cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Super Boost-up

የማስታወቂያ አቅምዎንና በአረጀ በአፈጀ የማስተዋወቅ ብልሃት በከንቱ አያባከኑ ፤ እኛ ዘመኑን በሚመጥንና በተጠና የዲጂታል ማስታወቂያ ጥበብ ደንበኞቾ ጋር በእንርግጠኝነት እናደርሶታልን !! contact- 0908 222223  / 0914 949494

Show more
Advertising posts
132 689
Subscribers
-12924 hours
-1 0977 days
-5 15430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

“እሺ” እና “እምቢ” ሕይወት ተፈጥሯዊ ሂደቷን እንድትቀጥልና ሁኔታዎች በራሳቸው መስመር እየያዙ እንዲሄዱ መለማመድ የምንችላቸው ሁለት ልምምዶች አሉ፡፡ እነዚህ ልምምዶች ከለመድናቸው እጅግ ቀላል የሆኑ፣ ካላወቅንበት ግን የሚከብዱ ልምምዶች ናቸው፡፡  1.  ለተገቢው ነገር “እሺ” ማለት፡- በሕይወታችን መልካም ነገሮች እንዲገቡ በሩን የሚከፍተው ቁልፍ! በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንደሆነ ላመናችሁበት ነገር “እሺ” ማለት ሌሎች መልካም ነገሮች እየተወለዱ የሚሄዱበትን መስመር ይከፍትላችኋል፡፡ 2.  ተገቢ ላልሆነ ነገር “እምቢ” ማለት፡- በሕይወታችን ጤና-ቢስ ነገሮች እንዳይገቡ በሩን የሚዘጋው ቁልፍ!  በሚገባና በተረጋጋ መንፈስ አስባችሁበት ትክክለኛ እንዳልሆነ ላመናችሁት ነገር “እምቢ” ማለት ደግሞ በሕይወታችሁ መልካም ያልሆኑ ነገሮች እየተበራከቱ እንዳይሄዱ መንገዱን ይዘጋዋል፡፡ እነዚህ ሁለት ልምምዶች ፍርሃትን አልፎ መሄድን ይጠይቃሉ፡፡ በአንድ ጎኑ፣ “እሺ” ለምንለው ነገር ብቁ ባንሆንስ፣ ባይሳካስ፣ በኋላ ብጸጸትስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ “እምቢ” በማለታችን ምክንያት ችግር ቢደርስብንስ፣ እድል ቢያመልጠንስ፣ ሰዎች ቢቀየሙንስ . . . እና የመሳሰሉትን ፍርሃቶች ማስወገድን ይጠይቃል፡፡ 👉 🙏🏽☄️Super Boost-up Digital marketing and consultancy ☎️0908 222223 / 0914 949494 📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp 📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp 🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/ 📱ቲክቶክ👉 tiktok.com/@superboostup Telegram
Show all...
Super Boost-up

የማስታወቂያ አቅምዎንና በአረጀ በአፈጀ የማስተዋወቅ ብልሃት በከንቱ አያባከኑ ፤ እኛ ዘመኑን በሚመጥንና በተጠና የዲጂታል ማስታወቂያ ጥበብ ደንበኞቾ ጋር በእንርግጠኝነት እናደርሶታልን !! contact- 0908 222223  / 0914 949494

👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ሚዛናዊ ጥቅም “ሌላውን ቤተሰብ ለመጥቀም የራሳችሁን ቤተሰብ መጉዳት የለባችሁም፤ የራሳችሁን ቤተሰብ ለመጥቀም ደግሞ ሌላውን ቤተሰብ መጉዳት የለባችሁም” (Balanced Life Quotes) ፧ ለሌላው ሰው ጥቅም ስንል ራሳችንን እስከመጉዳት ድረሰ የምንደርስበት ሁኔታ ሊኖር የመቻሉ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከሚዛናዊነት አንጻር ሲታይ ግን ይህ መርህ ሁለገብ እውነትነት አለው! ፧ የሌላውን ነጋዴ ንግድ ለመደገፍ የራሳችሁን ንግድ መጣል የለባችሁም፤ የራሳችሁን ንግድ ለማሳደግ ደግሞ የሌላውን ሰው ንግድ መጣል የለባችሁም፡፡ ፧ የራሳችሁን አካባቢ ለመጥቀም የሌላውን ሰው አካባቢ መጉዳት የለባችሁም፤ የሌላውን ሰው አካባቢ ለመጥቀም የራሳችሁን አካባቢ መጉዳት የለባችሁም፡፡                መልካም ቀን🙏 ☄️Super Boost-up Digital marketing and consultancy ☎️0908 222223 / 0914 949494 📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp 📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp 🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/ 📱ቲክቶክ👉 tiktok.com/@superboostup Telegram
Show all...
🔥 1
ወደ አለንበት እንመለስ! (“ትኩረት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) ፓይለቱ አይሮፕላን ማብረር ከጀመረ ሰንበት ብሏል፡፡ ከአጠገቡ ገና ጀማሪ የሆነ ረዳት ፓይለት ተቀምጧል፡፡ የበረራውን ቅድመ-ዝግጅት ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ተመደበላቸው የከፍታ መጠንና አቅጣጫ ተነሱ፡፡ መብረር ከጀመሩ የተወሰኑ ሰኮንዶች አልፈዋል ሆኖም የዋናው ፓይለት አይኖች ወደታች በማየት ተተክሏል፡፡ የሚያየው አንድን አነስተኛ ሃይቅ ነው፡፡ በዚህ ሃይቅ ዙሪያ የአካባቢው ሰዎች ይርመሰመሳሉ፡፡ ውኃ የሚቀዳው፣ ከብቶቹን የሚያጠጣው፣ የሚዋኘው ሰው ወዲህና ወዲያ ይላል፡፡ የአይሮፕላኑ ከፍታ እየጨመረ ቢሄድም እንኳ የዋናው ፓይለት አይኖች ከዚህ ሃይቅ ላይ አለመነሳቱን አይቶ ረዳቱ፣ “ምነው ፈዝዘህ ቀረህ?” አለው፡፡ የዋናው ፓይለት ትካዜ የሞላበት መልስ፣ “አይ አንዳንድ ነገሮች ትዝ ብለውኝ ነው፡፡ ይህ አሁን አይተነው ያለፍነው ሃይቅ እኔ ያደኩበት አካባቢ ነው፡፡ ያን ጊዜ በዚያ ሃይቅ ዙሪያ ሆነን አሳ እናጠምድ ነበር፡፡ ታዲያ በዚያን ጊዜ አይሮፕላኖች ከላያችን ሲያልፉ ቀና በማለት፣ “መቼ ይሆን ከዚህ የሕይወት ሁኔታ ወጥቼ በአይሮፕላን የምበረው እያልኩ እመኝ ነበር፡፡ አሁን ይህ ምኞቴ ደርሶ በአይሮፕላን መብረር ብቻ ሳይሆን ማብረርም ከጀመርኩ ሰንብቻለሁ፡፡ አሁን ግን ሃይቁን ወደታች እያየሁ፣ መቼ ይሆን አሁን ካለሁበት የስራ አዙሪት ወጥቼ አሳ የማጠምደው እያልኩ ነው”፡፡ ያተኮረን የሕይወት ዘይቤ የተለማመዱ ሰዎች ዋናው አላማቸው አሁን ያሉበትን ስፍራና አሁን በእጃቸው የገባውን ነገር ተጠቅመውና በእለቱ ሁኔታ ደስተኛ በመሆን መድረስ የሚችሉበት ደረጃ ለመድረስ መጣጣራቸው ላይ ነው፡፡ ነገ መሆን የሚፈልጉትና ለማድረግ የሚያቅዱት ነገር ቢኖራቸውም አሁን ግን ባሉበት ሆነው የወቅቱን ሁኔታ ማሻሻልና በእጃቸው ባለው ነገር መደሰት እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ይህንን አትዘንጉ፡- “ወሳኙና ትኩረታችንን ልንጥልበት የሚገባው ነገር በእጃችን የሌለን ነገርና ያልተገኘንበት ስፍራ ላይ ሳይሆን በእጃችን ባለው ነገርና አሁን ባለንበት ስፍራ ላይ ሊሆን ይገባዋል” በሉ እንግዲህ ወደ አለንበት እንመለስ! 👉 🙏🏽☄️Super Boost-up Digital marketing and consultancy ☎️0908 222223 / 0914 949494 📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp 📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp 🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/ 📱ቲክቶክ👉 tiktok.com/@superboostup
Show all...
Super Boost-up

የማስታወቂያ አቅምዎንና በአረጀ በአፈጀ የማስተዋወቅ ብልሃት በከንቱ አያባከኑ ፤ እኛ ዘመኑን በሚመጥንና በተጠና የዲጂታል ማስታወቂያ ጥበብ ደንበኞቾ ጋር በእንርግጠኝነት እናደርሶታልን !! contact- 0908 222223  / 0914 949494

👍 3🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ የሕይወታችሁ የመጀመሪያው ቀን ቢሆን! “ዛሬ የሕይወታችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው!” ብትባሉ . . .  •  ምን በማድረግ ቀኑን ትጀምራላችሁ? •  ምንስ በማቆም ቀናችሁን ትጀምራላችሁ? •  የትኛውን ነገር በመርሳትና ወደኋላ በመተው ሕይወታችሁን ትጀምራላችሁ? •  ከየትኛው መርዛማ ግንኙነት በመለየት ወደፊት ለመሄድ ውሳኔን ታስተላልፋላችሁ? •  ለወደፊቱስ ምን አይነት እቅድ ታወጣላችሁ? •  እስካሁን ተጨንቃችሁ ምንም ለውጥ ያላመጣችሁትን የትኛውን ጭንቀት ለመተው ትወስናላችሁ? በሉ እንግዲያው፣ “ዛሬ ለተቀረው ዘመናችሁ የመጀመሪያው ቀን ነው”! “Today Is The First Day Of The Rest Of Your Life” - Charles Dederich መልካም የአዲስ ጅማሬ ቀን ይሁንላችሁ! 🙏🏽☄️Super Boost-up Digital marketing and consultancy ☎️0908 222223 / 0914 949494 📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp 📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp 🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/ 📱ቲክቶክ👉 tiktok.com/@superboostup
Show all...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
🌻🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼🌻 🌼 እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2017 በሰላም አደረሳቹአደረሰን !!! አዲሱ ዓመት የሰላም፣የፍቅርና የጤና የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን። 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Show all...
👍 2
00:16
Video unavailableShow in Telegram
4.84 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ድምጻችሁ ይስተካከል! ዛሬ . . . •  የስሜታዊነታችሁን ድምጽ ቀንሱ፣ የምክንያታዊነታችሁን ድምጽ ጨምሩ . . .። •  ሰዎች ስለእናንተ የሚያወሩትን ድምጽ መስማት ቀንሱ፣ እናንተው ስለራሳችሁ የምታውቁትን የእውነታ ድምጽ ጨምሩ . . .። •  ያልሆነውንና ያልተሳካውን ነገር ድምጽ ቀንሱ፣ የተሳካውንና መስመር የያዘውን ሁኔታ ድምጽ ጨምሩ . . .። •  ግራ የገባችሁንና እርግጠኛ ያልሆናችሁበትን ሁኔታ ድምጽ ቀንሱ፣ እርግጠኛ የሆናችሁበትን ሁኔታ ድምጽ ጨምሩ . . .። •  የማይቀበሏችሁንና የማይወዷችሁን ሰዎች የመከተል ድምጽ ቀንሱ፣ የሚወዷችሁንና የሚናፍቋችሁን ሰዎች ድምጽ ጨመር አድርጉ። ብልህ ሁኑ፤ በክፉው አትገኙ፤ አመዛዝኑ፤ የምታስቡትንና የምታምኑትን ለዩ! 🙏🏽☄️Super Boost-up Digital marketing and consultancy ☎️0908 222223 / 0914 949494 📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp 📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp 🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/ 📱ቲክቶክ👉 tiktok.com/@superboostup
Show all...
🔥 4👍 2
የግብ እውነታዎች “""""""""""""""""""‟ በሕይወታችሁ ልትሰሩት ከምችሏቸው ቀንደኛ ስህተቶች መካከል ከግብ ውጪ የመኖር ሁኔታ ተጠቃሽ ነው፡፡ የግብ መኖር ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ሁሉ የግብ አለመኖርም ብዙ ጉዳቶች አሉት፡፡ የግብ ጥቅሞች 1.  ትኩረት፡- ግብ ያለው ሰው የሚያስበውንም ሆነ የሚያደርገውን ነገር ከግቡ አንጻር ስለሚቃኘው የየእለት ኑሮውን በከፍተኛ ትኩረት የሚኖር ሰው የሚሆነው፡፡ 2.  አዎንታዊ ስሜትና አመለካከት፡- ግብ ያለው ሰው በየእለቱ አዎንታዊ ስሜት፣ አዎንታዊ አመለካከትና አዎንታዊ ጉልበት ያለው ሰው ነው፡፡ ማታ ሲተኛ የቀኑን የግብ ጉዞ ገምግሞ የመተኛት፣ ጠዋት ሲነሳ ደግሞ የእለቱን ግብ አስቦ የመውጣት ልምምዱ ከፍተኛ አዎንታዊነትን ይሰጠዋል፡፡ 3.  በራስ መተማመን፡- ግብ ያለው ሰው መቼ ከየት ተነስቶ አሁን የት እንደደረሳና መቼ የቱ ጋር እንደሚደርስ በሚገባ ስለሚውቅ ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን ያለው ሰው ነው፡፡ 4.  ቆጣቢነት፡- ግብ ያለው ሰው የለውን የጊዜ፣ የገንዘብ፣ የስሜትና የመሳሰሉትን ሃብቶቹን ሳያባክን በሚገባ የሚጠቀም ሰው ነው፡፡ 5.  ተፈላጊነት፡- ግብ ያለውን ሰው ያለውን የከበረና ዓላማ-መር ሕይወት ብዙዎች ሊጠቀሙበት ስሚፈልጉ ተፈላጊነቱን ይጨምረዋል፡፡ አምስቱ “በፍጹሞች”! 1.  በፍጹም ከግብ ውጪ አትኑሩ! - የሕይወታችሁን ዓላማ እወቁና ከዚያ አንጻር ግልጽ የሆነን ግብ አውጡ፡፡ 2.  በፍጹም “ቅንጥብጣቢ” ግቦችን ስትከተሉ አትኑሩ! - ከሕይወታችሁን ዋና ዓላማ ጋር የማይዛመዱ ጥቃቅንና የተበጫጨቁ ግቦችን ከመከተል ተጠበቁ፡፡ 3.  በፍጹም ሰውን የማስደሰት ግብ አታውጡ፡- የግችሁን መሳካት ሰዎችን (ቤተሰብ፣ የትዳር አጋር፣ ፍቅረኛ . . . ) ከማስደሰት ጋር ካነካካችሁት ከተደሰቱ ግባችሁን እንደመታችሁ፣ ካልተደሰቱ ደግሞ ግባችሁን እንዳልመታችሁ ይመስላችሁ በከንቱ ትደክማላችሁ፡፡ 4.  በፍጹም ቀን ገደብ ያልተቀመጠለት ግብ አታውጡ! - የቀን ገደብ የሌለው ግብ መነሳሳት የማይሰጥ ከመሆኑም በላይ መሳካቱና አለመሳካቱን መመዘኛ ነጥብ የሌለው ግብ ነው፡፡ 5.  በፍጹም ከግባችሁ አትመለሱ! - ግብ ካለ እንቅስቃሴ አለ፤ እንቅስቃሴ ካለ ደግሞ ሁል ጊዜ እንቅፋት አለ፡፡ ወደግባችሁ ስትሄዱ እንቅፋት ሲያጋጥማችሁና ስትወድቁ እንደገና ተነሱና ቀጥሉ፡፡ 👉በየቀኑ ጠቃሚ መልእክቶችን፣ መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ በነፃ የምታገኟቸው አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች፣ የቢዝነስ ሃሳቦች እና የገንዘብና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ። ☄️Super Boost-up Digital marketing and consultancy ☎️0908 222223 / 0914 949494 📱ቴሌግራም👉 https://t.me/Superboostupp 📱ፌስቡክ ገጽ👉 https://www.facebook.com/SuperBoostUp?mibextid=NTRm0r7WZyOdZZsz https://www.facebook.com/SuperBoostUp 🌐ዌብሳይት 👉 https://superboostup.com/ 📱ቲክቶክ👉 tiktok.com/@superboostup
Show all...
Super Boost-up

የማስታወቂያ አቅምዎንና በአረጀ በአፈጀ የማስተዋወቅ ብልሃት በከንቱ አያባከኑ ፤ እኛ ዘመኑን በሚመጥንና በተጠና የዲጂታል ማስታወቂያ ጥበብ ደንበኞቾ ጋር በእንርግጠኝነት እናደርሶታልን !! contact- 0908 222223  / 0914 949494

🔥 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.