cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢትዮ - ኮን ሬድዮ ፕሮግራም

በግንባታው ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሳምንታዊ የባለሙያዎች ፕሮግራም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአሀዱ ሬድዮ 94.3 ትብብር ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2፡30-3፡30 ሰዓት የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው።

Show more
Advertising posts
3 510
Subscribers
No data24 hours
-27 days
+2330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በ57 ሚሊየን ዶላር እየታደሰ የሚገኘው የአፍሪካ አዳራሽ ሕንፃ በጥቅምት ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተባለ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው የአፍሪካ አዳራሽ ሕንፃ እድሳት ስራ ተጠናቆ በጥቅምት ወር አጋማሽ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ። በኮሚሽኑ የአፍሪካ አዳራሽ አስተዳደር ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አንቶንዮ ሕንፃውን ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ባስጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት፥ የእድሳት ስራው ሕንጻው ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ዘመኑን የዋጀ ገጽታ እንዲላበስ አስችሏል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽኑን በአዲስ አበባ የተመሰረተው በፈረንጆቹ 1961 ሲሆን፥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የድርጅቱ ሕንፃ 62 ዓመታትን አስቆጥሯል። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የቻርተር ፊርማን ጨምሮ በርካታ አፍሪካዊ ኩነቶች የተካሄዱበት ታሪካዊው ሕንፃ፥ ጥንታዊነቱን በጠበቀ መልኩ እድሳት ተደርጎለት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። ተመድ በተለያዩ ምክንያቶች ሕንፃውን ለማደስ እንደተነሳ የተገለፀ ሲሆን፥ በዋናነት ሕንፃው ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ያሉት ሆኖ በቀጣይ ዓመታት አገልግሎት መስጠት እንዲችል ለማድረግ ያለመ ነው። በሕንፃው ውስጥ የነበሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ወደ ተለዋጭ ቦታ የማዘዋወር ስራ ከተካሄደ በኋላ በሁለት ምዕራፎች የተከናወነው የሕንፃው የእድሳት ስራ በተለያዩ ካምፓኒዎች የተከናወነ ሲሆን፥ ዋናውን የእድሳት ስራ "አልክ" የተሰኘ የዱባይ ካምፓኒ ሰርቶታል። 57 ሚሊየን ዶላር የተመደበለት የሕንፃው እድሳት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተሟሉለት ሲሆን፥ ከድርጅቱ ጋር የተያያዙ ታሪካዊ ክዋኔዎችና ቅርሶች የሚጎበኙበት የኤግዚቢሽን ማዕከል እንደተሰራለትም ተገልጿል። የሎሬት አፈወርቅ ተክሌ የስዕል ስራን ጨምሮ በርካታ ጥበባዊ ቅርሶች ያሉበት ሕንፃው በጥቅምት ወር አጋማሽ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናልም ተብሏል ። (ኤፍ ቢ ሲ)
Show all...
👏 1
🏗 የግንባታ ውል ሰነድ በግልጽ ማስቀመጥ ያለበት ነጥቦች:- የፕሮጀክቱን ዲዛይን እና ዝርዝሮች: ▶️የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላትን ድርሻ፣ መብትና ግዴታ፣ ▶️የሚጠበቀውን የግንባታ ጥራት የሚገልጹ ትንታኔዎች፣ ▶️የፕሮጀክቱን ተጠባቂ የጊዜ ሰሌዳዎች፣ ▶️የፕሮጀክቱን ዋጋ እና አከፋፈል ሁኔታዎች፣ ▶️የደህንነት እና የጤና አጠባበቅ፣ መመሪያዎች፣ ▶️ፕሮጀክቱን የሚመለከቱ የሕግ ማእቀፎች ▶️የፕሮጀክቱ ባለድርሻ አካላትን ፊርማ እና ማኅተም ▶️ፕሮጀክቱ የሚፈልገውን የሰው ኃይል ብቃትና ብዛት ▶️ፕሮጀክቱ የሚፈልገው ማሺነሪ አይነትና ብዛት ▶️የእያንዳንዱን የሥራ አይነት ዝርዝርና የግንባታ ስነዘዴ ▶️የፕሮጀክቱን ባለድርሻ አካላት ዝርዝር መረጃ አንድ የግንባታ ውል ሰነድ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ጭብጥ ጉዳዮች በግልጽ እና በዝርዝር ማስቀመጥ ይኖርበታል። የተወሳሰበ፣ ያልተብራራ እና እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሀሳብ ቢኖርበት ግን በሚኖረው የፍርድ ቤት ክርክር ባለድርሻ አካላትን በተናጠል አልያም በጋራ ኪሳራ ላይ ሊጥል ይችላል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ፕሮጀክቱን በጤናማ ግንኝነት ለመፈጸም እክል ሊፈጥር ስለሚችል ለጥራት ችግር እና ለጊዜ ብክነት እንዲጋለጥ ያደርገዋል። 
Show all...
👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
👉 የዛሬ ምሽት መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ሳምንታዊ ፕሮግራም 🚧የሬድዮ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመንቀስ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የተለያዩ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን በመጋበዝ ዘርፉ ላይ ያላቸውን የሙያ ክህሎታቸውንና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ነው፡፡ 📷በዛሬ ፕሮግራማችን፡- 👷የእንግዳ ሰዓት - የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር የቦርድ አመራሮች ጋር ቆይታ እናደርጋለን፡፡ እንግዶቻችን በምናደርገው ቆይታ....... - የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር በ2016 ዓ.ም ምን ምን ስራዎችን አከናወነ? በ2016 የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው እንዴት አለፈ? እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎችን እያነሳን ቆይታ የምናደርግ ይሆናል፡፡  ✍️📞☎️የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡ 🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችንን ትከታተሉ ዘንድ ከወዲሁ በአክብሮት እጋብዛለሁ፡፡                                              መልካም ምሽት!
Show all...
2👍 1
🏗🏚የዓለማችን ድንቅ እስላማዊ የ ኮንስትራክሽን ስትራክቸሮች እንሆ ⏺1. መስጂድ አል-ሀራም፡- መካ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ መስጂድ አል-ሀራም የአለማችን ትልቁ መስጂድ ሲሆን በእስልምና እጅግ የተቀደሰ ቦታ የሆነውን ካባንን ይከብባል።  መስጂዱ በሀጅ ወቅት እስከ 4 ሚሊዮን ሰጋጆችን ማስተናገድ ይችላል። ⏺2. መስጂድ አል-ነበዊ፡- በመዲና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ መስጂድ አል-ነበዊ በእስልምና ሁለተኛው ቅዱስ መስጂድ ነው።  የነብዩ መሐመድ መቃብር የሚገኝበት ሲሆን በግሩም አረንጓዴ ጉልላት እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የስነ-ህንፃ ጥበብ ይታወቃል። ⏺3. ቡርጅ ካሊፋ፡ 828 ሜትር ላይ የቆመው ቡርጅ ካሊፋ በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ በአለማችን ረጅሙ ህንፃ ነው። ኢስላማዊ እና ዘመናዊ ኪነ-ህንፃዎች ቅልቅል ያለው እና ተወዳጅ የቱሪስት መስህብ ነው። ⏺4. ሱልጣን አህመድ መስጂድ፡- በተለምዶ ሰማያዊ መስጂድ በመባል የሚታወቀው በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው ሱልጣን አህመድ መስጂድ የውስጥ ግድግዳውን እና ስድስቱን ሚናራዎችን በሚያጌጡ ሰማያዊ ሰቆች ይታወቃል። ⏺5. ሀሰን II መስጂድ፡ በሞሮኮ ካዛብላንካ ውስጥ የሚገኝ፣ ሀሰን 2 መስጂድ በአለም ላይ ካሉት ትልቁ መስጊዶች አንዱ ነው እና አስደናቂ የእብነበረድ ውስጠኛ ክፍል፣ ውስብስብ የጣር ስራ እና አስደናቂ የባህር ዳርቻ አቀማመጥ አለው።  ⏺6. አልሀምብራ፡ በግራናዳ፣ ስፔን ውስጥ የምትገኝ፣ አልሀምብራ መጎብኘት ያለበት የእስልምና አርክቴክቸር ድንቅ ነው። ይህ ቤተ መንግስት እና ምሽግ ውስብስብ የስቱኮ ማስዋቢያዎች፣ የፈረስ ጫማ ቅስቶች እና የተረጋጋ የአትክልት ስፍራዎችን ያሳያል። ⏺7. የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጊድ፡ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አቡ ዳቢ የሚገኘው የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጂድ የዘመናዊ ኢስላማዊ ኪነ-ህንፃ ድንቅ ስራ ነው። ነጭ የእብነበረድ ጉልላቶች፣ ውስብስብ ቅርጻ ቅርጾች እና አስደናቂ የአበባ ንድፎችን ይዟል። ⏺8. ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ፡ በ8ኛው ክፍለ ዘመን በኮርዶባ፣ ስፔን ውስጥ የተገነባው ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ የሞሪሽ፣ የጎቲክ እና የህዳሴ ስነ-ህንፃ ቅጦች ድብልቅልቅ የሚያሳይ የባህል ሀብት ነው።  ውስጣዊ ክፍሎቹ ከ 850 በላይ አምዶች እና ውስብስብ ቢሞች ኣሉት። (ETCONp)
Show all...
2👍 1🕊 1
👉የዓለማችን ድንቅ እስላማዊ የ ኮንስትራክሽን ስትራክቸሮች እንሆ 🚧1. መስጂድ አል-ሀራም፡- መካ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ መስጂድ አል-ሀራም የአለማችን ትልቁ መስጂድ ሲሆን በእስልምና እጅግ የተቀደሰ ቦታ የሆነውን ካባንን ይከብባል።  መስጂዱ በሀጅ ወቅት እስከ 4 ሚሊዮን ሰጋጆችን ማስተናገድ ይችላል። 🚧2. መስጂድ አል-ነበዊ፡- በመዲና፣ ሳውዲ አረቢያ፣ መስጂድ አል-ነበዊ በእስልምና ሁለተኛው ቅዱስ መስጂድ ነው።  etconp የነብዩ መሐመድ መቃብር የሚገኝበት ሲሆን በግሩም አረንጓዴ ጉልላት እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የስነ-ህንፃ ጥበብ ይታወቃል። 🚧3. ቡርጅ ካሊፋ፡ 828 ሜትር ላይ የቆመው ቡርጅ ካሊፋ በዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ በአለማችን ረጅሙ ህንፃ ነው። ኢስላማዊ እና ዘመናዊ ኪነ-ህንፃዎች ቅልቅል ያለው እና ተወዳጅ የቱሪስት መስህብ ነው።  etconp 4. ሱልጣን አህመድ መስጂድ፡- በተለምዶ ሰማያዊ መስጂድ በመባል የሚታወቀው በቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘው ሱልጣን አህመድ መስጂድ የውስጥ ግድግዳውን እና ስድስቱን ሚናራዎችን በሚያጌጡ ሰማያዊ ሰቆች ይታወቃል።  etconp የኦቶማን አርክቴክቸር ድንቅ ስራ ነው። 🚧5. ሀሰን II መስጂድ፡ በሞሮኮ ካዛብላንካ ውስጥ የሚገኝ፣ ሀሰን 2 መስጂድ በአለም ላይ ካሉት ትልቁ መስጊዶች አንዱ ነው እና አስደናቂ የእብነበረድ ውስጠኛ ክፍል፣ ውስብስብ የጣር ስራ እና አስደናቂ የባህር ዳርቻ አቀማመጥ አለው።  etconp 🚧6. አልሀምብራ፡ በግራናዳ፣ ስፔን ውስጥ የምትገኝ፣ አልሀምብራ መጎብኘት ያለበት የእስልምና አርክቴክቸር ድንቅ ነው። etconp ይህ ቤተ መንግስት እና ምሽግ ውስብስብ የስቱኮ ማስዋቢያዎች፣ የፈረስ ጫማ ቅስቶች እና የተረጋጋ የአትክልት ስፍራዎችን ያሳያል። 🚧7. የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጊድ፡ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አቡ ዳቢ የሚገኘው የሼክ ዛይድ ታላቁ መስጂድ የዘመናዊ ኢስላማዊ ኪነ-ህንፃ ድንቅ ስራ ነው።  etconp ነጭ የእብነበረድ ጉልላቶች፣ ውስብስብ ቅርጻ ቅርጾች እና አስደናቂ የአበባ ንድፎችን ይዟል። 🚧8. ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ፡ በ8ኛው ክፍለ ዘመን በኮርዶባ፣ ስፔን ውስጥ የተገነባው ታላቁ የኮርዶባ መስጊድ የሞሪሽ፣ የጎቲክ እና የህዳሴ ስነ-ህንፃ ቅጦች ድብልቅልቅ የሚያሳይ የባህል ሀብት ነው።  ውስጣዊ ክፍሎቹ ከ 850 በላይ አምዶች እና ውስብስብ ቢሞች ኣሉት። ❤️መልካም ዒድ😇 (@etconp)
Show all...
Ethio Con Work

📌ETCONp WORK የኮንስትራክሽን ስራ 📍 የምንሰጣቸው አገልግሎቶች 👉ሰራተኛ ማቅረብ ከባለ ሙያ እስከ መሀንዲስ ድረስ 👉ማቴሪያል ማቅረብ 👉በግልም ሆነ በመንግሥት የሚወጡ ጨረታዎች እና የ ስራ ማስታወቅያዎች መለጠፍ 👉የማሽን ኪራይ እና አቅርቦት ✌ ምን ይፈልጋሉ ??? 💌 @ETCONpBOT ወይም +251925446661 ያናግሩን

የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት የላቀ ብቃት ያካበቱ ባለሙያዎችን ለማፍራት ማስቻሉ ተገለጸ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት በሲቪልም ሆነ በሃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች የላቀ ብቃት ያካበቱ ባለሙያዎችን ማፍራት መቻሉ ተገለጸ። የግድቡ ግንባታ ፕሮጀክት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኤፍሬም ወልደኪዳን (ኢ/ር)፤ ለፕሮጀክቱ ስኬት ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ግንባታው የኢትዮጵያውያን ሚና የላቀ መሆኑን አስታውሰዋል። የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጀመር በአንድ ጊዜ እስከ 15 ሺህ ዜጎች በግንባታው ሂደት ላይ በተለያዩ ሙያዎች ይሳተፉ የነበሩ ባለሙያዎች ሌት ከቀን በመትጋት ለግድቡ እውን መሆን ዘላለማዊ አሻራቸውን በማሳረፍ የሚያኮራ ተግባር ፈፅመዋል ብለዋል። በግንባታው የረጅም ዓመት ልምድ በቀን ሰራተኝነት የጀመሩ በርካታ ወጣቶች አሁን ላይ ከፎርማን እስከ ሱፐርቫይዘርነት መድረሳቸውን አብራርተዋል። በዚህም በሲቪልም ሆነ በሃይድሮ ሜካኒካል ሥራዎች የላቀ ብቃት ያካበቱ በርካታ ባለሙያዎችን ማፍራት ስለመቻሉ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው። ግድቡ 13 ተርባይኖች እንዳሉት ገልጸው፤ የጀነሬተር አካል እስከ 12 ሜትር ዲያሜትርና ከ460 ቶን በላይ ክብደት ስላለው በትራንስፖርት አጓጉዞ ለማድረስ ፈታኝ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ ነገር ግን በፕሮጀክቱ ግንባታ ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አቅማቸውን በማጎልበት ዛሬ ላይ ግብዓቶችን በስፍራው እንዲገጣጠሙ ማድረግ የሚችሉበት አቅም ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ ኢትዮጵያ ለምትገነባቸው የሀይድሮ ፓወር ፕሮጀክቶች የሙያ ብቃትና ዝግጁነት እንዲኖር አስችሏል ሲሉ ተናግረዋል። የግድቡ ግንባታ ሲጀመር ተቀጥረው ይሰሩ እንደነበር ያስታወሱት የኬ.ቲ ኢንዱስትሪያል ሶሉሽን ሥራ አስኪያጅ ሞላ አስማረ፤ በሂደት የራሳቸውን ድርጅት ከፍተው ለተርባይን ማቀዝቀዣ ክፍል አካል የሆነውን ራዲያተር በራሳቸው መስራት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡ አብዛኛውን የፕሮጀክቱን ግብዓት በራሳቸው መሥራት እንደሚችሉ ገልጸው፤ ከአቅም ግንባታ ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ያስችላልም ብለዋል፡፡ በግድቡ ላይ በተለያዩ ሙያዎች ላይ የተሳተፉ በርካታ ወጣቶች በየዘርፉ የተሻለ የሙያ ደረጃ ላይ የደረሱ እንዳሉም ተናግረዋል። ( FBC)
Show all...
👍 4 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
መልዕክት
Show all...
2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.