cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

እምነ እምነ ንዒ(TserhaAryam)

እንኳን ደህና መጣችሁ ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርዓትን የጠበቁ ጽሁፎችን፣ መጽሐፍትን እና ትምህርቶችን የሚያገኙበት ነው። https://t.me/yeberehan_enat https://t.me/yeberehan_enat https://t.me/yeberehan_enat "❤ Only orthodox tewahdo❤" "❤ Only orthodox tewahdo❤"

Show more
Advertising posts
208
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ደብረ - ዘይት የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ፡24፤ 1፤ኢየሱስም፡ከመቅደስ፡ወጥቶ፡ኼደ፥ደቀ፡መዛሙርቱም፡የመቅደሱን፡ግንቦች፡ሊያሳዩት፡ቀረቡ። 2፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፦ይህን፡ዅሉ፡ታያላችኹን፧እውነት፡እላችዃለኹ፥ድንጋይ፡በድንጋይ፡ላይ፡ሳይፈርስ፡ በዚህ፡አይቀርም፡አላቸው። 3፤ርሱም፡በደብረ፡ዘይት፡ተቀምጦ፡ሳለ፥ደቀ፡መዛሙርቱ፡ለብቻቸው፡ወደ፡ርሱ፡ቀርበው፦ንገረን፥ይህ፡ መቼ፡ይኾናል፧የመምጣትኽና፡የዓለም፡መጨረሻ፡ምልክቱስ፡ምንድር፡ነው፧አሉት። 4፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ማንም፡እንዳያስታችኹ፡ተጠንቀቁ። 5፤ብዙዎች፦እኔ፡ክርስቶስ፡ነኝ፡እያሉ፡በስሜ፡ይመጣሉና፤ብዙዎችንም፡ያስታሉ። 6፤ጦርንም፡የጦርንም፡ወሬ፡ትሰሙ፡ዘንድ፡አላችኹ፤ይህ፡ሊኾን፡ግድ፡ነውና፥ተጠበቁ፥አትደንግጡ፤ዳሩ፡ ግን፡መጨረሻው፡ገና፡ነው። 7፤ሕዝብ፡በሕዝብ፡ላይ፡መንግሥትም፡በመንግሥት፡ላይ፡ይነሣልና፥ራብም፡ቸነፈርም፡የምድርም፡መናወጥ፡ በልዩ፡ልዩ፡ስፍራ፡ይኾናል፤ 8፤እነዚህም፡ዅሉ፡የምጥ፡ጣር፡መዠመሪያ፡ናቸው። 9፤በዚያን፡ጊዜ፡ለመከራ፡አሳልፈው፡ይሰጧችዃል፡ይገድሏችኹማል፥ስለ፡ስሜም፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ የተጠላችኹ፡ትኾናላችኹ። 10፤በዚያን፡ጊዜም፡ብዙዎች፡ይሰናከላሉ፡ርስ፡በርሳቸውም፡አሳልፈው፡ይሰጣጣሉ፥ርስ፡በርሳቸውም፡ይጣላሉ፤ 11፤ብዙ፡ሐሰተኛዎች፡ነቢያትም፡ይነሣሉ፡ብዙዎችንም፡ያስታሉ፤ 12፤ከዐመፃም፡ብዛት፡የተነሣ፡የብዙ፡ሰዎች፡ፍቅር፡ትቀዘቅዛለች። 13፤እስከ፡መጨረሻ፡የሚጸና፡ግን፡ርሱ፡ይድናል። 14፤ለአሕዛብም፡ዅሉ፡ምስክር፡እንዲኾን፡ይህ፡የመንግሥት፡ወንጌል፡በዓለም፡ዅሉ፡ይሰበካል፥በዚያን፡ ጊዜም፡መጨረሻው፡ይመጣል። 15፤እንግዲህ፡በነቢዩ፡በዳንኤል፡የተባለውን፡የጥፋትን፡ርኵሰት፡በተቀደሰችው፡ስፍራ፡ቆሞ፡ስታዩ፥አንባቢው፡ ያስተውል፥ 16፤በዚያን፡ጊዜ፡በይሁዳ፡ያሉት፡ወደ፡ተራራዎች፡ይሽሹ፥ 17፤በሰገነትም፡ያለ፡በቤቱ፡ያለውን፡ሊወስድ፡አይውረድ፥ 18፤በዕርሻም፡ያለ፡ልብሱን፡ይወስድ፡ዘንድ፡ወደ፡ዃላው፡አይመለስ። 19፤በዚያችም፡ወራት፡ለርጕዞችና፡ለሚያጠቡ፡ወዮላቸው። 20፤ነገር፡ግን፥ሽሽታችኹ፡በክረምት፡ወይም፡በሰንበት፡እንዳይኾን፡ጸልዩ፤ 21፤በዚያን፡ጊዜ፡ከዓለም፡መዠመሪያ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያልኾነ፡እንግዲህም፡ከቶ፡የማይኾን፡ ታላቅ፡መከራ፡ይኾናልና። 22፤እነዚያ፡ቀኖችስ፡ባያጥሩ፡ሥጋ፡የለበሰ፡ዅሉ፡ባልዳነም፡ነበር፤ነገር፡ግን፥እነዚያ፡ቀኖች፡ ስለተመረጡት፡ሰዎች፡ያጥራሉ። 23፤በዚያን፡ጊዜ፡ማንም፦እንሆ፥ክርስቶስ፡ከዚህ፡አለ፡ወይም፦ከዚያ፡አለ፡ቢላችኹ፡አትመኑ፤ 24፤ሐሰተኛዎች፡ክርስቶሶችና፡ሐሰተኛዎች፡ነቢያት፡ይነሣሉና፥ቢቻላቸውስ፡የተመረጡትን፡እንኳ፡እስኪያስቱ፡ ድረስ፡ታላላቅ፡ምልክትና፡ድንቅ፡ያሳያሉ። 25፤እንሆ፥አስቀድሜ፡ነገርዃችኹ። 26፤እንግዲህ፦እንሆ፥በበረሓ፡ነው፡ቢሏችኹ፥አትውጡ፤እንሆ፥በዕልፍኝ፡ነው፡ቢሏችኹ፥አትመኑ፤ 27፤መብረቅ፡ከምሥራቅ፡ወጥቶ፡እስከ፡ምዕራብ፡እንደሚታይ፥የሰው፡ልጅ፡መምጣት፡እንዲሁ፡ይኾናልና፤ 28፤በድን፡ወዳለበት፡በዚያ፡አሞራዎች፡ይሰበሰባሉ። 29፤ከዚያች፡ወራትም፡መከራ፡በዃላ፡ወዲያው፡ፀሓይ፡ይጨልማል፥ጨረቃም፡ብርሃኗን፡ አትሰጥም፥ከዋክብትም፡ከሰማይ፡ይወድቃሉ፥ 30፤የሰማያትም፡ኀይላት፡ይናወጣሉ።በዚያን፡ጊዜም፡የሰው፡ልጅ፡ምልክት፡በሰማይ፡ይታያል፥በዚያን፡ ጊዜም፡የምድር፡ወገኖች፡ዅሉ፡ዋይ፡ዋይ፡ይላሉ፥የሰው፡ልጅንም፡በኀይልና፡በብዙ፡ክብር፡በሰማይ፡ደመና፡ ሲመጣ፡ያዩታል፤ 31፤መላእክቱንም፡ከታላቅ፡መለከት፡ድምፅ፡ጋራ፡ይልካቸዋል፥ከሰማያትም፡ዳርቻ፡እስከ፡ዳርቻው፡ከአራቱ፡ ነፋሳት፡ለርሱ፡የተመረጡትን፡ይሰበስባሉ። 32፤ምሳሌውንም፡ከበለስ፡ተማሩ፤ጫፏ፡ሲለሰልስ፡ቅጠሏም፡ሲያቈጠቍጥ፥ያን፡ጊዜ፡በጋ፡እንደ፡ቀረበ፡ ታውቃላችኹ፤ 33፤እንዲሁ፡እናንተ፡ደግሞ፡ይህን፡ዅሉ፡ስታዩ፡በደጅ፡እንደ፡ቀረበ፡ዕወቁ። 34፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ይህ፡ዅሉ፡እስኪኾን፡ድረስ፡ይህ፡ትውልድ፡አያልፍም። 35፤ሰማይና፡ምድር፡ያልፋሉ፥ቃሌ፡ግን፡አያልፍም። 36፤ስለዚያች፡ቀንና፡ስለዚያች፡ሰዓት፡ግን፡ከአባት፡ብቻ፡በቀር፡የሰማይ፡መላእክትም፡ቢኾኑ፡ልጅም፡ ቢኾን፡የሚያውቅ፡የለም። 37፤የኖኅ፡ዘመን፡እንደ፡ነበረ፡የሰው፡ልጅ፡መምጣት፡እንዲሁ፡ይኾናልና። 38፤በዚያች፡ወራት፡ከጥፋት፡ውሃ፡በፊት፥ኖኅ፡ወደ፡መርከብ፡እስከገባበት፡ቀን፡ድረስ፥ሲበሉና፡ሲጠጡ፡ ሲያገቡና፡ሲጋቡም፡እንደ፡ነበሩ፥ 39፤የጥፋት፡ውሃም፡መጥቶ፡ዅሉን፡እስከወሰደ፡ድረስ፡እንዳላወቁ፥የሰው፡ልጅ፡መምጣት፡ደግሞ፡እንዲሁ፡ ይኾናል። 40፤በዚያን፡ጊዜ፡ኹለት፡ሰዎች፡በዕርሻ፡ይኾናሉ፤አንዱ፡ይወሰዳል፡አንዱም፡ይቀራል፤ 41፤ኹለት፡ሴቶች፡በወፍጮ፡ይፈጫሉ፤አንዲቱ፡ትወሰዳለች፡አንዲቱም፡ትቀራለች። 42፤ጌታችኹ፡በምን፡ሰዓት፡እንዲመጣ፡አታውቁምና፡እንግዲህ፡ንቁ። 43፤ያን፡ግን፡ዕወቁ፤ባለቤት፡ከሌሊቱ፡በየትኛው፡ክፍል፡ሌባ፡እንዲመጣ፡ቢያውቅ፡ኖሮ፥በነቃ፡ቤቱም፡ ሊቈፈር፡ባልተወም፡ነበር። 44፤ስለዚህ፥እናንተ፡ደግሞ፡ተዘጋጅታችኹ፡ኑሩ፥የሰው፡ልጅ፡በማታስቡበት፡ሰዓት፡ይመጣልና። 45፤እንኪያስ፡ምግባቸውን፡በጊዜው፡ይሰጣቸው፡ዘንድ፡ጌታው፡በቤተ፡ሰዎች፡ላይ፡የሾመው፡ታማኝና፡ ልባም፡ባሪያ፡ማን፡ነው፧ 46፤ጌታው፡መጥቶ፡እንዲህ፡ሲያደርግ፡የሚያገኘው፡ያ፡ባሪያ፡ብፁዕ፡ነው፤ 47፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ባለው፡ዅሉ፡ላይ፡ይሾመዋል። 48፤ያ፡ክፉ፡ባሪያ፡ግን፦ጌታዬ፡እስኪመጣ፡ይዘገያል፡ብሎ፡በልቡ፡ቢያስብ፥ 49፤ባልንጀራዎቹን፡ባሪያዎች፡ሊመታ፡ቢዠምር፥ከሰካሮችም፡ጋራ፡ቢበላና፡ቢጠጣ፥ 50፤የዚያ፡ባሪያ፡ጌታ፡ባልጠበቃት፡ቀን፡ባላወቃትም፡ሰዓት፡ይመጣል፥ 51፤ከኹለትም፡ይሰነጥቀዋል፥ዕድሉንም፡ከግብዞች፡ጋራ፡ያደርግበታል፤በዚያ፡ልቅሶና፡ጥርስ፡ማፋጨት፡ ይኾናል።
Show all...
እምነ እምነ ንዒ (እናታችን ነይ ነይ) 🙏🙏🙏

በዚህ ግሩፕ * የቅዱሳን አባቶች ምክር * መዝሙር *ትምህርቶች *መፃህፍት እና *አስተማሪ ታሪኮችን ያገኙበታል። *ሀሳብ መስጠት ፣ ጥያቄ መጠየቅ ፣ አስተማሪ ነገሮችን መልቀቅ መወያየት ይቻላል ።

https://t.me/yeberehanenat

https://t.me/yeberehanenat

"❤ Only orthodox tewahdo❤" "❤ Only orthodox tewahdo❤"

+ ለምን ትቀናለህ? +  በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡ አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡ ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው:: ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡   ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡ ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡   ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ  አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡ ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡ የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡ ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡ የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡ ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡ ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡ ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡  በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው፡፡ ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡ ‘በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13 ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ አለታ ወንዶ ኢትዮጵያ ጥር 5 2013 ዓ.ም. መነሻ ሃሳብ:- የአንድ በቅናት ጦስ ሊያበሩ ሲችሉ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ቤተሰቦች ታሪክ ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! https://t.me/yeberehan_enat https://t.me/yeberehan_enat
Show all...
እምነ እምነ ንዒ(TserhaAryam)

እንኳን ደህና መጣችሁ ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርዓትን የጠበቁ ጽሁፎችን፣ መጽሐፍትን እና ትምህርቶችን የሚያገኙበት ነው።

https://t.me/yeberehan_enat

https://t.me/yeberehan_enat

https://t.me/yeberehan_enat

"❤ Only orthodox tewahdo❤" "❤ Only orthodox tewahdo❤"

ሚስትህን አትናቃት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በቤት ውስጥ በሚስትህ ምክንያት አንድ ደስ የማያሰኝ ስሕተት ቢፈጠር ‘አይዞሽ’ ልትላት ይገባል እንጂ ኀዘኗን ልታባብሰው አይገባህም፡፡ ኹሉንም ነገር ብታጣም እንኳን ከጎኗ ኹን፡፡ እርግጥ ነው ለባልዋ ደንታ ከሌላት ሚስት በላይ ምንም አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ በእናንተ መካከል ጸብ ክርክር ከሚፈጥር የሚስትህ ጥፋት በላይ አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ ስለዚሁ ዋና ምክንያት ግን ለእርስዋ ያለህ ፍቅር እጅግ ጽኑዕ ሊኾን ይገባዋል፡፡ እኛ ክርስቲያኖች አንዳችን የሌላችንን ሸክም እንድንሸከም የታዘዝን ከኾነ፥ ከዚህ በላይ ደግሞ አንተ የሚስትህን ሸክም ልትሸከም ይገባሃል፡፡ በመኾኑም ድኻ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት በፍጹም አትናቃት፡፡ ሰነፍ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት አስተካክላት እንጂ አታዋርዳት፡፡ እርስዋ አካልህ ነችና፤ አንተም አካልዋ ነህና፤ አንድ አካል ናችሁና፡፡ ‘ክፉ ነች፤ ቁጡ ነች፤ ራስዋን መቈጣጠር የማትችል ግልፍተኛ ነች’ ልትለኝ ትችላለህ፡፡ ስለዚሁ ጠባይዋ እጅግ ልታዝን ይገባሃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ጠባይ ያርቅላት ዘንድ ጸልይላት እንጂ አንተም መልሰህ አትቈጣት፡፡ ልታሳምናት ሞክር እንጂ ወደ ሙግት አትግባ፡፡ እነዚህን ክፍተቶችዋን ከእርስዋ ለማራቅ ኹሉንም ዓይነት በጎ ዘዴዎችን ተጠቀም፡፡” “ይህን እንደማድረግ ሚስትህን የምትመታትና የምታሠቃያት ከኾነ ግን እነዚህ ሕመሞችዋ እንዲድኑ አታደርጋቸውም፡፡ ኃይለኝነት የሚወገደው በጭካኔ ሥራ ሳይኾን በየውሃት ነውና፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም ሚስትህ በየውሃት ስትይዛት ከእግዚአብሔር ዘንድ ሹመት ሽልማት እንደምታገኝ አስታውስ፡፡ ከአሕዛብ ፈላስፎች አንዱ ክፉ፣ መራራና ሥርዓት የለሽ ሚስት ነበረችው ይባላል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ለምን ከእርስዋ ጋር እንደሚኖር (ለምን እንደማይፈታት) በተጠየቀ ጊዜ ጠቢቡ ሰው በገዛ ቤቱ ውስጥ የፍልስፍና ትምህርት ቤት እንዳለው ነበር የመለሰው፡፡ ‘ዕለት ዕለት በዚህ ትምህርት ቤት የምማር ከኾነ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ታጋሽ እኾናለሁ’ ነበር ያለው፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እኔ ግን መላእክት እንዲያውም ከእነርሱም በላይ የዋሃን ኾነን እግዚአብሔርን እንድንመስለው ከታዘዝነው ከእኛ ይልቅ አረማውያን ሰዎች ጠቢባን ኾነው ስመለከታቸው ፈጽሜ አለቅሳለሁ፡፡ ያ ፈላስፋ ሚስቱን እንዳይፈታት ምክንያት የኾነው የእርስዋ ክፉ ጠባይ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ‘ይህ ፈላስፋ ይህቺን ሴት ሚስት ትኾነው ዘንድ ያገባት ይህን ለማግኘት ብሎ ነው’ ይላሉ፡፡ አንተም ዕጮኛ ስትመርጥ በምርጫህ ተሳስተህ ክፉ ሚስት አግብተህ ከኾነ (ብታገባ) ቢያንስ ቢያንስ ይህን አረማዊ ፈላስፋ አብነት አድርገው፡፡ ሚስትህን ለማስተካከል የተቻለህን አድርግ፡፡ ክፋትዋን በሌላ ክፋት አትመልስላት፡፡ ከእርስዋ ጋር ኾነህ የትዳርን ቀንበር የምትሸከም ከኾነ ሌሎች ብዙ ረብ ጥቅሞችንም ታገኛለህና፤ መንፈሳዊ ተግባራትን ለመተግበር ቀላል ይኾንልሃልና፡፡” ኢየሱስ ክርስቶስ፡- “ጨለማን ያሳደደው ብርሃን ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና የማይነዋወጥ መሰረትና የማይፈርስ ግንብ የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማህደር የለዘበ ቀንበርና የቀለለ ሽክም እርሱ ለአባቱ ሃይል ጥበቡም የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ “ለሁሉ ያስባል ፡፡ ሁሉንም ያጠግባል ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል፡፡ የተዘጉ መስኮቶችን ይከፍታል ህሙማንን ይሰማቸዋል፡፡ የተደፈነችውን ጆሮ እንድትሰማ ያደርጋል፡፡ ከሰውነት የለምፅን ልብሶች ገፍፎ የስጋን መጎናፀፊያ ያለብሳል፡፡ የደረቀውን የእጅ ክንድ ያቀናል፣ የአንካሳውን እግር እንዲሄድ ያደርጋል ነፍስን ወደ ሕዋስዋ ይመልሳታል መንፈስንም በማደሪያዋ ያኖራታል፡፡ አለቆች ባሏቸው አጋንንት የእርያን መንጋ ያሰጥማል ከደከመችውም ሰውነት ደዌን ያርቃል፡፡ “ከክንፍህ የፅድቅ ፀሃይና የጥቅም ምንጭ የሚወጣ የፅድቅ ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ ጌትነትና ክብር ምስጋናም ይገባሃል ለዘላለሙ አሜን፡፡” https://t.me/yeberehan_enat https://t.me/yeberehan_enat
Show all...
እምነ እምነ ንዒ(TserhaAryam)

እንኳን ደህና መጣችሁ ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርዓትን የጠበቁ ጽሁፎችን፣ መጽሐፍትን እና ትምህርቶችን የሚያገኙበት ነው።

https://t.me/yeberehan_enat

https://t.me/yeberehan_enat

https://t.me/yeberehan_enat

"❤ Only orthodox tewahdo❤" "❤ Only orthodox tewahdo❤"

Show all...
እምነ እምነ ንዒ(TserhaAryam)

እንኳን ደህና መጣችሁ ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርዓትን የጠበቁ ጽሁፎችን፣ መጽሐፍትን እና ትምህርቶችን የሚያገኙበት ነው።

https://t.me/yeberehan_enat

https://t.me/yeberehan_enat

https://t.me/yeberehan_enat

"❤ Only orthodox tewahdo❤" "❤ Only orthodox tewahdo❤"

6_አዲስ_ዝማሬ”#ደብረዘይት”_“ዝም_አይልም_አምላክ_“_abel_begena_zem_aylem.mp38.20 MB
4_አዲስ_ዝማሬ_'ለድሆች_ወንጌልን”_abel_begena_ledhoch_wengelen.mp38.31 MB
5_አዲስ_ዝማሬ_“መፃጉዕ”_abel_begena_metsague.mp36.39 MB
2_አዲስ_ዝማሬ_“እመኑ_በልጁ”_abel_begena_“emenu_beliju”.mp35.81 MB
3_አዲስ_ዝማሬ_“ያከብርዋ”_abel_begena_“yakeberewa_“.mp36.81 MB
፯.ቀራንዮ (የትምወርቅ ሙላት).mp310.40 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.