cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Ministry of Education Ethiopia

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel. For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Show more
Advertising posts
109 802
Subscribers
+3524 hours
+4287 days
+10 62230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢንኩንቬሽን ማዕከላት መጠናከር እንዳለባቸው ተገለጸ -------------------------------------- በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኢንኩንቬንሽን ማዕከላትን በማጠናከር ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናውን ያስጀመሩት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የኢንኩንቬንሽን ማዕከላትን ማጠናከር በተቋማቱ ያለውን የተዛባ ሚዛን ያስተካክላል ብለዋል። አሁን ባለው ግምገማ በተቋሞቻችን ያለው የኢንኩንቬንሽን ማዕከላት አሰራር ከዘመኑ ጋር ያልተራመደ በመሆኑ ስልጠና ማዘጋጀት ማሰፈለጉን ጠቁመው በቀጣይ በዚህ ዘርፍ ላይ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ ሃላፊ አቶ ተሾመ ዳንኤል በበኩላቸው ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዩንቨርሲት ኢንዱስትሪ ትስስር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና እንኩንቤሽን ማዕከላት ኃላፊዎች የሚሰጠው ስልጠና ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት እንደሚያሳይ ጠቁመው ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይህንን የሪፎርም ተልዕኮ በብቃት መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል። አቶ ተሾመ አያይዘውም ስልጠናው በፈጠራ ስነምህዳር፣ በስራ ፈጠራ ማበልጸጊያ ማዕከላት እና የምርምር ውጤቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ገበያ ለማስገባት በሚከናወኑ አስተዳደራዊ ስራዎች ላይ የሚስተዋለውን የግንዛቤ እጥረት መፍታትን ትኩረት ያደርገ መሆኑን ገልጸው ስልጠናውን በዘርፉ ልምድ ያካበቱ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ባለሙያች እውቀታቸውን ይጋሩበት መሆኑን ጠቁመዋል። በመጨረሻም ከየተቋማቱ የመጡ የስራ ሃላፊዎች ማዕከላቱ በሚጠናከሩበት ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በስልጠናው ብዙ ልምድ እንዳገኙ ጠቁመዋል።
Show all...
ማስታወቂያ በተዘጋጁ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ የቀረበ ጥሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሥራውን በተገቢው ሁኔታ ለማከናወን ይችል ዘንድ የተለያዩ የአሰራር ሥርዓቶችን የመዘርጋትና መመሪያዎችን የማዘጋጀት ተግባራትን ሲከውን መቆየቱ ይታወቃል። ከዚህ አንጻር፣ 1. የርቀት ትምህርት ፕሮግራም፣ 2. የማታ ትምህርት ፕሮግራም፣ እና 3. የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ መመሪያዎችን በአዲስ መልክ አዘጋጅቷል። በመሆኑም የተዘጋጁትን ረቂቅ መመሪያዎች አፅድቆ ሥራ ላይ ለማዋል በረቂቆቹ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በውይይት የማዳበር ሥራ ተሰርቷል። ነገር ግን ተጨማሪ ግብዓት በማሰባሰብ መመሪያዎቹን የበለጠ ማዳበር አስፈላጊ በመሆኑ ፕሮግራሞቹን በመተግበር ላይ ያላችሁ (የርቀት ትምህርት ፕሮግራም ተግባሪ ተቋማት፣ የማታ ትምህርት ፕሮግራም ተግባሪ ተቋማት እና የተፋጠነ ትምህርት ፕሮግራም ተግባሪ ተቋማት) አስተያየት ለመስጠት የተጋበዛችሁ ስለሆኑ መስከረም 14/ 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው መድረክ በመገኘት እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።
Show all...
ማስታወቂያ ረቂቅ መመሪያን በውይይት ለማዳበር አስተያየት እንዲሰጥ ስለመጠየቅ የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፍ ሁለንተናዊ እድገት እና ጥራትን ለማረጋገጥ ትክክለኛ እና ጥራት ያለዉ የትምህርት መረጃ የማይተካ ሚና ሰላለዉ በዘርፉ የትምህርት መረጃ አሰተዳደር ስርዓት ግልፅነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር ለመፍጠር የሚያስችል የትምህርት መረጃ አሰተዳደር ስርዓት ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል። የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ፀድቆ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት በቀጥታ ህብረተሰቡ በሚሳተፍበት መድረክ አስተያየት እና ግብአት እንዲሰበሰብ ማድረግ አስፈልጓል፡፡ በመሆኑም መሰከረም 08/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው የመስሪያቤታችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመገኘት ይፋዊ የህዝብ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ሰነዱን ለማዳበር የሚያስችል ግብአት ይሰጡን ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የአሜሪካ የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ቻንስለር በዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ የተመራ የልዑካን ቡድን ተቀብለው በጽ/ ቤታቸው አነጋገሩ፡፡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ቻንስለሩንና የልዑካን ቡድናቸውን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ስለ አገራችን ዘመናዊ ትምህርትና የከፍተኛ ትምህርት ታሪክና መስፋፋት ዙሪያ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡ የረትገር ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቴክኖሎጂና በሌሎችም የትብብር መስኮች በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መክረዋል፡፡ ዶክተር አንቶኒዮ ዲ. ቲሊስ በበኩላቸው የረትገር ዩኒቨርሲቲ-ካምደን ከማላዊ፣ ኬኒያ ፣ ናይጄሪያና ከሌሎችም የአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ ጠቅሰው ከትምህርት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በተለያዩ መስኮቸ በትብብርና በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
Show all...
ቀን፡ 29/12/2016 ዓ.ም ማስታወቂያ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን እንደ ፈተና ማዕከል ለመረጣችሁ የ ‘NGAT’ ተፈታኞች በሙሉ ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜ 01/ 2016 ዓ.ም ድረስ በመላው ሀገሪቱ ይሰጣል ተብሎ በእቅድ የተያዘው የ “NGAT’ ፈተና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በፈተና ጣቢያነት ለመረጣችሁ ተፈታኞች ብቻ የፈተናው ጊዜ የተለወጠ መሆኑን እያሳወቅን ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት የምናሳውቅ ሆኖ በሌሎች የፈተና ጣቢያዎች (ዩኒቨርሲቲዎች) ፈተናውን ለመውሰድ ያመለከታችሁ በሙሉ ፈተናው በተያዘው ዕቅድ መሰረት ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም ከ8:00 (ከስምንት ሰዓት) ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር
Show all...
ቀን፡ 29/12/2016 ዓ.ም ማስታወቂያ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን እንደ ፈተና ማዕከል ለመረጣችሁ የ ‘NGAT’ ተፈታኞች በሙሉ ከነሐሴ 30 እስከ ጳጉሜ 01/ 2016 ዓ.ም ድረስ በመላው ሀገሪቱ ይሰጣል ተብሎ በእቅድ የተያዘው የ “NGAT’ ፈተና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በፈተና ጣቢያነት ለመረጣችሁ ተፈታኞች ብቻ የፈተናው ጊዜ የተለወጠ መሆኑን እያሳወቅን ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት የምናሳውቅ ሆኖ በሌሎች የፈተና ጣቢያዎች (ዩኒቨርሲቲዎች) ፈተናውን ለመውሰድ ያመለከታችሁ በሙሉ ፈተናው በተያዘው ዕቅድ መሰረት የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር
Show all...
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማት ስፖርት ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ ====================== የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የመግባቢያ ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ስፖርት አእምሮአዊና አካላዊ ብቃት የተላበሱ ዜጎችን ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ብቃት ያላቸው ዜጎችን የማፍራት ተግባር የትምህርት ዘርፉ ሪፎርም አካል አድርጎ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በቀጣዩ የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤቶች ስፖርት ውድድርን ለማካሄድ እና መርሃ ግብሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በበኩላቸው በሁሉም ዘርፍ አሸናፊ አገር ለመፍጠር ብቁና ንቁ ዜጎች ማፍራት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው በማህበረሰብ አቀፍ እና በባህላዊ ስፖርቶች ላይ የትምህርት ማህበረሰቡን በማሳተፍ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ሁለቱ ተቋማት በዕለቱ የተፈረረሙት የመግባቢያ ሰነድ መሰረት በቀጣይ በየደረጃው ባሉ ቴክኒካል ባለሙያዎች በየጊዜው እየታቀደ እና እየዳበረ ለተሻለ ስኬት እንደሚውል ጠቁመዋል፡፡ የትብብር ስምምንቱ ዓላማ በሁለቱ ተቋማት መካከል ወጥ እና ተከታታይነት ያለው ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር የትምህርት ቤት ስፖርት ልማትን በማስፋፋት የስፖርት ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ሰፖርታዊ ልማትን ባህል ያደረገ በመማር ውጤቱ የተሻለ የሆነ ንቁና ሁለንተናዊ ሰብዕናው የተሟላ ተተኪ ትውልድ ለማፍራት ምቹ ሁኔታን መፍጠር የስምምነት ሰነዱ ሌለው ዓላማ መሆኑን ተመላክቷል፡፡ ===////====
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.