cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

Show more
Advertising posts
428
Subscribers
-124 hours
-17 days
+4030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

09/12/2016                      የዕለቱ የወንጌል ክፍል                        ማቴዎስ 7:24-ፍጻሜ     ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም። ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል። ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ። ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና.......... ሮሜ 8:35-ፍጻሜ ያዕቆብ 1:2-13 ሐዋ.ሥራ20:16-22                                 ምስባክ                          መዝሙር 45:3-4 ደምፁ ወተሐምገ ማያቲሆሙ ወአድለቅለቁ አድባር እምኃይሉ ፈለግ ዘይውኅዝ ያስተፌሥሕ ሀገረ እግዚአብሔር https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

የራስንኃጢአት ብቻ መመልከት ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጥ መንፈሳዊጸጋ ነው። It is a spiritual gift from God for a man to perceive his own sins. ማርይስሐቅ "ከሰይጣን ይልቅ ልማድን ፍራ" ሰዎችን ወደጥፋት መንገድ የሚወስደንና የሚያጠፋን የራሳችን ልማድ ነው ። እኛ እንደ ትንሽ ነገር የምንቆጥራቸው ልማዶቻችንን ሰይጣን ሳይንቅ እኛን ለማጥፋት ይጠቀምባቸዋል። ብሒለ አበው አስተዋይ የሆኑ ሰዎች በዓለም የሚነገሩትን ብዙ ንግግር መስማት አያስፈልጋቸውም ነገርግን በእግዚአብሔር ፍቃድ በሚመራውና በሚጠቅመው ነገር ላይ ብቻ መገኘት ይፈልጋሉ ታላቁ ቅዱስ አትናቴዎስ https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂🕯🍂 ⛪️✍  #ጻድቅስ_ከመ_በቀልት ይፈሪ ወይበዝኀ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ ትኩላን #እሙንቱ_ውሰተ_ቤተ_እግዚአብሔር            (መዝ/ዳዊት ፺፪ ፥፲፪)❤🙏❤ #እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች     (  ፰🕯)  ለጻዲቁ    አባ    ኪሮስ🦋 ✍አባ ኪሮስ አባቱ #ንጉስ_ዮናስ_እናቱ_አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡ አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ #ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡ በ17 ዓመቱ #ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ #ከዚህ_በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ #መላእክት_መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት #ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል።        ⛪️   #አባ_ኪሮስ_አባቴ 🕯 በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ #ገዳም_ገብተህ በሀዘን ስሜት ውስጥ እንባህን አፍሰስህ እመቤቴ ጠራህ አትለይኝ ብለህ ሰባት መቶ ስግደትን ለእመ አምላክ ሰግደህ ምህረትን አገኘህ እንደ እንግዳ ሆነህ ወደ እግዚአብሔር ፀለይክ በሽተኛ ልታድን #መላእክትም_መጡ ካንተ ጋር ለመሆን እልፍ አዕላፋት እንዲሁም ጌታችን ለችግረኞች ተስፋ የሆነው አምላካችን ልክ እንደ አብርሀም እንደ #ፃድቁ_ሰው ሰው ስትቀበል በሰላም በፍቅር ነው የራስ ፀጉር  እንደ በረዶ የነጣ የፂምህ ውበት ነጭ ሆኖ የወጣ አሟሟትህ ይገርማል ለሰማው የደንቃል #እግዚአብሔር ተቀበሎ ለሚካኤል ሰጣት በመቃብርህ ላይ መስቀሉን ተከሉት ነፍስህን ከአምላክ ጋር እንዲ አሳረጓት እርሷም በተሰጣት #ክብር_ደስ እያላት        ❤️ወስብሐት #ለእግዚአብሔር 🦋 "ወር በገባ በ8 ፃድቁ አባታችን ቅዱስ አቡነ ኪሮስ  ናቸው ። ካልታሰበ አደጋ ወቶ ከመቅረት ይሰውሩን በቃል ኪዳናቸው ያስምሩን🙏    🤲           🤲           🤲 #አሜን......... 🧡 ......... #አሜን               ⊹ #አሜን🙏³⊹ 🍁🕯🍁🕯🍁🕯🍁🕯🍁🕯🍁🕯🍁🕯🍁🍂 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

💀 የሰይጣን ለቅሶ 💀 አንድ ለመመንኮስ የፈለገ ወጣኒ ወደ አበመኔቱ ይሄድና እንዲያመነኩሰው ይጠይቀዋል አበመኔቱም እንዳመነኩስህ ከፈለክ ሂድና በእስክንድርያ አደባባዮች እኔ ዘማዊ ነኝ እያልክ ለመንገደኛው ሁሉ ንገር ይለዋል ይህም ወጣት እንደታዘዘው ሲያደርግ ውሎ በነጋታው ጠዋት ቤተክርስቲያን ሲገባ በዚያ የተሰበሰቡት ሁሉ "አንተ ዘማዊ እያሉ አፌዙበት አበመኔቱም "አዎ አንተ ሀጢያተኛ ነህ" ብሎ አስወጣው ወጣቱም ምንም ሳይናገር ወጣ ይህ ወጣት ከወጣ በኋላ ግን አበመኔቱ ለተሰበሰቡት ምዕመናን እንዲህ አላቸው 👉"በትክክል ለምንኩስና የታጨች ነፍስ ይህቺ ናት እናንተ ስትስቁበት አጋንንት ግን ሲያለቅሱ አያቸው ነበር፣ እኛ ሀጢአቱን ስንዘረዝር መላእክት ግን ስሙን በብርሃን መዝገብ ሲፅፉት ተመለከትኩ አላቸው፣ ያንንም ወጣት ጠርቶ አመነኮሰው 👉ብዙ ሰዎችን ከቤተክርስቲያን ፣ ከመንፈሳዊ አገልግሎት፣ ከበጎ ስራ ከሚያርቁት ነገሮች ዋነኞቹ ትችት እና ሀሜት ነው ብንል ማጋነን አይሆንም በተለይ ደግሞ ለመንፈሳዊ ተግባር አዲስ የሆኑትን እስከመጨረሻው ላያስመልስ የሚችል ተግባር ነው 👉ወዳጄ የቱንም ያህል ብትሰደብ ፤ የቱንም ያህል ብትናቅ፤ የቱንም ያህል ሰዎች ተሰብስበው ስላንተ ቢያወሩ ፤ በተሰደብከው ልክ ክብርህም ይጨምራልና ከደጁ እንዳትርቅ 👉አንቺን ብሎ ጸሎተኛ ፤ አንቺን ብሎ ጾመኛ፤ አንቺን ብሎ ዘማሪ ፤አንቺን ብሎ ቤተክርስቲያን ተሳላሚ ፤ አንቺን ብሎ ቆራቢ ፤ .......ብዙ ብዙ ነገር እያሉ ሊያሸማቅቁሽ ቢሞክሩ ከመንገድሽ እንዳትወጪ ሰዎች በሳቁብሽ ልክ ፈታኝሽ ዲያቢሎስ ያለቅሳልና 👉 እናንተም ፈራጆች ሆይ ሰው ላይ ስትፈርዱ ሰይጣን በናንተ ይስቃል፣ የሰውን ሀጢአት ስትመዘግቡ ሰይጣን በደስታ የናንተን ሀጢአት ይፅፈዋል ስለዚህ ለወዳጆችህ እየፀለይክ ሰይጣንን አስለቅሰው በቅዱስ መስቀሉ ጠላታችን ዲያብሎስን ከእግራችን በታች ይጣልልን አሜን 🙏 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

#የቃሉን_ወተት መዝሙር 23 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። ² በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል። ³ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ። ⁴ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። ⁵ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው። ⁶ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ። https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

የኦርየንታል ኦርቶዶክስ እና የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የነገረ መለኮት ውይይት ከ34 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በካይሮ መካሄድ ጀመረ  ! ጉባኤው “የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡14) በሚል መሪ ቃል በእምነት እና  እና በአገልግሎት እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂደዋል፤ ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ በግብጽ ቅዱስ ቢሾይ ገዳም “ሎጎስ” የስብሰባ ማዕከል መካሄድ የጀመረ ሲሆን በኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያናት እና በምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መካከል ይፋዊ የነገረ መለኮት ውይይት በዚህ ስብሰባ ተካሂዷል። ዓላማው ከ30 ዓመታት በላይ የተቋረጠውን ይፋዊ የሥነ-መለኮት ንግግር እንደገና ለመቀጠል እና እንደገና ለመገምገም መሆኑን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን አስታውቃለች። ጉባኤው የተከፈተው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እና በፓትርያርክ አቡነ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ፣ መልእክት ነው። በስብሰባው ላይ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያናት ቤተሰቦች ላይ የሚነሱ ልዩ ልዩ የአስተምህሮ ጉዳዮች ወደ አንድ ወጥ አቋም ለመድረስ በማለም በዚሁ ልክ ውይይት መደረጉ ነው የተገለጸው። የምሥራቃውያን ኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያናት ልዑካንን ጨምሮ በጉባኤው  የአሌክሳንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ (አስተናጋጅ ቤተ ክርስቲያን)፣ የአንጾኪያ እና የመላው ምሥራቅ ፓትርያርክ (ሶርያ )፣ የአርመን ኦርቶዶክስ፣ የኦርቶዶክስ የኢትዮጵያ የኤርትራ አቢያተ ክርስቲያናት መወከላቸውን የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ገልጻለች ። https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

🕊 † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤ † [  † መስከረም ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †  ] † 🕊  ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት 🕊  † † ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል:: ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ: አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው:: ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል:: [መዝ.፴፫፥፯] (33:7) ¤ እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል:: [መዝ.፺፥፲፩] (90:11) ¤ የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው:: [መሳ.፲፫፥፲፰] (13:18) ¤ ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! [ዳን.፲፥፳፩] (10:21) ¤ ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው:: [ዳን.፲፪፥፩] (12:1) ¤ በፊቱ ሲቆምም ስለ ክብሩ ጫማ አውልቆ: ባጭር ታጥቆ ነው:: [ኢያ.፭፥፲፫] (5:13) + ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር በዚህች ዕለት መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች:: በድሮው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች:: ይህች ከተማ ክርስቲያኖችም: ኢአማንያንም ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት:: በከተማዋ የክርስቲያኖች ቁጥር ትንሽ ቢሆንም በእምነት ግን ጠንካሮች ነበሩ:: በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ባለ ፍጹም እምነት ሰው ነበር:: በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረጉ ነበር:: ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ [ዮናናውያን] ግን ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ:: በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ:: በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ:: በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር:: ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት:: ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ:: ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ:: በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ቢወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው:: አሰበው: ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ ሊሆን ነው:: እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ ቅዱስ ሚካኤልን ተማጸነ:: ከዚያ ላለመውጣትም ወሰነ:: ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ:: በዚህ ጊዜ ግን ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ:: መጋቢውንም "ጽና: አትፍራ" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት:: በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ:: ወንዙም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ:: +የሚገርመው ሸለቆው የተፈጠረው በቤተ ክርስቲያኑ በታች ነው:: ቅዱስ ሚካኤል ግን መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ:: በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው:: መልአኩንም አከበሩት:: አሕዛብ ግን አፈሩ:: † 🕊 ቅዱስ ቢሶራ ሰማዕት  🕊  † † በዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያን መሆን ብቻ የሚያስከፍለው ዋጋ ብዙ ነበር:: ከምንም በላይ መከራው የጸናባቸው ግን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ነበሩ:: ክደው ያስክዳሉ በማለት አብዝተው ያሰቃዩአቸው ነበር:: ቶሎም አይገድሏቸውም:: መከራውን ከማራዘም በቀር:: ከእነዚህም አንዱ አባ ቢሶራ ነው:: እርሱ በምድረ ግብፅ 'መጺል' ለምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ ነበረ:: በእድሜው አረጋዊ: በትምሕርቱ ምሑር: በምግባሩ ቅዱስና በእረኝነቱም የተመሠከረለት በመሆኑ በምዕመናን ዘንድ ተወዳጅ ነበር:: መከራው እየገፋ ሲመጣ ግን ቅዱሱ በመፍራት ፈንታ የሰማዕትነት ፍቅር አደረበት:: ስለ ሃይማኖት መሞትን እና ቶሎ ወደ ክርስቶስ መሔድን ናፈቀ:: ነገር ግን መልካም እረኛ ነውና በጐቹን [ምዕመናንን] እንዲሁ ሊተዋቸው አልወደደም:: ሰብስቦ ምን እንዳሰበ አማከራቸው:: የሰሙት ነገር ክርስቲያኖችን አስለቀሳቸው:: "አቡነ ለመኑ ተኀድገነ-አባታችን ለማን ትተኸን ትሔዳለህ?" ሲሉም ከእግሩ ወደቁ:: እርሱ ግን አስረድቷቸው: አጽናንቷቸውም በእንባ ተሰናበታቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ "አብረንህ እንሞታለን" ብለው ተከተሉት:: ቅዱስ አባ ቢሶራን ከብዙ ስቃይ በኋላ አረማውያን ከነተከታዮቹ በዚህ ቀን ገድለውታል:: †   🕊  ቅዱስ ያሳይ ንጉሥ  🕊  † † በቀደመው ዘመን መንግስታቸውን ትተው ከመነኑ ነገሥታት አንዱ ቅዱስ ያሳይ ነው:: ምናኔ በቁሙ ከባድ ነው:: መንግስትን: ዙፋንን: ክብርን ትቶ መመነንን ደግሞ ከማድነቅ በቀር እንዲህ ብለው ሊገልጹት ይከብዳል:: ቅዱስ ያሳይም መንግስቱን ትቶ ልምላሜ ወደሌለበት ደረቅ በርሃ ሔደ:: በዚያም ከአንዲት ዛፍ በቀር ምንም ነገር አላገኘም:: በዚያች ደረቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ለዓመታት በጾምና በጸሎት ተጋደለ:: በዘመነ ተጋድሎው ከዛፏ አልወረደም: ሰውም አይቶ አያውቅም:: በመጨረሻም ስለ ቅድስናው ዛፏ ለምልማለች:: እርሱም በዚህች ቀን ዐርፏል:: † አምላከ ቅዱሳን ተራዳኢ መልአክን ይዘዝልን:: ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን:: 🕊 [  † መስከረም ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ፪. ቅዱስ ቢሶራ ሰማዕት ፫. ቅዱስ ያሳይ ንጉሥ ፬. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት [ ልደቱ ] ፭. "14,730" ሰማዕታት [ የቅዱስ ፋሲለደስ ማሕበር ] † " የፋርስ መንግስት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቁዋቁዋመኝ:: እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ:: እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት:: " † [ዳን.፲፥፲፫] (10:13) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር †          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

🌼ወዳጄ ሆይ መልካም ወዳጅ ትባል ዘንድ🌼 "እግዚአብሔር አምላክህን ካላወቅክና ካልመሰልከው በቀር ባልንጀራህን፣ ወንድምህን፤ እኅትህን ከዛም አለፍ ሲል እናትህን አባትህን ከዚህም ሲከፋ የገዛ ሚስትህን ጤናማ በሆነ መውደድ ልትወዳቸው አትችልም፡፡ ስለዚህ ወዳጄ ይህን እርከን ተከትለህ ወደ እውነተኛው ወዳጅነት እለፍ፡፡ “በእምነት ላይ በጎነትን፤ በበጎነት ላይ እውቀትን፤ በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፤ ራስንም በመግዛት ላይ መጽናትን፤ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፤ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማች መዋደድ፤ በወንድማማች መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ” (2ጴጥ.1÷7) እንዲህ አድርጎ ራሱን በቅድስና ያበቃ ሰው ራሱን ከራስ ወዳድነት በጠራ መልኩ ይወዳል፡፡ ስለዚህም ባልጀራውንም መውደድ ለባልንጀራው መልካም ወዳጅ መሆን ይቻለዋል፡፡" https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

                          †                           🌼 [ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ! ] 🌼    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🍒 [ ፀጉራችንንና ውበታችንን ለእግዚአብሔር ! ] 🕊 ......... " ፀጉርን ከማሳጠር በላይ ምን ትንሽ ነገር አለ ? ነገር ግን ይህንንም ለእግዚአብሔር ክብር ማድረግ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ሴቶች በፀጉራቸው ምክንያት ወንዶች የሚሰነካከሉ ከኾነና ይኽንንም ዐውቀው ባይቆርጡትም ወንዶች በማይሰነካከሉበት መንገድ ራሳቸውን ቢያጌጡ ፀጉራቸውን ለእግዚአብሔር ክብር አድርገውታልና ሹመት ሽልማታቸው የበዛ ነው፡፡  የክፉ ምኞት ፍላጻን ለእግዚአብሔር ክብር ሲባል አስቀርተውታልና ዋጋቸው በሰማያት ዘንድ ታላቅ ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ክብር ብሎ አንዲት ኩባያ ውኃን የሰጠ ሰው ርስት መንግሥተ ሰማያትን የሚያገኝ ከኾነ ፥ የምናደርገው ኹሉ ለእግዚአብሔር ክብር ብለን የምናከናውነው ከኾነማ ሹመት ሽልማታችን እንደምን አይበዛ ? ለእግዚአብሔር ክብር ብሎ መሔድም አለመሔድም አለ፡፡ ምን ማለት ነው ? ወደ ክፋት የማንሔድ ከኾነ ፣ የቆነጃጅትን ውበት በማድነቅ ስም ልቡናችንን በምኞት መንፈስ የማንጠመድ ከኾነ ፣ አንዲት ቆንጆ [ በሰውኛ ግንዛቤ ] ልጅ በፊታችን ብናይና እንደምታሰናክለን ተረድተን ዐይናችንን ከእርሷ ዞር የምናደርግ ከኾነ ውበትን ለእግዚአብሔር ክብር አዋልነው ይባላል፡፡ አለባበሳችንም ቢኾን ለእግዚአብሔር ክብር ልናደርገው ይገባናል፡፡ እጅግ ውድ የኾኑ አልባሳትን ባንለብስ ፣ ሰውነታችንን እጅግ ሳናራቁት ፣ በአጠቃላይ ሰውን የማያሰናክል አለባበስን ስለ እግዚአብሔር ክብር አደረግነው ይባላል፡፡" 🕊 [ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ] †                       †                        † 🌼                    🍒                     🌼 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

                          †                           [    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ] 💛 [     ሦስተኛ ጸሎቱ  ፦ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ❝ ከእንቅልፌ ስነቃ ፈጥኜ ወደ አንተ አንጋጥጣለሁ ፤ አቤቱ የሰው ሁሉ ወዳጅ የሆንክ ጌታ በአንተ ፍቅርና ደግነት ወደ አንተ ለመጸለይና መንፈሳዊውን ሥራ ለመሥራት እጥራለሁ፡፡ በሁሉም ጊዜ በማንኛውም ነገር እርዳኝ ፤ ከማንኛውም ከዓለም ክፉ ሥራና ከዲያብሎስ ጥቃት ሁሉ አውጣኝ ፤ ወደ ዘላለማዊው መንግሥትህ ምራኝ፡፡ አቤቱ ፈጣሪዬ አንተ የማንኛውም መልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ነህና ፣ ተስፋዬ ሁሉ በአንተ ላይ ነው፡፡ አቤቱ ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን፡፡ ❞ የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡ ይቆየን ! †                       †                         † 💖                    🕊                     💖 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780
Show all...
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.