cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dr. Sara Yohannes_health tips/ስለጤናዎ ይወቁ_በዶ/ር ሳራ ዮሀንስ

ይህ የቴሌግራም ገጽ ጤናን የሚመለከቱ ጉዳዮች የሚቀርቡበት ነው። በተጨማሪም በYouTube https://youtube.com/@Sarayohannes_444?si=KLp_A8Mu5sNOzgMW Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

Show more
Advertising posts
829
Subscribers
-224 hours
-37 days
+1030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

❌❌ጥንቃቄ ሦስት ሕገወጥ የከረሜላ ምርቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከሕብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በነሐሴ ወር በመርካቶ ገበያ በአደረገው የዳሰሳ ስራ ብሔራዊ አስገዳጅ ገላጭ ጽሑፍ ደረጃ CES 73/2013 ሳያሟሉ ገበያ ላይ የዋሉ ሦስት አይነት የከረሜላ ምርቶችን ማግኘቱን በመግለጽ፤እነዚህ ህገወጥ የከረሜላ ምርቶች ማን እንዳመረታቸው፣ የት አገር እንደተመረቱ፣ የአምራቹ አድራሻ ያልታወቀ እና የምርቱ ባች ቁጥር የሌለው በመሆኑ የአገሪቱን አስገዳጅ ገላጭ ፅሑፍ ደረጃ ስለማያሟሉ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ያሳስባል፡፡ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥቆማ በመስጠት ተሳትፎ ያደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን በዚህ አጋጣሚ እያመሰገነ መሰል ጤና የሚጎዱ ሕገወጥ ምርቶች ሲያጋጥሙ ህብረተሰቡ በባለስልጣኑ ነፃ የስልክ መስመር 8482 ወይም በየአካባቢው ላሉ የጤና ግብዓት ተቆጣጣሪ ተቋማት አልያም ለፖሊስ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ https://www.facebook.com/share/p/15f8QwhSESd7EHUT/?mibextid=oFDknk
Show all...
Show all...
ስትሮክ ምንድነው?እንዴትስ እንከላከል?ህክምናውስ?ስትሮክ የመታው ሰው ምን ምን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል?በዶ/ር ሳራ/Stroke by Dr Sara/Healthy

📌ስትሮክ በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት በመላው ዓለም እንዲሁም በሀገራችን እጅግ እየተበራከተ የሚገኝ እና ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የህመም አይነት ነው፡፡ 📌ስትሮክ ሊከሰትባቸው የሚችሉባቸው መንገዶች ሁለት ናቸው። ✔ በጭንቅላት ውስ በሚከሰት የደም መፍሰስ ✔ ወደ ጭንቅላት ሊደርስ የሚገባው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋረጥ 📌ስትሮክ ከተከሰተ በኋላ በአፈጣኝ ወደ ህክምና መውሰድ እና ህክምናውን ወዲያውኑ መውሰድ የታማሚውን ሊደርስበት የሚችለውን የጉዳት ክብደት መቀነስ እና የማገገም ሁኔታውን ሊፋጥን ይችላል፡፡ * ለበሽታው ሚያጋልጡ ሁኔታዎች ✔ እድሜ፡ በእድሜ በገፋን ቁጥር በስትሮክ የመጠቃት እድላችን ይጨምራል ✔ ጾታ፡ ስትሮክ በአብዛኛው በወንዶች ላይ እንደሚከሰት ጥናቶች ያመለክታሉ ✔ በዘር ሊተላለፍ እንደሚችልም ጥናቶች ያመለክታሉ ✔ የደም ግፊት መጨመር ✔ የኮሌስትሮል መጠን መጨመር ✔ ሲጋራ ማጤስ ✔ በስኳር ህመም መያዝ ✔ የሰውነት ክብደት መጨመር ✔ ከዚህ ቀደም በስትሮክ መጠቃት * የስትሮክ ህመም ምልክቶች 📌ስትሮክ በተከሰተ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የአንጎል ህዋሶች መሞት ይጀምራሉ ይህም የሚከተሉትን አይነት ምልክቶች ያስከትላል ✔ ለመራመድ መቸገር ወይም ሚዛን አለመጠበቅ ✔ ለመነጋገር መቸገር ✔ የሰውነት ክፍል (እጅ ወይንም እግር) ያለመታዘዝ ✔ የአይን ብዥታ ✔ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የራስ ምታት ✔ ግራ የመጋባት ስሜት 📌ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች በአቅራቢያው በሚገኘው ሰው ከተመለከቱ አፋጣኝ እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ ተገቢ ነው። * ስትሮክን የመከላከያ መንገዶች የመጀመሪያ እና ቀዳሚው የመከላከያ መንገድ ስለበሽታው ምንነት እና ስለሚያስከትለው ጉዳት ማወቅ ነው፡፡ ስትሮክን የመከላከያ መንገዶች ከእለት ተእለት የአኗኗር ሁኔታችን ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ► የደም ግፊት መጠናችንን ማወቅ እና የደም ግፊታችን ከፍተኛ ከሆነም በሚገባ ለመቆጣጠር መሞከር፡፡ የደም ግፊት መድሃኒት የምንወስድም ከሆነ በትክክል እና ያለማቋረጥ መውሰድ፡፡ ► የስኳር ህመም ተጠቂ ከሆኑ የስኳር መጠኖን መቆጣጠር ► ጭንቀትን ማስወገድ ► ሲጋራ አለማጤስ ► የአልኮል መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ መጠጦችን አለመውሰድ ► የምንጠቀመውን የጨው መጠን መቀነስ ► ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ያለማዘውተር ► በቀን ለ 30 ደቂቃ ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም የእግር መንገድ መሄድ ► የሰውነት ክብደትን መቀነስ፡፡ እባክዎን ለወዳጅዎችዎ ያካፍሉ! 📌In this video types, definition, symptoms, diagnosis, treatment and prevention of stroke is explained by Ethiopian family physician in Amharic. Stroke Ischemic stroke Hemorrhagic stroke Hypertension Diabetes Mellitus Heart disease Preventive medicine Family Medicine Medicine Physiotherapy Speech therapy Rehabilitation Internal medicine Telegram channel 👉

https://t.me/healthtipsbydrsarayohannes

https://youtube.com/shorts/jCVAUUhNq_M?si=AWQCbN_oBJysx2fX

https://youtube.com/shorts/0jWbiG0MV0A?si=4QHc4j_mLQP4ySok

#ebs #etvnews #seifuonebs #seifufantahun #seifu #ethiopia #eritrea #africa #healthy #health #lifestyle #stroke #cerebrovascular #healthtips #medical #medicaladvice #stroketreatment #strokesurvivors #youtube #trending #viralvideo

3
ቀድሞ መከላከል የሚቻሉ የጤና እክሎቸችን ባለማውቅ እና ቅድመ ምርመራ ባለ ማድረግ ሳቢያ የሚከሰቱ፤ እስከ የህይወት ህልፈት የሚያደርሱ በሽታዎችን ለመከላከል ያለመ የነፃ ህክምና በአዲስ አበባ ተሰጠ። የኩላሊትና የልብ ችግሮች ፣ ስኳር ፣ ደምግፊት፣ ካንሰርና መሰል ተላላፊ ያለሆኑ በሽታዎች ቀድሞ መከላከል እየተቻለ ነገር ግን ባለማወቅና ወደ ጤና ተቋማት ዘግይቶ በመምጣት ሳቢያ ከፈተኛ የሰው ህልፈትን እያስከተሉ ይገኛሉ። እንደ አብነትም ባደጉ ሀገራት በቅደመ ምርመራ ሳቢያ የማህፀንና የጡት ካንሰር በሽታዎችን ገዳይነት ከ5 ከመቶ በታች ማድረስ ቢቻልም በኢትዮጵያ ግን በበሽታዎቹ ምክንያት የሚከሰት ሞት ምጣኔ አሁንም ከ50 ከመቶ በላይ ነው። ኢንስቲዪዩት ኦፍ ሄልዚ ሜትሪክስ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር ያሳተመው ጥናት እንደሚያሳየው እ ኤ አ በ2019 በአዲስ አበባ በበሽታዎች ምክንያት ከተከሰቱ ሞቶች ውስጥ 55 ከመቶ የሚሆኑት ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የተመዘገበ ነው። መሰል ነባራዊ ሁኔታዎችን መነሻ በማድረግ ፍቅረ ሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ማህበራዊ ሀላፊነትን መወጣት በሚል መርህ በትላንትናው እለት የነፃ የቅድመ ምርመራ ህክምና በመቶዎች ለሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሰጥቷል። በሆስፒታሉ የጥራት ማሻሻያ እና ቁጥጥር ሀላፊ የሆኑት ሲ/ርቅድስትሀብተማርያም_ እንደተናገሩት ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ቀድሞ መከላከል እና ከፍ ያለ ጉዳት ሳያስከትሉ መድረስ መቻል ዋነኛው በሽታዎቹን ለመቆጣጠር የሚያስችል መንገድ መሆኑን አንስተዋል። ይሁን እንጂ በሀገራችን ያለው አነስተኛ ግንዛቤ ሰዎች ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጡት በሽታው ከፍ ያለ ጉዳት ካስከተለባቸው ብቻ ነው የሚሉት ሲስተር ቅድስት በዚህም ሳቢያ የሚከሰቱ የህይወት ህልፈቶች ተበራክተዋል ብለዋል። ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሚያስከትሉትን ሞት ለመቀነስ ባለመ ቅድመ ምርመራ አማካኝነት ፍቅረሰላም ሆስፒታል በትላንትናው እለት በሰጠው የነፃ አገልግሎት በተለምዶ ሀያት አደባባይ በሚባለው ስፈራ ከ350በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የቅድመ ምርመራ ህክምና መሰጠቱን ሲስተር ቅድስት ገልፀዋል። የትላንቱ መርሀ ግብር ፍቀረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግልት መስጠት ከጀመረበት ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ ለሶስተኛ ጊዜ ያከናወነው ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል። በጥቅሉ በ2016 ዓ.ም በሽዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ህክምናው እንደተሰጠ አስታውሰው በመጭው አመትም ይህንኑ ማህበራዊ ሀላፊነት በሁለት ወር ለአንድ ጊዜ ለማከናወን ማቀዳቸውን አስገንዝበዋል። ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ከ24 አመት በፊት በክልኒክ ደረጃ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ባስገነባው ባለ 9 ወለል ህንጻ አጠቃላይ የህክመና አገልገሎትን ከመስጠቱ ባሻገር ከ350 ዜጎች በላይ ቋሚ የስራ እደል መፍጠር ችሏል። https://t.me/fikreselamghospital
Show all...
Fikreselam General Hospital

This is our official telegram group of Fikreselam General hospital TikTok - fikreselam_g.hospital

3
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የመውሊድ በአል ይሁንላችሁ። መልካም በአል❤
Show all...
🥰 4 3
Show all...
አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ የፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ክብር አምባሳደር፣በ+251939595960 ይደውሉና ቀጠሮ ያስይዙ/Ethiopia

📌የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ  ገመቹ በፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ሰኞ ነሐሴ 20,2016 ዓ.ም ተገኝተው ወዳጃዊ ጉብኝት በማድረጋቸው ክብር ይሰማናል። በዝግጅቱ ላይ ለአርቲስት ሀረገወይን አሰፋ እና ለዶ/ር ሳምሶን እስጢፋኖስ የብራንድ አምባሳደር ሰርተፍኬት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ተበርክቶላቸዋል። የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ  ገመቹ ላደረጉልን ጉብኝት እና ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን። ✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች 📌አንድ ላይ በመሆን የፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል መለያ የሆኑትን ልዩ አገልግሎቶችን እና ርህራሄ የተሞላበት አካሄድን ለማህበረሰቡ በሰፊው ተደራሽ ለማድረግ ቆርጠው ተነስተዋል ። የጋራ ችሎታቸው  ታካሚዎቻችን እና ማህበረሰቦቻችን ለጤንነታቸው እና ለደህንነታቸው ቅድሚያ እንዲሰጡ ያነሳሳቸዋል። ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል መልካም የስራ ዘመን ይመኝላችኋል🙌 የቴሌግራም አድራሻችን👉

https://t.me/fikreselamghospital

በ+251939595960 በመደወል የሚፈልጉት ሀኪም ጋር ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። መልካም አዲስ አመት🇪🇹 #ebs #ethiopia #youtube #youtuber #eritrea #health #seifufantahun #seifuonebs #familydoctor #familymedicine #trending #viralvideo #youtubeshorts #

2
Photo unavailableShow in Telegram
አስደሳች ዜና | የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከOperation Smile ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ላለባቸው ሕጻናት እና አዋቂዎች ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመደበኛነት ሳምንቱን ሙሉ እንደሚሰጥ ያውቃሉ? እንግዲያውስ የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ችግር Cleft lip እና Cleft palate ያለባችሁ በመሉ ወደ የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመሔድ መመዝገብ ይችላሉ:: ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚመጡ ታካሚዎች የትራንስፖርት እና የምግብ አገልግሎት እንዲሁም ለሚያድሩት ;የአልጋ (መኝታ ) ወጪ ይሸፈናል፡፡ ✔ወቅታዊ የስራ ቅጥር መረጃዎችን በየጊዜው ለማግኘት ቻናላችንን ይከታተሉ:: 🩵 t.me/addlist/IWOV6uABAi5lYTA0  🖥 youtube.com/@HIVN 📱 fb.com/healthinovation/
Show all...
👍 5👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2017 ዓ.ም በሠላም አደረሳችሁ፣ይህ አዲስ አመት የሠላም፣የፍቅር፣የጤናና የብልጽግና ዘመን ይሁንላችሁ።መልካም በአል 🇪🇹❤
Show all...
7🥰 3
Show all...
ወላጆችና አሳዳጊዎች ንቁ!!የህጻናትን ጾታዊና አካላዊ ትንኮሳና ጥቃትን እንዴት እንከላከል?በዶ/ር ሳራ/Dr Sara #children #justiceforheaven

📌ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በሁሉም የዓለማችን ክፍል የሚፈጸም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው። ይህ ጥቃት በተለይም በሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ላይ ጎልቶ የሚታይ ችግር ነው። 📌በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሦስት ሴቶች መካከል አንዷ ማለትም 35 በመቶ የሚሆኑት በሕይወት ዘመናቸው አካላዊ ጥቃት ወይም ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸውና በአጠቃላይ በዓለማችን ካሉት ሴቶች 50 በመቶ የሚሆኑት አንድ ወይም ሌላ አይነት ጾታዊ ጥቃት እንደሚያጋጥማቸው መረጃዎች  ይጠቁማሉ። 📌እንደ 2016 የሥነ-ህዝብና ጤና ዳሰሳ መሰረት፤ በሀገራችን 26 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች አካላዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። በሴቶችና ታዳጊ ሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች የተለያየ መልክ ቢኖራቸውም፣ መገለጫቸው በዋነኛነት አካላዊ፣ ወሲባዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቃት ነው። በተጨማሪም የስርዓተ-ጾታ እኩልነት አለመከበር፣ አድሎዓዊ እና የተዛቡ አመለካከቶች፣ ልማዶችና ባህሎች ናቸው። 📌እነዚህ ጥቃቶች ከሚያመጡት አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት በተጨማሪ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይገድባሉ። ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ዳፋው በልጆች፣ በቤተሰብ፣ በማህበረሰብና በሀገር ደረጃም የሚያስከትለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ከፍተኛ ነው፡፡ 📌3Rs to prevent sexual abuse and assault 1) Recognize unsafe touch 2) Refuse unwanted touch 3)Report abuse

https://youtu.be/5qVreR-Myt8?si=dBHJFxXAC6_WYaRC

የቴሌግራም ቻነል👉

https://t.me/healthtipsbydrsarayohannes

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት በቴሌግራም @drsara4444 መልእክት ያስቀምጡ። ከእኔ ጋር በአካል ለመገናኘት በፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል በ0939595960 በመደወል ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። አድራሻ - CMC ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ #ebs #ethiopia #eritrea #ethiopian #habesha #youtube

👍 3 2
1 comment
Repost from WeCare ET
🚨በአለም የጤና ስጋት መሆኑ የታወጀው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? እንዴትስ ይተላለፋል? 👩‍⚕️ በዝንጀሮ ፈንጣጣ በተያዘ ሰው ላይ የሚታዩት ምልክቶች ? 🌡ትኩሳት 🧠ራስ ምታት 💟የንፍፊት እብጠት 🫳በጣም የሚያሳክክ እና የሚቆጠቁጥ ሽፍታ 💪ጀርባ ህመም እና የጡንቻ ህመምን ያካትታል። 👨‍⚕️ በሽታው እንዴት ይተላለፋል ? 💟 የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በቆዳ ንክኪ ይተላለፋል ። 👩‍❤️‍💋‍👨በግብረስጋ ግንኙነት ፣ በመሳሳም እና በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ማውራትን ወይም መተንፈስን ጨምሮ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር በሚኖር የቀረበ ግንኙነት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። 🐀 በበሽታው በተያዙ እንስሳት ለምሳሌ እንደ ዝንጀሮ እና አይጥ ጋር ንክኪ ካለም ይተላለፋል። 👕 በተጨማሪም በቫይረሱ የተበከሉ የመኝታ አልባሳት፣ በልብሶች እና በፎጣዎች አማካይነት በሚኖር ንክኪ በሽታው ሊተላለፍ ይችላል። 📣 የበለጠ መረጃ ለማግኘት ወይንም ስፔሻሊስት ሐኪሞችን 👩‍⚕️👨🏽‍⚕️ ለማማከር 📞 9394 ላይ ይደውሉ ። #monkeypox #pandemic #pox #cdc #doctors #healthcare #doctors #wecareet #healthcare #digitalhealth #africa #9394
Show all...
👍 4
Repost from WeCare ET
የቤተሰብ ህክምና ይፈልጋሉ ? 🗣 ዶ/ር ሳራ ዩሃንስን ጨምሮ ሌሎች ስመጥር እና በሙያው የተካኑ ሐኪሞችን ለማግኘት መተግበሪያውን በመጫን ቀጠሮ ይያዙ ። 👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ። 📣Wecare ET social medias 📌 Facebook https://www.facebook.com/WeCareET/ 📌 Telegram: https://t.me/WeCareET 📌YouTube: https://tinyurl.com/rv4zjmwk 📌Instagram: https://www.instagram.com/wecareet/ 📌 Tiktok: https://vm.tiktok.com/ZMLbbyTXr/ 📌Website: wecare.et #wecare #doctors #hakim #wecareet #health #digitalhealth #healthcare #selamdoctor #9394#drselam #family
Show all...
8
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.