cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopian Coffee and Tea Authority

Ethiopian Coffee and Tea Authority

Show more
Advertising posts
3 782
Subscribers
+324 hours
+107 days
+9130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
Ethiopia fetches record $196 m from coffee export in August

Ethiopia has earned the highest $196 million from coffee export in August 2024, the Ethiopian Coffee and Tea Authority (ECTA) announced.

በኦሮሚያ ክልል የሻይ ቅጠል ተክል ሽፋንን ከ5 ዓመታት በኋላ 500 ሺህ ሄክታር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ነው (አዲስ አበባ፣ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በግብርናው ዘርፍ ለማሳካት እየሠራባቸው ካሉ ግቦች አንዱ የኤክስፖርት ምርቶችን መጠን ማሳደግ፣ ብዝሃነት መጨመር እና ጥራት ማሻሻል ዋነኞቹ ናቸው። ይህን ግብ በማሳካት ረገድ የሻይ ቅጠል ልማት ኢኒሼቲቭ ድርሻ ከፍተኛ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያጋሩት መረጃ ያመላክታል። በመረጃው መሰረት፥ በክልሉ በአንድ ወረዳ ውስጥ በአንድ የግል ድርጅት ብቻ ተወስኖ የነበረውን የሻይ ቅጠል ልማት፣ በ2013 ዓ.ም ወደ ስራ በገባው "የአሌይ አዋጅ" በመቀየር፣ በአሁኑ ጊዜ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ አራት ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ ማስፋፋት ተችሏል። መረጃውን ያገኘነው ከግብርና ሚ/ር ቴሌግራም ገፅ ነው::
Show all...
Ministry of Agriculture - Ethiopia

በኦሮሚያ ክልል የሻይ ቅጠል ተክል ሽፋንን ከ5 ዓመታት በኋላ 500 ሺህ ሄክታር ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ነው (አዲስ አበባ፣ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በግብርናው ዘርፍ ለማሳካት እየሠራባቸው ካሉ ግቦች አንዱ የኤክስፖርት ምርቶችን መጠን ማሳደግ፣ ብዝሃነት...

ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በሻይ ልማት ዘርፍ በትብብር መስራት ትፈልጋለች - አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ (አዲስ አበባ፣ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር) ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር በሻይ ልማት ዘርፍ በትብብር መስራት እንደትምትሻ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ገለጹ። በኢትዮጵያ በሻይ ኢንዱስትሪ ከተሰማሩ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት የተወጣጣ የልዑካን ቡድን በኬንያ የሻይ ምርትና ኢንዱስትሪ ተሞክሮ መቅሰምን አላማ ያደረገ ጉብኝት አድርገዋል። ልዑካን ቡድኑ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ አባላትን ያቀፈ መሆኑም ተገልጿል። ቡድኑ ከኬንያ የሻይ ልማት ኤጀንሲ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል። በኬንያ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮችና የሻይ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከእርሻ እስከ ሽያጭ ባለው ሂደት ያላቸውን ትስስር አስመልክቶ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። ልዑካን ቡድኑ የሻይ ቅጠል እርሻ፣ ማቀነባበሪያ ፋብሪካና የማምረቻ ማሽኖችን ጎብኝቷል። ጉብኝቱ ኢትዮጵያና ኬንያ በሻይ ልማት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር እንዲሁም አገራቱ ያላቸውን ጠንካራ ትብብር ይበልጥ እንደሚያጎለብት ተገልጿል። በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ የኬንያ የሻይ ልማት ኤጀንሲ በሻይ ምርትና ኢንቨስትመንት ያለውን ተሞክሮ በማጋራቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ኢትዮጵያና ኬንያ የሻይ ልማትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ልምድ በመለዋወጥ የዜጎቻቸውን ኑሮ ማሻሻል እንደሚችሉ መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
Show all...
በቡና ኤክስፖርት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ተገኘ!! በነሀሴ ወር የተገኘው ገቢ እስከዛሬ ከነበሩ ወራቶች ሪከርድን የሰበረ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ መስከረም 02/2017 በዘንድሮው በጀት ዓመት ነሀሴ ወር ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ ካቀረበችው 42ሺህ 322 ቶን ቡና 196 ሚሊየን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ የተገኘው ገቢ እስከዛሬ ከነበሩ ወራቶች ሪከርድን የሰበረም ሆኖ ተመዝግቧል፡፡  ይህ ውጤት ከታቀደው አንጻር በመጠን 165% እንዲሁም በገቢ የ143% ጭማሪ መሆኑን ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ገልጸዋል፡፡ የሀምሌ እና ነሀሴ ወራት የሁለት ወራት አፈጻጸም በድምሩ ሲታይ በመጠን 82ሺህ 853 ቶን ቡና ተልኮ 377 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን በባለፈው ዓመት ሁለት ወራት ከነበረው አፈጻጸም ጋር ሲታይ ደግሞ በመጠን 32ሺህ 925 ቶን (66%) እንዲሁም በገቢ 110 ሚሊየን (41%) ጭማሪ የታየበት መሆኑን ክቡር ዶ/ር አዱኛ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ዘርፍ ተዋናዮች በሙሉ እንኳን ለ2017 አዲስ አመት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ። *********** በዓሉ እና መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ! መልካም በዓል!!! አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳ/ር
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.