cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Al-Jazeera Amharic [አልጀዚራ] ️

This is Official Ethiopian - Aljazeera News Channel

Show more
Advertising posts
259
Subscribers
+224 hours
+27 days
+1230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 5 ጀምሮ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ አንደሚጀምር ገለፀ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሱዳኗ የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ዕለታዊ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ መጀመሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሀገራት ያላትን የመዳረሻ ቁጥር እንደሚያሳድግ ጠቁሟል፡፡ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድና ቱሪዝም ትስስር በማጎልበት የቀጣናውን የኢኮኖሚ እድገት እንደሚጠናክርም የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ አየር መንገዱ ወደ በናይሮቢ የጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሠራተኞች በስራ ማቆም አድማ ላይ በመሆናቸው ወደ ናይሮቢ የሚያደርገው በረራ እየተከናወነ እለመሆኑን በትላንትናው ዕለት አስታውቋል።ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንድሚገኝ የገለጸው አየር መንገዱ በክስተቱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቋል።
Show all...
1
በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እየተጣለባቸው እንደሆነ አስመጪዎች ተናገሩ! የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እየተጣለባቸው በመሆኑ፤ በሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት ለማሰራጨት በሚያደርጉት ጥረት ላይ እንቅፋት እየሆነባቸው እንደሚገኝ አስመጪዎች ተናገሩ።የነዳጅ ተሽከርካሪዎች ወደ ሐገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከሉን ተከትሎ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች በብዛት እንዲገቡ ለማበረታታት ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳይጣልባቸው መደረጉ ይታወሳል። ቅሬታቸውን ለአሐዱ የገለጹት የተሽከርካሪ አስመጪዎች ግን፤ መመሪያው ተግባራዊ እየተደረገ እንዳልሆነ ይናገራሉ።‹‹ከገንዘብ ሚንስቴር መመሪያ ሳይተላለፍ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንድንከፍል እየተገደድን ነው›› የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጉምሩክ ቅርንጫፍ የደረሱ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ ካልከፈሉ እንደማይወጡ ተነግሯቸዋል ብለዋል። አክለውም በቅርቡ የጸደቀው የተጨማሪ ዕሴት ታክስ አዋጅ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የሚመለከት አንቀጽ እንዳልተካተተበት ነግረውናል።ይህንኑ አስመልክቶ አሐዱ ያነጋገረቻቸው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚንስቴር ምንጮች፤ ሙሉ ለሙሉ በውጭ ሀገር ተገጣጥመው ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ እና በከፊል ተገጣጥመው የሚገቡት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ አነስተኛ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደሚጣል የተናገሩ ሲሆን፤ ነገር ግን ተሽከርካሪዎቹ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ከታክሱ ነጻ እንደሆኑ ገልጸዋል። ይህም በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የተደረገው የቀረጥ ማበረታቻ የባለሀብቱን ተነሳሽነትና የሀገሪቷን የታዳሽ ኃይል አቅርቦት ለማሳደግ እንደሚረዳ የታመነበት ሲሆን የአየር ብክለትን ለመቀነስም የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።
Show all...
ለማይክ ሀመር “የፕሪቶርያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ አለመተግበር በቀጠናው ቀውስ የሚያስከትል ከፍተኛ መዘዝ እንደሚኖረው ነግሬያቸዋለሁ” - ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የአሜሪካን መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም ተገናኝተው በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አተገባበር ዙሪያ መምከራቸውን አስታወቁ።ፕሬዝዳንት ጌታቸው በይፋዊ የኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ከማይክ ሀመር ጋር በነበረኝ ቆይታ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ አለመተግበሩ በቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ቀውስ የሚያስከትል መዘዝ ይዞ ሊመጣ ይችላል ብየ ነግሬያቸዋለሁ ብለዋል። “አሁን ያለው ሁኔታ ከአሁን በኋላ ሊቀጥል እንደማይችል እና ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ አለመተግበሩ በአካባቢው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ከፍተኛ መዘዝ እንደሚኖረው አፅንዖት ሰጥቼ ገልጨላቸዋለሁ” ብለዋል።ከማይክ ሀመር ጋር በነበረኝ ቆይታ “በፕሪቶርያው ስምምነት ያልተፈጸሙ ጉዳዮችን የተመለከተ እና በቀጣይ ሊሰሩ ስለሚገባቸው ስራዎች ተወያይቻለሁ” ሲሉ ገልጸዋል።በውይይቱ ላይ አምባሳደር ማይክ ሀመር የአሜሪካ መንግስት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተጣለበትን ተልዕኮ በተቻለ ፍጥነት ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸውልኛል ሲሉም አመላክተዋል። አቶ ጌታቸው በተጨማሪም “ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ ለማስቻል ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ የተቀናጀ ግፊት እንደሚያደርጉ ሀመር ገልጸውልኛል” ብለዋል።ከቀያቸው ተፈናቅለው በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ መጠለያ ካምፖች እና በሱዳን በስደት የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ስቃይ እንዲያበቃ የአሜሪካ መንግስት ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው ለማይክ ሀመር እንደጠየቋቸውም አስታውቀዋል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አስመራ ውስጥ ያለንን ገንዘብ እንዳናወጣ ተከልክለናል - የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ሲያደርገው የነበረውን በረራ ከዛሬ ጀምሮ ማቋረጡን ገልጿል። አየር መንገዱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው አገልግሎቱን ለመስጠት በኤርትራ በኩል ባጋጠመው ከአቅም በላይ የሆነ የአሰራር ችግር ምክንያት እንደሆነ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። የአየር መንገዱ የአስመራ ቅርንጫፍ የሂሳብ ደብተር ሙሉ በሙሉ መታገዱ ወደ ከተማዋ ያደርገው የነበረው በረራ ለመቋረጡ አንድ ምክንያት መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ጠቅሰዋል። አየር መንገዱ ኤርትራ ውስጥ የናቅፋ እና የውጭ ገንዘቦች አካውንት እንዳለው የጠቀሱት አቶ መስፍን፤ ይህን ገንዘቡን በፈለገው ጊዜ የማንቀሳቀስ መብት እንዳለው ገልፀዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ይህን ገንዘቡን እንዳያንቀሳቅስ በኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መከልከሉን ጠቅሰዋል። በዚህም አየር መንገዱ ገንዘቡን ማንቀሳቀስ እና ለተለያዩ ወጪዎች መጠቀም ባለመቻሉ በረራውን ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቀዋል።እንዲያም ሆኖ ያጋጠሙ ችግሮችን በአፋጣኝ በንግግር ለመፍታት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁንም ዝግጁ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን ጣሰው ገልፀዋል።
Show all...
1
ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት   የተሰጠ  መግለጫ እስካሁን በዘረፋ እና እገታ ወንጀል የተጠረጠሩ 92 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ከቅርብ ጊዚያት  ወዲህ  በከተማችንና አካባቢው የተለያዩ   ወንጀሎች  መከሰታቸውና  የብዙ ወገኖቻችን ሰላምና ደህንነት የሚያውክ  ድርጊት እየተፈፀመ  ከመሆኑ ጋር ተያይዞ  ወገኖቻችንን  ያሳዘነና  ልብ  የሰበረ  መሆኑ ይታዎቃል። በተለየም ደግሞ ራሳቸውን  መከላከል  በማይችሉ  በሴቶች፣ በህፃናት እና  በአረጋውያን   ላይ ያነጣጠረ አፈና፣  እገታ  እና  ግድያ ሲፈጸም ቆይቷል። የከተማችን ሕዝብ በተለያዩ ጊዚያት  የችግሩን መንስኤ በውል በመለየት  በጥፋተኞች ላይ የሕግ የበላይነትን  እንድናስከብር የገለጸልንን ሐሳብ መነሻ በማድረግና ተጨማሪ ሥራዎችን በመሥራት በእገታ፣  በግድያና በዘረፋ  ወንጀል የተጠረጠሩ  49 ግለሰቦችን    በቁጥጥር ሥር አውለናል። ነሐሴ 27/16 ዓ.ም በከተማችን በተፈጠረው ችግር ምክንያት  ስለተጎዱ ወገኖቻችን ጉዳዩን አጣርተን የምንወስደውን ሕጋዊ እርምጃ ውጤቱን ለሕዝባችን የምናሳውቅ ይሆናል ። ሌሎች ቀሪ ተጠርጣሪዎችን ለመቆጣጠር ሥራ  እየሠራን ባለንበት ወቅት የከተችንን ሰላም እና ደህንነት  የማይሹ ኃይሎች  የግል ጥቅማቸውን ለማጋበስ ሲሉ ከጎንደር እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም የእናትና ልጅ ግድያ ተፈፅሟል። ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም ከእናቷ ጡት ነጥቀው የሁለት ዓመት  ህፃን በማገት  300 ሺህ ብር ከተቀበሉ  በኋላ   ገድለው ከወላጆቿ ግቢ ጥለዋታል። የእናቷን ጡት  ሳትጠግብ በጠዋቱ  ሕይወቷን በተነጠቀችው ህፃን  ልጃችን፣ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም በዚሁ  አረመኔና ጨካኝ ቡድን  ሕይወታቸውን  ባጡ የእናትና  ልጅ  ሕልፈተ ሕይወትና ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም   በተፈጠረው ችግር ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የፀጥታ ምክር ቤቱ የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለተጎዱ ቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና  ለመላው የከተማችን ሕዝብ  መፅናናትን እንመኛለን። የጋራ ፀጥታ ምክር ቤቱ  የተከሰተውን ግጭት  ለማስቆም ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት በወንጀሉ የተሳተፉ አካላትን ለሕግ የማቅረብ እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ  ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው። ወንጀለኞችን ለመቆጣጠር፣ የሕግ የበላይነትን  ለማረጋገጥ እና የከተማችንን ሰላም ለመጠበቅ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ ድምፅ አልባ  መሣሪያ እና ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ  መንቀሳቀስ፣  በተደራጀም ይሁን በተናጠል በከተማችን ወንጀል   መፈፀም ፍፁም ሕገ ወጥና  የተወገዘ ተግባር ነው ።  የተከበራችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የሰው ሃብት እና ንብረት ዘርፈው ለመክበር  የቋመጡ  ኃይሎች ከተማውን ለመዝረፍ  የተሰለፋ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከመንግሥት ጎን በመቆም የምትወዷትን ከተማችሁን ከአጋችና ከዘራፊ   ቡድን እንድትጠብቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን"ብሏል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተመራ ልዑክ በ9ኛው የቻይና-አፍሪካ ትብብር የሚኒስትሮች ጉባዔ እየተሳተፈ ይገኛል! ዛሬ ነሃሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም በመካሄድ ላይ ባለው በ9ኛው የቻይና-አፍሪካ ትብብር የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በተመራ ልዑክ እየተሳተፈች እንደሚገኝ ተገለጸ።ነገ ነሃሴ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በሚጀመረው የቻይና-አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የበርካታ ሀገራት መሪዎች ቤጂንግ እየገቡ እንደሆነም ተጠቁሟል። ከጉባዔው ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ወዳጅነቷን ለማጠናከር እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እንደምትሠራ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው መግለጻቸውን ከኤፍቢሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ መጪው ጊዜ በጋራ መሥራትን የሚፈልግ በመሆኑ ቻይና ከአፍሪካ ጋር የተሻለ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል። የደቡብ-ደቡብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ብሎም ወደ ጋራ ልማትና ብልፅግና ለመሸጋገርም ቻይና እንደምትሠራ አረጋግጠዋል፡፡አሁን በጋራ አዲስ ታሪክ እንድንፅፍ መተባበር ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡በጉባዔው ላይ የቻይና-አፍሪካን ግንኙነት እና ትስስር በይበልጥ የሚያሳድጉ ጉዳዮች እንደሚነሱ ይጠበቃል።
Show all...
1
Photo unavailableShow in Telegram
አቶ ማሞ ምህረቱ ከቢል ጌትስ ጋር ተወያዩ! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ መስራችና ሊቀ መንበር ባለሃብቱ ቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል። ቢል ጌትስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እና ከብሔራዊ መታወቂያ ዲጂታል ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ ጋር ባደረጉት ፍሬያማ ውይይት፤ ያለውን አጋርነት ማጠናከር ስለሚቻልበት ሁኔታና የዲጂታል ፋይናንስ አካታችነት ላይ መክረዋል። በተለይም ቀጣናዊ፣ ስርዓተ ጾታ እንዲሁም ኢስላሚክ ፋይናንስን ማስፋፋት ላይ መወያየታቸውን የብሔራዊ ባንክ መረጃ አመልክቷል። ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ መንግስት የዲጂታል መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የዲጂታል ሽግግርና የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ ቢል ጌትስ አረጋግጠዋል።
Show all...
👍 1 1
በጎንደር ከተማ የሁለት ዓመት ሕጻን በአጋቾቿ መገደሏ ቁጣን ቀሰቀሰ! በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የሁለት ዓመታ ሕጻን ታግታ ከተወሰደች በኋላ ትናንት ሰኞ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም. ተገድላ አስክሬኗ በወላጆቿ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ።ቢቢሲ ያነጋገራቸው የታጋቿ የቅርብ ቤተሰብ ነን ያሉ ግለሰብ ኖላዊት ዘገየ የተባለችው የሁለት ዓመት ታዳጊ ከምትኖርበት ቤት የታገተችው ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም. መሆኑን ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አጋቾች ከጠየቁት የማስለቀቂያ ገንዘብ አብዛኛውን መጠን ቢቀበሉም “ጡጦ ያልጣለችውን” ታዳጊ ገድለው መጣላቸውን የቤተሰብ አባሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል።የሕጻኗን በአጋቾቿ ተገድሎ መጣል አስመልክቶ የተቆጡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በትናንትናው ዕለት አደባባይ የወጡ ቢሆንም፣ ከከተማዋ የጸጥታ ኃይሎች ጋር መጋጨታቸውን እና ጉዳት መድረሱን የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኖላዊት ዘገየ የተባለችው ይህች የሁለት ዓመት ታዳጊ ለቤተሰቧ ብቸኛ ልጅ ነበረች።ታዳጊዋ የተወሰደችው ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አርብ ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም. ረፋድ 3፡30 ላይ ግቢዋ ውስጥ ስትጫወት መሆኑን የቤተሰብ አባሉ ይናገራሉ።የኖላዊትን መጥፋት ተከትሎ የአካባቢው ሰው ታዳጊዋን ፍለጋ በየአቅጣጫው ወጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ የታጋቿ ወላጆች ተከራይተው በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ በአጋቾቹ የተጣለ ማስታወሻ ወረቀት ከተገኘ በኋላ ኖላዊት መታፈኗ እንደታወቀ የቤተሰብ አባሉ አስረድተዋል።“በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ እኛ አግተን ወስደናታል እስክንደውልላችሁ ታገሱ” የሚል መልዕክት የሰፈረበት ወረቀት መገኘቱን የቤተሰብ አባሉ ይናገራሉ። በመኖርያ ቤቱ ውስጥ ወዳጅ ዘመድ ተሰብሰብቦ በነበረበት ወቅትም አጋቾቹ “ይህንን ካልበተናችሁ እንገላታለን። ለፖሊስ ብታመለክቱም እንገላታለን” የሚል ማስፈራርያ አዘል ጽሑፍ ግቢ ውስጥ መጣላቸውን አስረድተዋል። በመቀጠልም አጋቾቹ የማስለቀቂያ 1 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው የጠየቁ ሲሆን የታዳጊዋ አባት ተቀጥሮ የሚሰራ ሹፌር በመሆኑ “በድርድር 300 ሺህ ብር ለመቀበል መስማማታቸውን” ገልጸዋል።“መጀመርያ 1 ሚሊዮን ብር ነበር የጠየቁት። አባቷ ተቀጥሮ የሚሰራ ሹፌር በመሆኑ ተለምነው በ300 ሺህ ብር ተስማሙ” ይላሉ። ይሁን እንጂ የ300ሺህ ብር ክፍያውም ከሕጻን ኖላዊት ወላጆች እና ከወዳጅ ዘመድ አቅም በላይ ሆኖ በልመና የተገኘው ገንዘብ ግን 200 ሺህ ብር እንደነበር እና 100 ሺህ ብር መጉደሉን ይናገራሉ።ይሁንና ገንዘቡን አጋቾቹ በባጃጅ (በባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ) መጥተው ቢወስዱም ታዳጊዋን ገድለው ከወላጆቿ መኖሪያ ቤት ጓሮ አስከሬኗን መጣላቸውን በሐዘን ውስጥ ሆነው እኚሁ የቤተሰብ አባል አስረድተዋል። “ምናልባት 100 ሺህ በመጉደሉ ይሆናል የገደሏት” የሚሉት ግለሰቡ የባጃጁ ሰሌዳ ቁጥር፣እና የሚደውሉበትን ስልክ ቁጥር መያዛቸውን ይናገራሉ።የታዳጊዋን ግድያ ተከትሎ በጎንደር ከተማ ቁጣ መቀስቀሱን ጭምር ይህ የቤተሰብ አባል ለቢቢሲ ተናግረዋል።ትናንት ሰኞ አመሻሽ ላይ ወላጅ አባቷ እንዲሁም ሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች የሕጻኗን አስከሬን በመያዝ “ፍትሕ” እየጠየቁ ወደ ከተማዋ አደባባይ ከወጡ በኋላ ከአድማ በታኝ የጸጥታ አካላት ጋር መጋጨታቸውን ተናግረዋል። በመንግሥት ሰላም አስከባሪ አካላት እና አደባባይ በወጣው ኅብረተሰብ መካከል አለመግባባት መፈጠሩን ተከትሎ ጸጥታ አስከባሪዎች ጥይት ተኩሰው የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውንም ጨምረው አስረድተዋል።ከሕጻን ኖላዊት በተጨማሪ በቅርቡ በጎንደር ከተማ ከእገታ ጋር በተያያዘ የተገደሉ እናትና ልጅ መኖራቸውን የሚናገሩት የከተማዋ ነዋሪ፣ ከአንዴ በላይ የታገቱ፣ በፍራቻ ምክንያት አካባቢውን ለቅቀው የሄዱ መኖራቸውን ይናገራሉ። በጎንደር እገታ እና ግድያ “ንግድ ሆኗል” የሚሉት እኚህ የቤተሰብ አባል በርካቶች በሀብታቸው ምክንያት ዒላማ በመደረጋቸው ከተማዋን ለቅቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ይናገራሉ።አክለውም አጋቾች “መዋቅር ያለው፣ ጠንካራ፣ ተሽከርካሪ ያላቸው በምሽት የሚንቀሳቅሱ” መሆናቸውን ያስረዳሉ።ይህ የቤተሰብ አባል እንዲህ ሊሉ የቻሉበትንም ምክንያት ሲያስረዱ ከአጋቾቹ መካከል ሁል ጊዜ የሚደውለው ግለሰብ ደውሎ ገንዘብ እንዲቀንሱላቸው ሲጠየቅ “እኔ ስልክ ደዋይ ነኝ። ሌሎቹ ናቸው ገንዘቡን የሚወስኑት፤ እጠይቅልሀለሁ” የሚል መልስ እንደሚሰጥ ይገልጻሉ። ሰዎቹን አግተው የሚወስዱ፣ ስምሪት የሚሰጡ፣ ገንዘቡን የሚቀበሉ የተለያየ ግለሰቦች መኖራቸውን እና የተደራጁ መሆናቸውን ስልክ ከደወለው ግለሰብ መረዳታቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።ከዚህ ቀደም በእገታ ሰበብ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ግለሰቡ “ጡጦ የሚጠባ ሕጻን አግቶ ገድሎ በር ላይ አምጥቶ መጣል ግን ለመጀመርያ ጊዜ የታየ ነው” ይላሉ። በጎንደር ከተማ በእገታ ወንጀል የተጠረጠሩ 31 ግለሰቦች ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል::ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚከሰቱ እገታዎች ሕዝቡን ሰላም ነስቷል። አልፎ አልፎ በተለያዩ አካባቢዎች ይፈጸም የነበረው እገታ አሁን መልኩን ቀይሮ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል ማጋጠሙን የሚገልጹ መረጃዎች እየወጡ ነው። በተለይ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ለገንዘብ ሲባል የሚፈጸመው እገታ በርካቶችን ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ዳርጓል።ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከጥቂት ሺህ ብሮች ጀምሮ እስከ ሚሊዮኖች ድረስ ለመክፈል የተገደዱም በርካቶች እንዳሉ ሆነው በአጋቾቻቸው እጅ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች እንዲሁ በርካቶች ናቸው።
Show all...
👍 1 1
የሕግ አለመከበር እና የመንግሥት መዋቅር መላላት ስርአት አልበኝነትን አንግሷል-ኢሰመኮ በአገሪቱ የህግና ስርአት አለመከበርና የመንግስት አገርን አረጋግቶ የመምራት ሂደት አለመቻል ስርአት አልበኝነትን እያነገሰ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ይህን ያለው በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሚመለከት ክትትል እና ምርመራ አድርጎ ውጤቱን ባሳወቀበት ወቅት ነው፡፡ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከተራዘሙ የትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው የሕግ ማስከበር እና የመንግሥት መዋቅር መላላት ሳቢያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በታጣቂ ኃይሎች፣ ለዘረፋ በተደራጁ ቡድኖች እንዲሁም በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አባሎች የሚፈጸሙ እገታዎች ተባብሰው ቀጥለዋል ብሏል፡፡ አጋቾች ሰላማዊ ሰዎችን በአብዛኛው በጉዞ ላይ እያሉ አንዳንዴም ከመኖሪያ ቤታቸው ወይም ከሥራ ቦታቸው አግተው ወዳልታወቀ ቦታ በመውሰድ ከፍተኛ የማስለቀቂያ ገንዘብ ክፍያ  እንደሚጠይቁ ኢሰመኮ አመላክቷል፡፡ እገታው በአብዛኛው እንደ ገቢ ማስገኛ የተወሰደ መሆኑን፤ አልፎ አልፎም እንደ በቀል፣ ለፖለቲካ ዓላማ ወይም የታገተ ሌላ ሰውን ለማስለቀቅ በሚል በአጸፋ መልኩ የሚፈጸም መሆኑን ባደረገው ምርመራ አስታውቋል፡፡ በዚህም የታገቱ ሰዎችን ለማስለቀቅ ገንዘብ እንደሚጠየቅ እና መክፈል ያልቻሉ ታጋቾች የድብደባ ግድያ እንዲሁም ጾታዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ተጠቁሟል፡፡ በዓለም አቀፉ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ማዕቀፎች መሠረት በጦርነት ዐውድ ውስጥ የሚፈጸም እገታ በዓለም አቀፍ የሰብአዊነት እንዲሁም የወንጀል ሕግ መሠረት የጦር ወንጀልን ሊያቋቁም የሚችል በመሆኑ፣ መንግሥት ብቻ ሳይሆን የታጠቁ ቡድኖችም ድርጊቱን ከመፈጸም የመታቀብ ዓለም አቀፍ ግዴታ እንዳለባቸው ኮሚሽኑ አስታውሷል፡፡ በመሆኑም የፌዴራል እንዲሁም የክልል መንግሥታት ለችግሩ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በተለይም በተደጋጋሚ እገታ በሚፈጸምባቸው አካባቢዎች እገታን ለመከላከል ውጤታማ የጥበቃና ቁጥጥር ሥራዎችን ከማከናወን በተጨማሪ የታጋቾችን ደኅንነት በጠበቀ መልኩ የማስለቀቅ ሥራዎችን እንዲያጠናክሩ አሳስቧል፡:
Show all...
1
Photo unavailableShow in Telegram
ተፈናቃዮችን በቋሚነት የማቋቋም ሥራ ከዕቅድ በዘለለ ወደ ትግበራ አልገባም -ኢሰመኮ በኦሞ ወንዝ የላይኛው ተፋሰስ አካባቢዎች ከነሐሴ ወር የመጀመሪያ ቀናት ጀምሮ በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት የዳሰነች ወረዳ ዋና ከተማ በሆነው የኦሞራቴ ከተማ እንዲሁም ቻይና ካምፕ በተባሉ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ በውሃ የመጥለቅለቅ ሥጋት ተጋርጦባቸዋል ብሏል። ኢሰመኮ አደረኩት ባለው ክትትል በባዩ የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ 2 ሺህ 744 የሚሆኑ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በአካባቢው በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ለዳግም መፈናቀል መዳረጋቸውን አስታውቋል፡፡
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.