመበት ነው፡፡ ምንጭ፡-የሰ/መ/ቁ የሰ/መ/ቁ 191629 መስከረም 26/2013 ዓ.ም የተወሰነ /ያልታተመ/ በዚህ ውሳኔ ምን ያክል ይስማሙበታል?
Show all...
በውርስ ክርክር ተፈጻሚ ሊሆን የሚገባዉ ህግ አውራሽ በሞተበት ጊዜ በሥራ ላይ የነበረዉ ህግ ነዉ፤ ***************** የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሠበር ሠሚ ችሎት በሠበር መ/ቁ. 86089፣ 995873፣ 121822 እና 183645 “ለውርስ ክርክር ተፈጻሚነት ያለው ሟች በሞተበት እና ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ የነበረው ህግ ሳይሆን ክርክሩ በቀረበ ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት ሊሆን ይገባል” በማለት የሰጠውን ትርጉም በመለወጥ፤ “በውርስ ክርክር ወራሾቹ ሆነ ቀዳሚ ወራሾች እነማን ናቸው የሚለው ሊወሰን የሚገባው አውራሽ በሞተበት ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት ሊሆን ይገባል” በማለት በሠበር መ/ቁ. 191393 ሚያዚያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል። የዉሳኔዉን pdf ፋይል ሊንኩን በመጫን ማገኘት ይችላሉ፡፡https://t.me/khalidkebede
Show all...
🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል። ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ ስልክ- 0935439820 ኢሜይል- [email protected]

የሰ.መ.ቁ 239711 የሰ.መ.ቁ 23141.pdf7.23 KB
የጦር መሳሪያ አዋጁ ከመጽናቱ በፊት በነበሩ ሕጎችና አሰራሮች ያልተመዘገበ ወይም ፈቃድ ያልተሰጠው በሰው ሊያዝ የሚችል የጦር መሣሪያን መያዘ ወንጀል ነዉን? ************************ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥሮች 205727 እና 205827 “የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁ. 1177/2012 አንቀጽ 23(2) ከአዋጁ መሰረታዊ ዓላማ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ የድንጋጌው ዋናው ዓላማ ፈቃድ የሌላቸው ሰዎች ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ መሳሪያውን ይዘው ሲንቀሳቀሱ ሊያጋጥማቸው ከሚችለው የህጋዊነት ጥያቄ ለመጠበቅ እንጂ እስከ አንድ አመት ድረስ ያለማንም ጠያቂ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመፍቀድ አይደለም፡፡" በማለት የህዊነት መርህ እና አመክንዮ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጋጭ አስገዳጅ የህግ ትርጉም በመስጠቱ ምክንያት ሰዎች በህግ የተፈቀደላቸዉን መብት ሲጠቀሙ የወንጀል ድርጊት ፈፅመዋል በሚል የእስር፣ የገንዘብ መቀጮ እና የጦር መሳሪያ መዉረስ የቅጣት ዉሳኔ እንዲተላለፍባቸዉ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጅ ሰበር ሰሚ ችሎት ከላይ በ5 ዳኞች ተሰጥቶ የነበረ አስገዳጅ የህግ ትርጉም በመ/ቁ. 239711 እና 233141 ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በመለወጥ፤
“የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 አዋጁ ከጸናበት ከ30/4/2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አንድ አመት ይኸውም እስከ 30/04/2013 ዓ.ም ባለው የአንድ አመት ጊዜ ውስጥ አዋጁ ከመጽናቱ በፊት በነበሩ ሕጎችና አሰራሮች ያልተመዘገበ ወይም ፈቃድ ያልተሰጠው በሰው ሊያዝ የሚችል የጦር መሣሪያን የያዘ ወይም የተጠቀመ ሰው የአዋጁን አንቀጽ 4(2) እና 22(3) ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የወንጀል ተጠያቂነት የለበትም”
በሚል የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ የዉሳኔዉን pdf ፋይል ሊንኩን በመጫን ማገኘት ይችላሉ፡፡https://t.me/khalidkebede
Show all...
🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️

ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል። ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ ስልክ- 0935439820 ኢሜይል- [email protected]

255 የሚለው 25 ተብሎ ይነበብልኝ፡፡
Show all...
ተከራካሪ ወገኖች በፌደራል መንግስት ህግ የተመዘገቡ እና የተቋቋሙ ከሆነጉዳዩ የፌደራል ፍ/ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ነው:: ይሁን እንጅ ክሱ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት ሆኖ ንብረቱም የሚገኘው በከልል ከሆነ ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ የሚገኘው ፍ/ቤት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 255(1)(ሐ) መሰረት ጉዳዩን የማየት የግዛት ስልጠን አለው:: ሰበር መ/ቁ 218203, ያልታተመ::
Show all...
በሰባት ዳኞች የተለወጡ የሰበር ውሳኔዎች ≈≈≈ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 ስር እንደተደነገገው አምስት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠን ትርጉም በተለያዩ ምክንያቶች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት እንዲታይ እንደሚደረግ እና በዚህ መልኩ የሚሰጠው የህግ ትርጉም ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በማናቸውም ደረጃ ለሚገኝ የፌደራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት አስገዳጅ እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡ በዚህ መሰረት ባሳለፍነው በጀት አመት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት ውሳኔ የተሰጠባቸውን ጉዳዮች አጭር መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡ የውሳኔዎቹን ሙሉ ግልባጭ በፍርድ ቤቱ ዌብሳይት https://www.fsc.gov.et/ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ መልካም ንባብ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት
Show all...
የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ በሌላ ሰው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቤትን የጋራ ለማድረግ የተደረገ ስምምነት ከሌለ በስተቀር ለቤቱ መሰራት የገንዘብ ወይም የጉልበት አስተዋፅዖ ማድረግ ብቻውን የጋራ ባለሀብት የማያደርግ ነው ተብሎ ተወስኗል። https://t.me/ethiolawtips @ethiolawtips
Show all...
ለቤቱ_መሰራት_የገንዘብ_ወይም_የጉልበት_አስተዋፅዖ_ማድረግ_ብቻውን_የጋራ_ባለሀብት_የማያደርግ_ስለመሆኑ.pdf1.26 MB
ተከሳሽ የሆነ ወገን መልስ የማቅረብ መብት መታለፍ ውጤቱ ምንድን ነው? ተከሳሽ የሆነው ወገን በጽሀፍ መልስ የማቅረብ መብቱ ከታለፈ በክርክር ሂደት መሳተፍ ሲቀጥል ከሚያቀርበው የክርክር ወሰን ሆነ ከማስረጃ አቀራረብ ረገድ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ የፅሁፍ መልስ የማቅረብ መብት ሲታለፍ ቀጥተኛ ውጤቱ ከመልሱ ጋር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 223 እና 145 መሰረት የሚቀርቡ ማስረጃዎችን የማቅረብ መብትም አብሮ የሚታለፍ ይሆናል፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 223 ተከራካሪ የሰው ማስረጃ እና በዕጁ የሚገኝ የፅሁፍ ማስረጃን የሚያቀርብበት ሲሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 145 መሰረት ደግሞ በተከራካሪ ዕጅ የሌሉ ወይም ለማቅረብ ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቁ ማስረጃዎች በፍርድ ቤት እገዛ የሚቀርቡበት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ የፅሁፍ መልስ እንዲያቀርብ ካልተፈቀደለት በስተቀር በክሱ በሚሰማበት ሆነ በሙግት ጊዜ መቅረቡ የእነዚህን ማስረጃዎች ዝርዝር ፍርድ ቤቱ እንዲመዘግብለት ሆነ ማስረጃዎችን እንዲያቀርብ ዕድል የሚሰጠው አይደለም፡፡ የፅሁፍ መልስ የማቅረብ መብቱ የታለፈ ተከሳሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 137 መሰረት ማስረጃ ሊያቀርብ አይችልም፡፡ ሰለሆነም ተከራካሪ ወገኖች በመብታቸው ለመስራት ተገቢውን ትጋት ማድረግ ያለባቸው መሆኑ እንዳለ ሆኖ ፍርድ ቤቶች የተከሳሽን መልስ የማቅረብ መብት ከማለፋቸው በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሕጉ ኃላፊነት ጥሎባቸዋል፡፡ ምንጭ፡-የሰ/መ/ቁ. 188331 የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ/ም የተወሰነ /ያልታተመ/
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.