cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Rift Valley

Advertising posts
580
Subscribers
+124 hours
+87 days
+530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
በትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ በቡኖ በደሌ ዞን በደሌ ወረዳ  በደረሰ ትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ  ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡ በዚህም የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ  የአደጋው መንስዔ እየተጣራ  መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የዕለቱ ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Qabxiin qormaata kutaa 12ffaa guyyaan ifa ta'u barame. https://bbc.in/4gciKHX
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የዕለቱ የውጭ ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ https://t.me/RiftValleyMedia
Show all...
እናቱን ጨምሮ 4 ሰዎች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ያደረገው በእስራት ተቀጣ በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባ ቦራ ዞን ዳሪሙ ተብሎ በሚጠራ ወረዳ አንድ ግለሰብ ወላጅ እናቱን ጨምሮ 4 የቤተሰብ አባላትን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ በጽኑ እስራት ተቀጣ። በዳሪሙ ወረዳ ቤና 3ኛ ተብላ በምትጠራ መንደር አሕመድ ኡስማን የተባለው ወንጀለኛ ወላጅ እናቱን፣ እህቱን እና የ8 ወር ጨቅላ የሆኑ መንትያ የእህቱን ልጆች በእሳት ተቃጥለው ሕይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጉ ተገልጿል። የኢሉ አባ ቦራ ዞን ዐቃቤ ሕግ የተለያዩ ወንጀሎች የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ ጉታ ዱጉማ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ ግለሰቡ በአራት የገዛ የቤተሰብ አባላቱ ላይ አሰቃቂ ወንጀሉን የፈጸመው ሰኔ 29/2016 ዓ.ም. ነው። “ወንጀሉ በተፈጸመበት ዕለት ግለሰቡ ከእናቱ የጠየቀውን የገንዘብ ብድር ባለማግኘቱ የቂም በቀል ይዞ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ተደብቆ ቆየ” ይላሉ። የዞኑ የዐቃቤ ሕግ ባልደረባ እንደሚሉት ከሆነ ከለሊቱ 7 ሰዓት ሲሆን፤ አሕመድ ኡስማን የተባለው ግለሰብ ወደ ወላጅ እናቱ ቤት በመመለስ አራቱ የቤተሰብ አባላት ያሉበትን የሳር ክዳን ቤት ላይ እሳት አያይዟል። “ወደ እናቱ ቤት ተመልሶ አራቱ ሰዎች ከውስጥ እያሉ ከውጪ በሩን ዘግቶት እሳት አያያዘ” በማለት የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመበትን ሁኔታ አቶ ጉታ አስረድተዋል። በዚህም ምክንያት የፍርደኛው እናት፣ እህት እና የ8 ወር ዕድሜ ያላቸው የእህቱ መንትያ ልጆች ሕይወታቸው ማለፉን ጨምረው ተናግረዋል። የወንጀል ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ተደርጎ የክስ ሂደቱ በኢሉ አባ ቦራ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱን ተናግረዋል። በፍርድ ሂቱ ላይ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም የወንጀል ክስ እንደሌለበት፣ አካል ጉዳተኛ መሆኑን እና ባለቤቱ ነብሰ ጡር መሆኗን በመግለጽ የቅጣት ማቅለያ እንዲደረግለት ጠይቋል። ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ተከሳሹ ይህን አሰቃቂ ወንጀል በገዛ የቤተሰብ አባላቱ ላይ የፈጸመው በበቀል ተነሳስቶ እና አስቦበት በመሆኑ ከባድ ቅጣት እንዲተላለፍበት ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ ነሐሴ 28/2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት አሕመድ ኡስማን በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል። ይሁን እንጂ አቶ ጉታ በበቀል ተነሳስቶ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ጨቅላ ሕጻናትን ጨምሮ 4 ሰዎችን በገደለው ሰው ላይ የተላለፈው ቅጣት አነስተኛ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “እንደ ዐቃቤ ሕግ የተላለፈው ቅጣት በቂ ነው ብለን አናምንም። ፍርድ ቤቱ በምን ላይ ተመርኩዞ ይህን ውሳኔ እንደሰጠ ለማወቅ ግልባጭ እንዲሰጠን ጠይቀናል። በሕጉ መሠረት በቀጣይ ይግባኝ የምንጠይቅ ይሆናል” ሲሉ የዞኑ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ባልደረባ ለ#ቢቢሲ ተናግረዋል።
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ቻይና ለአፍሪካ 51 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ትሰጣለች፣ አንድ ሚሊዮን ስራዎችን እንደምትሰራም ቃል ገብታለች።                                                                                 ፕሬዚደንት ዢ ጂንፒንግ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ወደ 51 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ ለተጨማሪ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች እና ቢያንስ 1 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ቻይና በዕዳ በተሞላባት አፍሪካ ዙሪያ የምታደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር ሐሙስ ዕለት ቃል ገብተዋል። ቻይና ከአፍሪካ ጋር በኢንዱስትሪ፣በግብርና፣በመሰረተ ልማት፣በንግድ እና በኢንቨስትመንት ትብብሯን ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ዢ በቤጂንግ ለተሰበሰቡ ከ50 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ልዑካንን ለሶስት አመታት የሚቆየውን የቻይና አፍሪካ የትብብር ጉባኤ ልዑካን ተናግረዋል። @Reuters እንደዘገበው)
Show all...
"የመሻገር ጥሪቶች የአዲስ ብርሃን ወረቶች" #ጳጉሜን1 #የመሻገር_ቀን_ተከብሮ_ይውላል ፩ "ግብርና (የስንዴ ሰብል....) ፪ ኢዱስትሪ (ተኪ ምርቶች....) ፫ ቱሪዝም (አዳዲስ መዳረሻዎች፦ ገበታ ለሀገር ፥ ነባሮችን ማደስ፣ ደረጃቸውን ከፍ ማድረግ ፬ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ" ለመሻገር ቀን "የመሻገር ምልክቶቻችን።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ክርስቲያኖ ሮናልዶና ሊዮኔል ሜሲ በባሎንዶር ሽልማት እጩ ውስጥ ሳይካተቱ ቀሩ ከ21 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሊዮኔል ሜሲ በባሎንዶር ሽልማት እጩ ዝርዝር ውስጥ ሳይካተቱ ቀሩ፡፡ ሽልማቱን አምስት ጊዜ ያሸነፈው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ሮናልዶ ባለፈው ዓመትም የእጩነት እድል ሳያገኝ መቅረቱ ይታወሳል፡፡ አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በበኩሉ 18 ጊዜ ታጭቶ ስምንተ ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን ዘንድሮ የአርጀንቲና ኮፓ አሜሪካ ዋንጫን ቢያሸንፍም ለባሎንዶር እጩነት ግን ሳይሳካለት ቀርቷል። የአውሮፓ ሊግ 2024 አሸናፊ የሆነችው ስፔን የ17 ዓመቱ የባርሴሎና የክንፍ ተጫዋች ላሚን ያማልን ጨምሮ 6 ተጫዋቾቿ በእጩ ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል፡፡ ከሪያል ማድሪድ ጋር የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ያነሱት ኒኮ ዊሊያምስ፣ አሌሃንድሮ ግሪማልዶ፣ ዳኒ ኦልሞ፣ ሮድሪ እና ዳኒ ካርቫጃል ለባሎንዶር 2024 እጩ ከሆኑተ መካከል ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም እንግሊዝ ለኢሮ 2024 የፍፃሜ ውድድር እንድታልፍ የረዱ 6 ተጫዋቾች በ2024 የባሎንዶር እጩ 30 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በፓሪስ ኦሊምፒክ የተሳተፈችው አትሌት ፍቅረኛዋ ባደረሰባት ጥቃት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች ዑጋንዳዊቷ የማራቶን ሯጭ ርብቃ ቼፕቴጌ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በፍቅረኛዋ በደረሰባት ጥቃት አብዛኛው የሰውነቷ ክፍል በእሳት ከተቃጠለ ከቀናት በኋል ለህልፈት ተዳርጋለች፡፡ በአትሌቷ እና ፍቅረኛዋ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ቤንዚን በላይዋ ላይ በማርከፍከፍ በእሳት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት መገለፁ ይታወቃል፡፡ በክስተቱ ፍቅረኛዋም መጎዳቱና ሁለቱም ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ነበር፡፡ ነገር ግን አትሌቷ በህክምና ስትረዳ ቆይታ ሕይወቷ ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.