cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopian Institution of the Ombudsman

EThiopian Institution of the Ombudsman Public Channel

Show more
Advertising posts
267
Subscribers
+124 hours
+47 days
+1330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለክቡራን የፌስ ቡክ ተከታዮቻችን በሙሉ! ==== በቅድሚያ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሠላም አደረሳቻሁ እያለን ማክሰኞ ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም ማታ ጀምሮ ተቋማችን በማያዉቀዉ መንገድ   የተቋማችን Facebook page በመጥለፍ ከተቋሙ ዓላማና ተግባር ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸዉን ቪዲዮዎችን እየጫኑባቸዉ ይገኛሉ። በመሆኑም  "Ethiopian institution of the ombudsman/EIO የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም" ገጽ የሚለቀቀው ሁሉ የተቋሙ አለመሆኑን እንገልፃለን።
Show all...
የተቋማችን Facebook page ከእኛ ቁጥጥር ውጭ ስለሆነ "Ethiopian institution of the ombudsman/EIO የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም" ገጽ የሚለቀቀው ሁሉ የተቋሙ አለመሆኑን እናሳስባለን። https://www.facebook.com/profile.php?id=100063701050699
Show all...
Ethiopian Institution of the Ombudsman/EIO የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

Ethiopian Institution of the Ombudsman/EIO የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም. 9,045 likes · 145 talking about this. Article 55 of the F.D.R.E. constitution provides that the house of people’s representatives shall

Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው የሀገራችን ህዝቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም እንኳን ለ2017ዓ.ም አደረሳችሁ እያለ በአዲሱ አመት በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር መሰረት በማድረግ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ተደራሽነታችንን በማሳደግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በትጋት የምናገለግል መሆናችንን እንገልፃለን፡፡ በድጋሜ እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ
Show all...
It is said "Access to information is essential to bring about smooth and efficient development." ======== To bring about rapid and efficient development in the society, Access to information is essential said Ato Temesgen Kidane, Head of the Access to Information Law Implementation Desk in the Ethiopian Institution of the Ombudsman. The head of the desk said that the primary goal of freedom of information is to unite the government and the people to act in a way that is conducive to development. He said this at a discussion forum organized by the institute to gather professional opinions on a bill to amend the Access to Information Act with officials and experts from the judiciary, higher education institutions and civic associations. In this discussion platform, the strengths and weaknesses of the current Freedom of Information Act, as well as the problems encountered in the implementation process of the law, were raised and discussed. The provision that anyone can request, obtain and use information from any government body is considered as a strong point; the power given to the Ethiopian People's Ombudsman is incomplete, there is no mandatory system to ensure the right to access information, the restrictions imposed on freedom of information are interpreted in vague and ambiguous terms, where information is denied. It was mentioned in the discussion that the appeal process is very long or takes up to 100 days. On the other hand, the participants commented that it would be good if the issue of information quality is given attention and included in the decree. Finally, the draft law aims to correct specific issues and create a better and comprehensive freedom of information law, said Denek Shanko, the representative of the institution.
Show all...
It is said "Access to information is essential to bring about smooth and efficient development."
Show all...
“ፈጣንና ቀልጣፋ ልማት ለማምጣት የመረጃ ነፃነት ወሳኝ ነዉ"ተባለ ************* በማህበረሰቡ ዘንድ ፈጣንና ቀልጣፋ ልማት ለማምጣት የመረጃ ነፃነት ወሳኝ ነዉ ሲሉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የመረጃ ነፃነት ህግ ማስተግበር ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተመስገን ኪዳኔ ገለጹ። የመረጃ ነፃነት ቀዳሚ ዓለማ መንግስትና ሕዝብን አንድ በማድረግ ለልማት በተናበበ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ መሆኑን ዴስክ ኃላፊዉ አያይዘዉ ተናግረዋል፡፡ ይህን የተናገሩት ተቋሙ የመረጃ ነፃነት አዋጅን ለማሻሻል በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሙያዊ አስተያየቶችን ለማሰባሰብ ከፍትህ አካላት፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከሲቪክ ማህበራት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ለመወያየት በተዘጋጀ የዉይይት መድረክ ላይ ነዉ፡፡ በዚህ የዉይይት መድረክ ላይ አሁን በስራ ላይ ያለዉ የመረጃ ነፃነት አዋጅ ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶች እንዲሁም ህጉን በማስተግበር ሂደት ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ተዳሰዉ ለዉይይት መነሻነት ቀረበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል። በመጨረሻም ረቂቅ አዋጁ በክፍተት የተለዩ ጉዳዮችን በማረም የተሻለና ምልዕዑ የሆነ የመረጃ ነፃነት አዋጅ እንዲኖር ታስቦ መሆኑን በተቋሙ ተወካይ ዋና ዕንባ ጠባቂ የሆኑት አቶ ደነቀ ሻንቆ ተናግረዋል።
Show all...
A Forum is being held by the Ethiopian Institution of Ombudsman with the judicial bodies, higher education institutions and civil society officials and experts since August 30, 2016 E.C to collect inputs on the currently implemented Access to Information. The main purpose of the forum is to discuss on decree. የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም ከፍትህ አካላት፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከሲቪክ ማህበራት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የረቂቅ መረጃ ነፃነት አዋጅ ላይ ግብአቶችን ለማሰባሰብ የውይይት መድረክ አካሔደ፡፡ "We are striving for Good Governance!" ለመልካም አስተዳደር መስፈን እንተጋለን. ፌስቡክ: https://www.facebook.com/profile.php?id=100063701050699 ቴሌግራም፡ https://t.me/EthiopianOmbudsman ቲዉተር፡ https://twitter.com/Ethiopianinsti2 ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/@EIO23 https://www.linkedin.com/in/ombudsman-ethiopia-4378bb2ba/ ቲክቶክ፤ ombudsmanethiopia2 E-mail፡ [email protected] ስልክ: 9503 ነፃ የጥሪ ማዕከል
Show all...
የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ የማይፈጽሙ፣ ለህግ የበላይነት የማይገዙ፣ ማን ይነካኛል በሚሉ አመራሮች ምክንያት ስራ መስራት አልቻልኩም አለ፡፡ *********************** በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን የሚመሩ አመራሮች «ለምን እነካለው» በሚል የፍርድ ቤቶችን ትዕዛዝ የማይቀበሉ፣ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሰብ የማይፈጽሙ፤ የስራ ኃላፊዎች እንቅፋት እንደሆኑበት ጽህፈት ቤቱ አስረድቷል፡፡ የእነዚህን አመራሮች መስሪያ ቤት በቅርቡ ይፋ እንደሚደርግ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጋሻነው ደሴ ነግረውናል፡፡ «የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣውን ህግ አልፈጽም ለህግ የበላይነትም አልገዛም ምን ይነካኛል» ለሚሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዩ ሪፖርት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት እና ለክልሉ ምክር ቤት እያሰናዱ እንዳሉም የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ጋሻነው ደሴ ነግረውናል፡፡ የመንግስት ሥርዓት ተጠቃሚ የሚሆነው እራሱ ህግን ሲያከብር ነው ያሉት ኃላፊው እሱ ህግን ካላከበረ ሌላውን ማስከበር አይችልም ሲሉ ነግረውናል፡፡ «እኛ የዴሞክራሲ ተቋማት ያለን ጉልበት ህግ ነው ይሁንና ችግሮችን መርምረን መስረጃዎችን አሰናድተን እንዲፈፀሙ ህግ ለሚያስገድዳቸው የስራ ኃላፊዎች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጣለው ግዴታ አለ አንዳንዶቹ በከፋ መንገድ የማያስፈጽሙ የፍርድ ቤትንም ትዕዛዝ የማይፈጽሙ አሉ ይህም የህዝብ ተወካይዎችን ምክር ቤት ስልጣን መናቅ ነው» ብለዋል ኃላፊው፡፡ ‘’አትንኩኝ ባይነቱ በጣም ሰፊ ነው’’ ያሉት አቶ ጋሻነው ‘’አንዳንድ የስራ ኃላፊዎች እኛ ከህዝብ የተቀበልነውን እንዲያስፈጽሙ ስንጣይቃቸው ፍቃደኛ አይሆኑም ይሁንና በክልል ከፍተኛ የአመራር ለውጥ አለ ያኔ እነሱ ከስልጣን ሲወርዱ ያለ ምክንያት ከደረጃ ዝቅ ተደርጊያለሁ ገላግሉኝ’’ ብለው ፍትህ ፍለጋ ይመጣሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ... https://tinyurl.com/3hjukp35 SHEGER FM 102.1 RADIO
Show all...
የእምባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ የማይፈጽሙ፣ ማን ይነካኛል በሚሉ አመራሮች ምክንያት ስራ መስራት አልቻልኩም አለ፡፡

ነሐሴ 22፣2016 የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ የማይፈጽሙ፣ ለህግ የበላይነት የማይገዙ፣ ማን ይነካኛል በሚሉ አመራሮች ምክንያት ስራ መስራት አልቻልኩም አለ፡፡ በአማራ ክልል የሚገኙ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን የሚመሩ አመራሮች «ለምን እነካለው» በሚል የፍርድ ቤቶችን ትዕዛዝ የማይቀበሉ፣ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሰብ የማይፈጽሙ፤ የስራ ኃላፊዎች እንቅፋት እንደሆኑበት ጽህፈት ቤቱ አስረድቷል፡፡ የእነዚህን አመራሮች መስሪያ ቤት በቅርቡ ይፋ እንደሚደርግ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጋሻነው ደሴ ነግረውናል፡፡ «የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያወጣውን ህግ አልፈጽም ለህግ የበላይነትም አልገዛም ምን ይነካኛል» ለሚሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዩ ሪፖርት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት እና ለክልሉ ምክር ቤት እያሰናዱ እንዳሉም የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ጋሻነው ደሴ ነግረውናል፡፡

2
መረጃ የማይሰጡ ሀላፊዎች በሚዲያ የሚጋለጡበት/Naming and Shaming አሰራር በመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ እንዲካተት አስተያየት ተሰጠ፡፡ ************************* የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የመረጃ ነጻነት አዋጅ ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ ሰነድ ዙሪያ ባዘጋጀው የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ መረጃ የማይሰጡ የተቋማት ሀላፊዎች በሚዲያ የሚጋለጡበት አሰራር የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ ውስጥ እንዲካተት ተጠየቀ፡፡ የተቋሙ ተወካይ ዋና ዕንባ ጠባቂ አቶ ደነቀ ሻንቆ እንደተናገሩት ለሀገራት ስጋት እየሆነ ያለው ማህበራዊ ሚዲያ ከዋናው ሜንስትሪሚንግ ሚዲያ እየበለጠ እና ሰፊ ተደራሽነት እያገኘ ስለሆነ በሶሻል ሚዲያ የሚሰራጩ አሳሳችና የተዛቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል፤ መንግስት እና ህግ አውጭው ተገንዝቦ የመረጃ ነፃነት አዋጁን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ አዋጁን ለማስፈጸም የፖለቲካ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ደነቀ ም/ቤቱ ይህንን የተሻሻለ አዋጅ በማጽደቅ በሁሉም አስፈፃሚ ተቋማት ላይ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ የረቂቅ አዋጁን ጽሁፍ ያቀረቡት የመረጃ ነጻነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ማናየ አለሙ በበኩላቸው ለህዝብ ጥቅም ሲባል መረጃ የማይሰጡ ሃላፊዎች አስተዳደራዊ ቅጣት የሚጣልባቸው ሲሆን መግለጫ የሚሰጡ አካላትም ሁሉንም የግል እና የመንግስት ሚዲያ በእኩል በማየት ማስተናገድ አለባቸው፤ ለመረጃ ጠያቂዎች በ21 ቀናት ውስጥ ተቋማት መረጃውን ለጠያቂው እንዲሰጡ እና አጣዳፊ መረጃዎችን በ5 ቀን እንዲሰጡ ለማድረግ አስገዳጅነት በረቂቅ አዋጅ ላይ ተካቷል ብለዋል፡፡
Show all...
በጎፋ ዞን ከመሬት መንሸራተት ለተረፉ ከ620 በላይ አባወራዎች የመኖሪያ መንደር እንዲገነባ ተጠየቀ https://www.ethiopianreporter.com/132747/ ከአንድ ወር በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ ቀንቾ ሻጫ ጎዘዲ ጎፋ ዞን ጋዜ ጎፋ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከቦታው በሥጋት የተነሱ ከ620 በላይ አባወራዎች፣ እንደ አዲስ ይመሠረታል ለተባለው የመኖሪያ መንደር ግንባታ በቂ ገንዘብ እንዲመደብ፣ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ጥያቄ አቀረበ፡፡ ተቋሙ በጎፋ ዞን የመሬት መንሸራት አደጋው ከደረሰ በኋላ፣ አደራጅቶ የላከው የባለሙያዎች ቡድን ክስተቱን አጣርቶ መመለሱን አስታውቋል፡፡ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ተወካይ አቶ ደነቀ ሻንቆ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በመሬት መንሸራተት ምክንያት በመጠለያ ለሚገኙ ዜጎች የሚደረገውን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትና የመልሶ ማቋቋም ሥራ ያለበትን ሁኔታ ቡድኑ ተመልክቶ ተመልሷል፡፡ ቡድኑ በምልከታው ምንም እንኳ አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚገኘው ሕዝብ የኖረበትን ቀዬ ለቆ ላለመሄድ እምቢተኛ የነበረ ቢሆንም፣ በመንግሥት በኩል በበቂ ሁኔታ ሕዝቡን አሳምኖ ከአካባቢው በማስነሳት የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ መከናወን ነበረበት ብለዋል፡፡ በደረሰው አደጋ 249 ሰዎች መሞታቸውንና የ243 ሟቾች አስከሬን ሲገኝ የስድስት ሰዎች አስከሬን አለመገኘቱን አቶ ደነቀ በነበራቸው ጉብኝት መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም 50 ሰዎች በሕክምና ክትትል ላይ እንደነበሩ አክለው ገልጸዋል፡፡ ‹‹የመሬት መንሸራተት አደጋ በዚሁ አካባቢ ከዚህ ቀደም ተከስቶ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን በተፈጠረው ልክ የገዘፈ አደጋ እንዳላስከተለ ተረድተናል፤›› ያሉት አቶ ደነቀ፣ መንግሥት የመሬት አጠቃቀም ሥርዓቱን መቀየር አለበት ብለዋል፡፡ በቀጣይ በጂኦሎጂካል ጥናት በተደገፈ መረጃ የመኖሪያና የእርሻ ቦታን በመለየት ተገቢውን ሥራ ማከናወን ያስፈልጋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡ በርካታ ኮሚቴዎች ተዋቅረው የመልሶ ማቋቋም ሥራውን ለማገዝ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም፣ እስካሁን በጥሬ ገንዘብ የተሰበሰበው 109 ሚሊዮን ብር በቀጣይ ይገነባል ለተባለውና 11,000 ዜጎችን ይይዛል ተብሎ ለሚጠበቀው አዲስ መንደር ግንባታ እንደማይበቃ ተናግረዋል፡፡ ለተጎጂዎች በዓይነት የቀረበው ድጋፍ 220 ሚሊዮን ብር መድረሱን አክለው ተናግረዋል፡፡ በደረሰው የመሬት መንሸራተት በርካታ አቅመ ደካሞች ልጆቻቸው እንደሞቱባቸው፣ የሞተባቸውን ቤተሰብ አስከሬን ያላገኙ ሰዎች እንዳሉ፣ ከፍተኛ የሞራል ስብራት ጥሎ ያለፈ ክስተት በመሆኑ ለእነዚህ ወገኖች ጠንካራ የሆነ የሥነ ልቦና ሥራ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ከአደጋው ሥፍራ ወጣ ብሎ አዲስ መገንባት አለበት ተብሎ የቀረበው ፕላን ከቦታው በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ መሆኑን የተናገሩት አቶ ደነቀ፣ የተሰበሰበው ገንዘብ አነስተኛ በመሆኑ፣ የፌዴራል መንግሥትም ሆነ ሌሎች ክልሎችና የግሉ ዘርፍ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከ2,500 በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ገልጸው፣ ተማሪዎቹ ወደ ትምህርት ገበታ የሚመለሱበት ዕድል እንዲመቻችና በቀጣይ የትምህርት፣ የጤናና የሌሎች መሠረተ ልማት ግንባታዎችን ለማካሄድ የሚረዳ ሀብት ማሰባሰቢያ እንዲመቻች አሳስበዋል፡፡
Show all...
በጎፋ ዞን ከመሬት መንሸራተት ለተረፉ ከ620 በላይ አባወራዎች የመኖሪያ መንደር እንዲገነባ ተጠየቀ - ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best And Reliable News Source In Ethiopia

ከአንድ ወር በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ ቀንቾ ሻጫ ጎዘዲ ጎፋ ዞን ጋዜ ጎፋ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከቦታው በሥጋት የተነሱ ከ620 በላይ አባወራዎች፣ እንደ አዲስ ይመሠረታል ለተባለው የመኖሪያ መንደር ግንባታ በቂ ገንዘብ እንዲመደብ፣ የሕዝብ

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.