cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

Advertising posts
286
Subscribers
-224 hours
+227 days
+4830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የቴፒ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2016 ዕቅድ አፈጻጸምና የ2017 ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። በመድረኩ የፓርቲዉን የ2016 ዕቅድ አፈጻጸምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡት በጽህፈት ቤቱ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ካሣሁን አባተ እንደገለጹት በቴፒ ከተማ በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በመሠረተ ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በጤና፣ በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች ህብረተሰቡን በማስተባበር ጭምር የተሻሉ ተግባራት መከናወናቸዉን ገልጸዋል። ለአብነትም በህዝብ ተሳትፎ ከከተማዉ የተሰበሰበዉን 2 ነጥብ 3 ሚልዮን ብር በላይና በህዝብ ተሳትፎ በወባ መከላከል ዙሪያ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር የተከናወኑትን ተግባራት ጠቅሰዋል። በተያያዘም በከተማዉ ለሚገኙና ለተቸገሩ ተማሪዎች የደብተርና እስክብርቶ ድጋፍ ከመድረኩ ተበርክቶላቸዋል። ዘጋቢ ጌትነት ገረመዉ ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በተያዘው የበጀት ዓመት ፈጣን እና አስተማማኝ አገልግሎት በማስፋፋት 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ለማግኘት መታቀዱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል፡፡ ለቴክኖሎጂ ግንባታ ማስፋፊያ እና ለአዳዲስ አገልግሎቶች ማስጀመሪያ 1 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ገልፀዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ በ15 ከተሞች የ5ኛ ትውልድ ኔትዎርክ እና የ4ኛ ትውልድ ኔትወርክ አገልግሎት ያላገኙ አካባቢዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ እንደሚደረግ ነው የገለፁት፡፡ የዲጂታል ቴሌኮም መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ኢትዮጵያን ለውጭ ኢንቨስትመንት ተመራጭ ሀገር ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞቹን ቁጥርም 83 ሚሊዮን ለማድረስ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል። #Ebc ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት መድረክ በቴፒ ከተማ እያካሄደ ነው። በውይይት መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አስታውሰኝ አይሞ ፖሊስ የህብረተሰቡን የሰላም ፍላጎት በማርካትና በ2016 በጀት ዓመት የተለያዩ የርፎርም ስራዎችን በመስራት ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል። በመድረኩ የሁሉም መዋቅር የፖሊስ አባላት የፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች የሁሉም መዋቅር አስተዳዳረዎችና ከንቲባዎች የሀይማኖት አባቶች ከዞኑ ምክር ቤትና አስተዳደር ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ስል የዘገበው የዞኑ መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤ/ት ነው። ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ በመርህ ላይ የተመሰረተ ምላሽ ትሰጣለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስከረም 9/2017 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ መስመር ለማሳት የሚሰነዘሩ አስተያየቶችን በሰከነ እና መርህን በተከተለ መልኩ ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ገለጹ። በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ተከትሎ በአንዳንድ አካላት ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ንግግሮች እየተደመጠ መሆኑን የገለፁት ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ በሰከነ እና መርህን በተከተለ መልኩ ምላሸ ትሰጣለች ብለዋል። 79ኛው የተባበሩ መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 14 እስከ 20 በኒውዮርክ ከተማ ይካሄዳል። #walta ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የአስክሬን ሽኝት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የሽኝት መርሐ-ግብሩ ሲጠናቀቅም የቀብር ስርዓቱ በብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ዛሬ 8 ሰዓት ላይ ይፈጸማል። ፕሮፈሰሩ በገጠማቸው የልብ ህመም በሀገር ውስጥ እና በኬኒያ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ማክሰኞ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡ በኢንስቲትዩቱ ለተመራማሪዎች የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና በማመቻቸት ሙያቸውን እንዲያሳድጉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ሲሆን፥ ጀማሪ ተመራማሪዎችም አቅማቸውን አጎልብተው ትርጉም ያለው የምርምር ስራ እንዲሰሩ ጥረት ማድረጋቸው ይነገራል፡፡ ሁሉም የምርምር ስራዎች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ከማስቻል ባለፈ የምርምር ውጤቶች ለህብረተሰቡ እንዲደርሱና የሚመለከተው አካልም እንዲጠቀምባቸው በማድረግ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንደነበራቸው ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። #fana ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
11ኛው የምስራቅ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ኮንፈረንስ መካሄድ ጀመረ፡፡ ኮንፈረንሱ "የግልግል ዳኝነት በአዲሱ ዘመን” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡ የግልግል ዳኝነት ኮንፈረንሱን ፍትህ ሚኒስቴር እና ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት አፍሪካ በጋራ ያዘጋጁት መሆኑን ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በኮንፈረንሱ ላይ የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የመንግስት ባለድርሻ አካላት፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ከተለያዩ ሀገራት ተሳታፊ ሆነዋል። መድረኩ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎችን፣ የመንግስት ተወካዮችንና ባለድርሻ አካላትን የሚያገናኝ ሲሆን በአፍሪካ ቀጠናዊ ትስስርና እድገት ዙሪያ ምክክሮችና ገለጻዎች ይደረግበታል ተብሏል። #fana ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
ለመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት አከባበር 16 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ለማስተባበር መዘጋጀታቸውን የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር አስታወቀ። በመስከረም ወር በደማቅ ሥነ-ሥርአት ከሚከበሩት የአደባባይ በዓላት መካከል የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ይጠቀሳሉ። በእነዚህ በዓላት በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች፣ የበዓሉ አክባሪዎችና ታዳሚዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡ በዚሁ መሰረት ለበዓላቱ ሰላማዊ የአከባበር ህደት ለአቀባበልና መስተንግዶ በርካታ የመዲናዋ ወጣቶች መዘጋጀታቸውን የአዲስ አበባ ወጣቶች ማኅበር ዋና ጸሐፊ ይሁነኝ መሀመድ ተናግሯል፡፡ በሁነቱ ላይ እንግዶችን ለመቀበል፣ ለማስተባበርና ለማስተናገድ 16 ሺህ የማህበሩ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ዝግጁ መሆናቸውንም ነው ያመላከተው፡፡ #fana ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ ዝግጅት እየተደረገ ነው - ፌዴራል ፖሊስ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ እና ደኅንነት አካላት ጋር ሀገራዊ የጸጥታ ሁኔታዎችን ገምግሟል። በቀጣይም በአደባባይ በከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር የሚከበሩት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ ከወዲሁ ጠንካራ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተነስቷል፡፡ ለበዓለቱ በርካታ የጸጥታ ሃይል እንደሚሰማራና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ መጠቀሱን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል። #fana ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የአንድራቻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2017 የትምህርት ዘመን ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ ኮሌጁ በትምህርት ዘመኑ በመደበኛና በማታ መርሐ ግብሮች በተለያዩ የሙያ መስኮች ከደረጃ 1_4 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን ነው የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ደሳለኝ የተናገሩት ። ከመስከረም 6/2017 ዓ/ም እስከ መስከረም 19/2017 ዓ/ም ድረስ ብቻ የአዳዲስ ተማሪዎች የቅበላ ምዝገባ የሚካሄድ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ካሳሁን ተቋሙ አዲስ ባስገነባው የመማሪያ ክፍልና በአስተዳደር ሰራተኞች ቢሮ የመማር ማስተማር ስራውን እንደሚያከናውን ጨምሮ ገልጸዋል የዘገበው የአንድራቻ ወረዳ መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤ/ት ነው። ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የማሻ ከተማ ምክር ቤት ሲያካህድ የነበረዉን 2ኛ ዙር 11ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለዩ ዉሳኔዎችን በማፅደቅ ተጠናቅቋል። በቀጣይ ለሚሰሩ ተግባራቶችና የከተማይቱን ዕድገት በሚያፋጥኑትና የህህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ የበለጠ መስራት እንዳለበት ተገልጿል ። ከፀደቁት ዉሳኔዎች መካከል የ2017 ዓም የከተማ አስተዳደሩን ጠቋሚ ዕቅድ፣ የ2017 ዓም የከተማ አስተዳደር ዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚሆን 187,666,203 ብር ረቂቅ በጀትና የማሻ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤት አባላት ቀርበዉ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበት የፀደቁ ሲሆን የተለያዪ የከተማ አስ/ር ስር ለሚገኙት ጽ/ቤቶች ሹመት ቀርቦ በማጵደቅ ጉባኤው ተጠናቋል። ዘጋቢ ግሪማ ጮሪቶ ለተጨማሪ መረጃ ከታች ባሉት ድረ ገጾች ይከታተሉን! Facebook=https://www.facebook.com/profile.php?id=61552831883490 telegram =https://t.me/mashaFm103.8 tiktok=https://www.tiktok.com/@masha_fm103.8?_t=8h8vFNn1ToE&_r=1 YouTube=https://youtube.com/@MashaFM-op5hb?si=4gRo1QtHJYQoGZqY2q Instagram=https://instagram.com/mashafm2023?igshid=MWFsc2NqcTJ2cWJhcg== Twitter =https://twitter.com/masha_fm98 WhatsApp= https://whatsapp.com/dl/ website:www.mashafm.gov.et ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.