cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የአእምሮ ጤና ከ ዶ/ር ቶፊቅ ጋር

there is no health without mental health

Show more
Advertising posts
1 166
Subscribers
+324 hours
+937 days
+9330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ስለ ልጆት ይጨነቃሉ? እንግዲያውስ የዶ/ር አብዲ(የህፃናት ህክምና እስፔሻሊሽት) የቲክቶክ እና ቴሌግራም ድህረ ገፅ ይከታተሉ፡፡ ከልጆች ጋር በተያያዘ ስለ አካላዊ እንዲሁም አዕምሮዊ ጤና ተገቢውን ወቅታዊ መረጃ ያገኛሉ፡፡ መልካም እሁድ!!https://t.me/DrAbddiredawa
Show all...
Dr.Abdi(ዶ/ር. አብዲ ከበደ፣ የህፃናት ስፔሻሊስት ሐኪም፣ KidsHealth @Hand Tips.ድሬዳዋ

💜Welcome,Our purpose's are: 💕Dedicated to the promotion of health education in Dire Dawa, focused on developing children as agents of change and communicators of essential health messages in their families and community💐💕

👍 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል!
Show all...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል!
Show all...
በንጋታው የህግ አካለቶች የአዕምሮ ህክምና ያስፈልገዋል ብለው ሰበብ ፈልገው ሊያሰቃዩኝ ወደ አነድ የአዕምሮ ህክምና ወሰዱኝ፡፡ የድምፅ ጓዶቼ "አንተ ደና ነህ እነሱ ናቸው የታመት ምንም እዳትናገር ሊያደነዝዙክ ነው እያሉ ደጋግመው የወተውቱኛል" እኔም አሺ "እናንተን ነው እማምነው እላለው " ፖሊሱም እሺ አኛም እናምንሀለን ይለኛል እሱን እማወራው አየመሰለው ሚስኪን ፡፡ ከህክምና ባለሞያው ጋር ተገናኘን ፡፡ ሁሉን አስወጥቶ እኔ ብቻ እንደሚያናገርኝ ሲናገር እምነት አሳደርኩበት፡፡ ቀስ በቀስ ስለ ድምፅ ጓዶቼ ስለ አሳዳጆቼ እነዲሁም ወደ አዕምሮ ጓዳዬ ስለሚገቡት ሰዎች እና ስለ ጥቁሯ V-8 ለረዥም ሰአት አወራን፡፡አልፎ አልፎ የድምፅ ጓዶቼ ከእሱ ጋር እወራው እሚሉኝን እየጠየቀኝ የውይይቱ አባል ያደርጋቸው ነበር ፡፡ በስተመጨረሻ እንዲም አልኩ እባክህን እምትለኝን አደርጋለው ግን ግን ከድምፅ ጓዶቼ አትለየኝ፡፡ አሁን ህክምና ላይ ሆኜ ድምፆቹ ይናፍቁኛል በተይ የጥላሁን ገሰሰን "መለያየት ሞት ነው ለተዋደደ ሰው" እሚለውን መለያየት ሞት ነው ለተዋደደ ሰው መለያየት ሞት ነው ለተዋደደ ሰው ስቃዬን አሳየኝ ደርሶብኝ ብቀምሰው ስቃዬን አሳየኝ ደርሶብኝ ብቀምሰው ካለ አዕምሮ ጤና ፤ ጤና የለም!! ደ/ር ቶፊቅ አብደላ (የአዕምሮ ህከምና እስፔሻሊስት )
Show all...
👍 13 2
ድምፆቼን አትቀሙኝ……አእምሮዬ አልታመም !!!! ================================== ከድሮም አጀብ እና አጃቢ ወዳድ አልነበርኩም መነጠል/ብቸኝነት ትልቁ የደስታ ምንጬና መዝናኛዬ ነበር፡፡ ይህ ባህሪዬ ለቤተሰቤ የሁልጊዜ ሰቀቀን ነበር :: በተለይ እናቴ ለዚያም ነው መሰል እረ ተው የአብ ስራ ሰው ምሰል ፣ሰው ተቀላለቀል ፣ሰው ልመድ ትለኝ የነበረው ፡፡ የዩንቨርስቲ ነጥብ ሲመጣልኝ የእናቴ ሀሳብ" እንደው ይህን ልጅ ምን ብዬ ነው ሰው አገር እምሰድ እንዲ ሆንኩ እንኳን እማይል ልጅ ስትል አባቴ ግን" እሱ ጠንካራ ነው አንቺ ዝም ብለሽ ነው" በማለት ብቸኝነቴን እንደ ጥንካሬ ምልክት መቁጠሩን ያሳየኝ ፡፡ "ልጄ ደመ ቀዝቃዛ ነው ምንም ቢሆን ችሎ ያልፋል "በማለት ነበር የሽኙኝ ፡፡ ዩኒቨርስቲ የምድር ሲዖል ሆኖብኝ ነበር፡፡ አስር ሰው እሚኖርበት አንድ ክፍል ከአስር የተላያየ ባህሪ ካለው ሰው ጋር መኖር፤ለሻይ በዳቦ ቁረስ ሸማቾችን እሚያስንቅ ሰልፍ….የሻውር ሰልፍ …….የሽንት ቤት ሰልፍ…….ሰልፍ ለመሰለፍ ሰልፍ ብቻ አስቸጋሪ ነበር፡፡ በተለይ ብቸኝነቴን/ቁጥብነቴን እነደ ኩራት እሚቆጥሩ ፤ በጥቁር አንሶላ የተሰራች ቴንሽን ቦክስ ውስጥ እማሳለፈውን የራስ ገዝ አስተዳደሬን አንዳንዱ በጉጉት ሌላው በጥርጣሬ እግሬ እንደ ወጣ ሲፈትሹ ቢያምም አንድ ሁለት እያልኩ እንደምንም የአምስት አመት የዩኒቨርስቲ እስሬን ጨርሼ ወጣሁ ኡፈይይ…ወደ እራሴ ምሽግ ወደ ቤቴ አንድ ፍሬ እስኪሰጥ አስራ ዘጠን አመታት የተንከባከብከው የፍራፍሬ እረሻ በስተመጨረሻ ጊዜ ፍሬ አልባ ሲሆን አንድ ገበሬ ሊሰማው እሚችለው አይነት ስሜት ተሰምቶ ያቃል በቃ እንደዛ ይሰማኝ ጀመር በተመረኩ ሁለት አመታት ስራ ፈት ስሆን ፡፡" ስራ ፈትነትም ስራ ነው " ምክንያቱም አእምሮ ከማሰብ ስለማይቦዝን እነዳለው ገጣሚ ሰለሞን ዴሬሳ ፡፡ አዕምሮዬ የተለያዩ ጥያቄዎችን እራሱ በመፍጠር አራሱን ቢዚ ማድረግ ከእራሱ ጋር መከራከር ጀመረ፡፡ አዕምሮዬ ይጠይቅ ጀመር በተለይ ሀይማኖታዊ ጥያቄዎቸን "አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ " እዴት አነድ ነገር አነድም ሶስትም ይሆናል ፤ አላህ ለአንድ ወንድ አራት ሴት ከፈቀደ ለምን ለአደም አራት ሀዋዎች አልፈጠረም ፤ ክርስቶስ ለ እኛ ብሎ ከሞተ ለምን ይህን ሁሉ ስቃይ በ አለም ላይ እናያለን ? እኔ የትም አለው ካለ አላህ ለምን ሁሉም ሙስሊም ወደ ካባ ፊቱን ዞሮ ይሰግዳል ?አምላክ በአምሳሌ ፈጠርኳቹ ያለው ሊያሰቃየን ነው ምን አይነት ጨካኝ አምላክ ነው ? እኒ አና መሰል ጥያቄዎች አዕምሮዬን እረፈት ነሱት እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ቀናቶች ጠቆጠሩ የት ልሂድ ? ወትሮ ከአምላኬ ጋር እጅ እና ጓንት የነበርኩ እኔ ይህ እሳቤዬ አዲስ ሆነብኝ ክፍሌ ብቻዬን ቁጭ ባልኩበት የት ልሂድ ብዬ ሳስብ ? ልፀበል ? "እረ እምትጠራጠረው ጨካኝ ያልከው አምላክ ጋር አታፍርም እሚል ምላሽ ሰማው" ደነገጥኩ፡፡ በክፍሌ አራቱም መአዘን አይኔን ብዘውር ምንም ነገር አጣሁ ፡፡በር ከፍቼ ከክላሴ ውጭ ባይ የሰው ዘር የለም፡፡ በስመአም በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አልኩ አማተብኩ ፡፡ሆስፒታል ልሂድ እነዴ ዳግም ያው ድምፅ እንዴ "የአዕምሮ ሀኪም ጋር ወይ የአብ ስራ እ፨ዱ በቃ ለቀቀ ነው እሚልህ ህዝቡ፡፡እነደ መጀመሪያው ዙሪያ ገባውን ባይ ምንም ነገር የለም ፡፡ ይህ የነገሮች ሁሉ መጀመሪያ ነበር፡፡ለበአል እሚሰጠውን አንድ ሁለት ጠላ ስወስድ እምተኛውን እንቅልፍ ተመኘው ዛሬ በዚ ሁኔታ ማሳለፍ አልችልም በማለት ከሰፈር ራቅ ካለ አንድ ግሮሰሪ ገብቼ በድብቅ በሀይላንድ ፕላሰቲክ 2 ቢራ ገዝቼ ወደ ክፍሌ ገብቼ ጭልጥ ያለ እንቅልፈ ተኛው፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት አኒ ድምፆች ብቸኝነቴን ያስረሱኝ ጀመር ቅድሚያ ያስደነገጡኝ የነበሩ እኔ ድምፆች በርከት ብለው እንወያይ እንከራከር ጀመር ፡፡ በተለይ ሥለ ሀይማኖት እምናረጋቸው ክርክር ይናፈቀኝ ነበር፡፡ ሆኖም ይህን ነገር ያስተዋለችው እናቴ ፡፡ አብ ስራ ከማ ጋር ነው እምታወራው እረ አንተ ልጅ ከዚ መቃብር ውጣ እያለች ትወተውተ ጀመር፡፡ አልፎ አልፎ ከቤተስብ ጋር እራት እንድበላ ስገደድ እና ስቀላቀል የድምፅ ጓዶቼ በመሃል እየመጡ ከሁኔታው አስቂኝ ነገሮች እየፈጠሩ እያወሩኝ ፈገግ ሲያሰኙኝ እና ስስቅ አባት መአድ ላይ የምን መገልፈጥ ምንድነው እሚያስቅ እያለ ይቆጣኛል ፡፡ አይ እንትን ትዝ ብሎኝ ነው እያልኩ ለማለፍ እሞክራለው፡፡ እደምንም ያልቅና ወደ ክፍሌ አመራለው ፡፡ ገና ስገባ " ጥሩ አርቲስት ወቶሀል አንድኛ ይለኛል ይለኛል የድምፅ ጓዴ ዳግም እስቀለው ፡፡ በእናቴ "ስራ ቤት ድረስ አይመጣም ወጣ ብልህ ማስታወቂያ አየት አየት አርግ " እሚል ጉትጎታ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ለማንጋጠጥ ወጣው፡፡ አራት ሰው የጫነች ባጃጅ ላይ ከፊት አምስተኛ ሰው ሆኜ ጋቢና ገባው፡፡ ከመደበኛ ታሪፉ እጥፍ ሲቀበለኝ "በውስጤ ምን አይነት ሰቆንቋና ሹፌር ነው" ስል ፊቱ ልውጥውት አለ ሌሎች ተሳፋሪዎች ደግሞ ፈገግ አሉ፡፡ እነዴት ሀሳቤን አወቀ? አዕምሮዬ ራቁቱን የቆመ መሰለኝ ማንም ሀሳቤን እሚያቅብኝ እሚያነብብኝ አይነት ስሜት መልሴን ሳልቀበል በድንጋጤ ሽሽት ጀመርኩ ፡፡ በሁኔዬ ተሳፋሪዎቹ እና ሹፌሩ ዳግም ሳቅ ካካታ ሽምቅቅ አልኩ፡፡ ወደ ማስታወቂ ሰሌዳ ሳመራ ተርታውን ተቀምጠው ጫማ እሚያሰጠርጉ ሰዎች ስለኔ እያወሩ እነዳሉ ይሰማኛል አንዳነድ የእጅ ሰአቱን እያየ ለእኔ ጊዜ አልፎብሀል እሚል መልእክት ይሰጠኛል፡፡ አንዱ ደግሞ እኔን እየተመለከተ የጫማ ሶሉን ያሳየኛል እረግጣሀለው ከስሬ ነህ ማለቱ ነው፡፡ በመቀጠልም የሲጃራ ቁሬ ጣል አደረገና ከመሬቱ ጋር አሸው እእእ አሁን ገባኝ አገልሀለው ማለቱ ነው ፡፡ እራሴን መጠበቅ አለብኝ እንዴ አንዴ የማስታወቂያ ሰለዳ ማየቱን ትቼ ወደ እቤት እግሬ አውጭኝ ስል አንድ ጥቁር V-8 መኪና ይከተለኝ ጀምሯል ልቤ ከአሁን አሁን ያዘኝ በማለት በአፌ ልትወጣ ደረሰች ፡፡ ሹፌር ንዳው እላለው ፡፡ የሚከተለኝ መኪና ሲለው ከጎን ሲሻው ከፊት የሆና መስታወቱ በጥቁር ፕላሥቲክ የተሸፈነ ስለነበር ምንም ማየት አልቻልኩም፡፡ ግን እንደ ገባኝ የሆነ የመንግስት አካል እኔን እየተከታተለኝ መሆኑን ነው፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት አይደል ከቤት ከክፍል መውጣት አሻፈረኝ አልኩ ፡፡ የትኛውንም አይነት ኤሌክተሮኒክስ ከ ክፍሌ አወጣው አንፖሌን ጨምሮ እድሜ ለሻማ ፡፡ ከእናቴ በቀር ሌሎች የቤተሰብ አባላት ለመንግስት አካል እኔን እየሰለሉ እንደሆኑ ተረዳው ፡፡ ክፍሌ እራሴን ማፅዳት ካቆምኩ ሳምንታት ስላለፉ ክፍሉ የሆነ አይነት ሽታ አምጥቷል፡፡ ድንገት ከቤት የወጣው ቀን የለበስኩት ልብስ ላይ መከታተያ ገጥመው እነደሆነ አነዱ የድምፅ ጓዴ ሹክ አለኝ፡፡ በዚህም ምክንያት እነዚያን ልብሶች አንድ ቀን ምሽት ቤተሰብ በተኛበት ወቅት ሰብሰብ አድርጌ በሻማ ማቀታጠል ጀመርኩ፡፡ የቃጠሎ ጭስ አፍኗቸው የተነሱት የቤተሰብ አባላት የቤቱን መጋየት ሲያሰተውሉ ኡኡታቸውን አቀለጡት ሰው ተሰበሰበ ፖሊሶች እና እሳት አደጋ ሰፈራችንን ሞሉት፡፡
Show all...
👍 2
እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ!!! ወርሃዊው የሜንታል ሄልዝ አዲስ መርሃ ግብር ቅዳሜ መስከረም 4 ቀን 2017 ዓም አትላስ አካባቢ በሚገኘው በአዶር አዲስ ሆቴል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል:: የዚህ ወር ርዕስም፡- “በአዲስ አመት አዲስ ማንነት!” የሚል ሲሆን የዚህ ወር እንግዳችን ዶ/ር ምህረት ደበበ ናቸው፡፡ ለመታደም ይህን መስፈንጠሪያ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡ https://forms.gle/pyDAgWPBPhc6BCDh7 የማስታወሻ መልእክት እና የቦታውን አቅጣጫ ምልክት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይከተሉ፡፡https://t.me/mhaddisababa Happy New Year! The monthly Mental Health Addis’ event has come and it will be held on September 14, 2024 at Adore Addis Hotel (near Atlas) in the afternoon at 10:00 local time. This time the topic is “New Year New You.” Our guest speaker is Dr. Mehret Debebe. To attend please register by filling this Google form:- https://forms.gle/pyDAgWPBPhc6BCDh7 To get a reminder and get direction please join our Telegram Channel: https://t.me/mhaddisababa #mentalhealthaddis #AdoreAddis #mentalhealthawareness #talkmentalhealth #mentalhealthmatters
Show all...
MHA Event RSVP

Mental Health Addis is holding its monthly event on Saturday Sept 14/2024 (Meskerem 4, 2017) at Adore Addis Hotel near Atlas at 4:00PM (10:00 local time) on the topic of “ New Year New You!” Please fill out and submit this form if you are able to attend the event and share the link with others. Thank you.

👍 1
ሞትን በቀጠሮ ========== ማስጠንቀቂያ ፡- ይህ ፅሁፍ ለአንባቢን የሚረብሹ ይዘቶች አሉት ነጋ ለሊቱ ጀመረ ደሞ ኑሮዬ ነጋ ለሊቱ አወይ ችግሬ አዎ ስሜቴ እንዲ ነው ሰሞኑ ለምን ነጋ እልኩ ነው ከእንቅልፌ እምነቃው ግን ከእኔ እና እኔ በቀር ይህን ስሜቴን እሚያቅ አንድ ሰው የለም ፡፡መች ሰው አለኝ አዎ በፌስ ቡክ ከሶስት ሺ በላይ ጓደኞች አሉኝ ሌሎች በሺ እሚቆተሩ ተከታዮች እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊ ሚዲዎች ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው የበይነ መረብ ጓደኞች አሉኝ ፡፡ እኒህ ጓደኞች ልክ እንደ ጉርድ ፎቶ ከወገቤ በላይ ነው እሚያዩኝ ቆንጆ ሸሚዜን እና የአንገት ሀብሌን ብቻ ፡፡ ምን ይሉ ይሁን ሁለት ግራ እግር ጫማዬን እና የተቀዳደ ፑታንታዬን ቢያዩ ስንቱ የእኔን ኑሮ ይመኛል? እንዲ እጅ እጅ እያለኝ የጀመርኩትን እለት በማህበራዊ ሚዲያ ጀመርኩ ፡፡ ፌስ ቡኬ በመግቢያው ላይ ምን እያሰብሽ ነው ? (" what is on your mind ?") በማለት ይጠይቃል ካለስቃይ በአንዴ ድብን ስለማያ መንገዶች ልበል ? ለምን ነጋ ለሊቱ ልበል ? ሰው (ተከታዬቼ ) ምን ይሉኛል ? ይህን አይቼ አስክሪኔን መገላለጥ ስጀምር አንድ አብሮ አደግ ጓደኛዬ ከመጀመሪያ ልጇ እና ከባሏ ጋር የተነሳችውን እዩልኝ ስትል አየኋት ፡፡ ብሶቴን ልወጣ በዛውም አሳብቤ ላልቅስና ይውጣልኝ ብዬ የሁልግዜ ጥያቄዬን ለእጮኛዬ ልጠይቅ "መች ነው እምንጋባው ?" ልል ያጮሁኩት ስልክ አልተነሳም ፡፡ ደወልኩ ደገምኩ ደጋገምኩ በስተመጨረሻ ተነስቶ አንድ የሴት ድምፅ "ሄሎ" ፣ "ሄሎ" አለኝ የስልኬን እስክሪን ደጋግሜ አየሁት " ይሁን የእኔ " ይላል ከልብ ኢሞጂ ከስልኩ በስተጀርባ የጨቅላ ህፃን ድምፅ ያቃጭላል ፡፡ ሄሎ ይሁንን የለም ? አልኩ …… ባለቤቱ ራሄል ነኝ እሚል መልስ ከተመለሰ ብኋላ ስለተፈጠሩት ነገሮች አላስታውስም ፡፡ " ይሁን የኔ"…… እንደ ስሙ ምኞት ሆነ ፍቅረኛ የሆነ ግኡዝ አካል የሆንኩ አይነት ስሜት ይሰማኛል ፡፡ ብዙ መገፋቶቼ እንደ ፊልም ፊቴ ላይ ይታዩኛል፡፡ ለምን ቤተሰቦች እኔን ብቻ ለአያቴ ሰጡኝ ? ለምን እኔ ብቻ የመንግስት ት/ቤት ተማርኩ ? ለምን አበባየሆሽ ሲጨፍሩ አላስገባም አሉኝ ? ለምን የአይን ፍቅር ያስያዘኝ ቢኒያም" እንደ እህቴ ነው እማይሽ አለኝ " እለፍ አላፍ ብዙ መገፋቶች አንድ ላይ ተባብረው ከምድር ሊያሰናብቱኝ እየገፉኝ ነው፡፡ አንድ ነገር ብቻ "ነይ ሉሊት ነይ" ይለኛል እኔ እወድሻለው እያለ ይቀጥረኛል ይጠራኛል ፡፡ ከሰፈራች ካለ አንድ የእንስሳ መድኃኒት መሸጫ መደብር ስሄድ ይታወሰኛል ፡፡ በመንገዴ ላይ ብዙ "እንደምን አደረሽ ሉሊት ?" እሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ ግን መጠየቃቸውን እንጂ የእኔን "የዝምታ መልስ በውስጡ በሰላም አይደለም እሚል" የሰማኝ አልነበረም ፡፡ ስንቱ "እቺ ኩራተኛ ?" ሲል አልፏል ? ተጓዝኩ ሞት ነይ ብሎ ወደ ቀጠረኝ ቦታ …. መመለስ የሌለው በሀገራችን በቀን 21 ሰው እራሱን እንደሚያጠፋ ያውቃሉ ? ለዚህ ችግር ምን እናድርግ ? September 10 የአለም እራስን ማጥፋት መከላከል ቀን አስመልክቶ የተከተበ ዶ/ር ቶፊቅ አብደላ (የአዕምሮ ህክምና እስፔሻሊስት )
Show all...
😢 6👍 5
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.