cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኑር ሚድያ {Nur Media}

√√ ከምንም በፊት ቅድሚያ ለተውሂድ ---- በዚህ ቻናል በቻልኩት መጠን ሀቅን የበላይ ለማድረግ እና ባጢልን የበታች ለማድረግ የበኩሌን ለማድረስ እሞክራለው። •••• ሀይማኖታችንን ምንወስደው 1 ከቁርአን 2 ከሀዲስ 3 ከሰለፎች አረዳድ 4 የተለየዩ ሩዱዶች 5 አጫጭር ሀዲሶች

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
378
المشتركون
-124 ساعات
-57 أيام
-1730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ከኹጥባ የተቀነጨበ ሐምዛ ያሲን፣ ነቀምት
إظهار الكل...
Jaalala rasuulaa ..1.m4a3.55 MB
ጳጉሜ 02/13/2016 ✅ የጁመዓ ኹጥባ 📔 ርዕስ በኢስላም ላይ የተጋረጡ ሁለት ትላልቅ አደጋዎች 🎙 በኡስታዝ ተውፊቅ ሙሃመድ ሃፊዘሁላህ 🕌 በወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ https://t.me/tewuhidWereilu/5614
إظهار الكل...
ትልልቁ ሁለቱ አደጋዎች _06-23-29.mp36.45 MB
ሰለምቴነት ማሸማቀቂያ አይደለም! ~ አንዳንድ ሰዎች በእምነታዊ ጉዳዮች ላይ ስሜታቸውን ለመከተል፣ ከወረዱበት ለመውረድ ፈቃደኛ ያልሆላቸውን ሙስሊም ወደ ኋላ ታሪኩ በማጠንጠን “አንተ ሰለምቴ አይደለህ? ምን ታውቃለህ?” እያሉ ሊያሸማቅቁ ይጥራሉ። የተለየ አውቀው፣ የተሻሉ ሆነው ሳይሆን እንዲሁ የነሱን ስሜት ተከትሎ ስላላጨበጨበ ብቻ አንድን ሙስሊም በዚህ መልኩ ለማሸማቀቅ መሞከር ጋጠ-ወጥነት ነው። ሰለምቴነት ክብር እንጂ ነውር አይደለም። ሰለምቴነት ገድል እንጂ ማሸማቀቂያ አይደለም። በዚህ ፈተናው በበዛበት፣ የጥፋት ሃይሎች በሚርመሰመሱበት፣ ኢስላምን የሚያጠለሹ አካላት እንደ አሸን በፈሉበት፣ እጅግ ከባባድ ማደናገሪያዎች ያለ ገደብ በሚለቀቁበት ዘመን በምንም ሰበብ ቢሆን ወደ ኢስላም የሚመጡ ሰዎች ሊከበሩ እንጂ ሊነቆሩ አይገባቸውም። ድክመትም ካለባቸው መሸፈ፞ን እንጂ ማጋለጥ አይገባም። ከቻልን ሞራል እንስጥ። ይህን ማድረግ ካቃተን በማሸማቀቅ ገፍተን እንዳናስወጣቸው እንጠንቀቅ። ክርስቲያን ወይም አይሁድ የነበረ ሰውኮ ወደ ኢስላም ቢገባ በእጥፍ እንደሚመነዳ ነብዩ ﷺ ተናግረዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] አልኢማም አልቡኻሪ ረሒመሁላህ በሶሒሐቸው بَابُ فَضْلِ مَنْ أَسْلَمَ مِنْ أَهْلِ الكِتَابَيْنِ የሚል ርእስ እንዳሰፈሩ እናስተውል። ‘ፈድል’ ማለት ልቅና፣ ብልጫ ማለት ነው። ነብያችን ﷺ ለሮማው ንጉስ ሒረቅል በፃፉት ደብዳቤ ላይ ወደ ኢስላም ሲጠሩት ምን ነበር ያሉት? أَسْلِمْ تَسْلَمْ، يُؤْتِكَ اللَّهُ أَجْرَكَ مَرَّتَيْنِ “ስለም። ትድናለህ። አላህ ምንዳህን #ሁለት_ጊዜ ይሰጥሀል።” [ቡኻሪና ሙስሊም] ይሄ መልእክት በሒረቅል ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። የኢብኑ ሐጀርን ማብራሪያ ይመልከቱ። [ፈትሑል ባሪ፡ 8/221] በነገራችን ላይ አንድ ካ^ፊ^ር ወደ ኢስላም ከገባ ከመስለሙ በፊት ሲፈፅማቸው የነበሩ መልካም ስራዎች ይታሰቡለታል። ሐኪም ብኑ ሒዛም ረዲየላሁ ዐንሁ “በዘመነ ጃ^ሂሊያ ስፈፅማቸው ስለነበሩት ዒባዳዎች፤ ሶደቃ፣ ባሪያ ነፃ ማውጣት፣ ዝምድናን መቀጠል በተመለከተ ንገረኝ እስኪ። ምንዳ ይኖራቸዋልን?” ብለው ነብዩን ﷺ ቢጠይቁ እንዲህ ብለው ነው የመለሱላቸዋል፡- أَسْلَمْتَ عَلَى مَا أَسْلَفْتَ مِنْ خَيْرٍ “ካሳለፍከው መልካም ስራ ጋር ነው የሰለምከው።” [ሶሒሕ ሙስሊም] ልብ በል! ሐኪም ብኑ ሒዛም ከመካ መኳንንት የነበሩ ሲሆን በድር ላይ ከቁረይሾች ጋር ተሰልፈው ጦርነቱን ተካፍለዋል። አላህ ሲያድላቸው እንደ አጋሪ ጓዶቻቸው በድር ላይ ሳይገደሉ በመትረፋቸው ኋላ ላይ ሰልመዋል። ለዚህም ነበር “የበድር ቀን ከመገደል ባተረፈኝ ጌታ ይሁንብኝ” እያሉ ይምሉ የነበሩት። ወንድሜ ሆይ! 1. እስኪ የነዚያን በጀነት የተመሰከረላቸውን ሶሐብዮች ታሪክ እናንብብ። ከነዚያ ታላላቅ የኢስላም ፈርጦች ውስጥ ቀድሞ ጣኦት አምላኪ የነበሩት'ኮ እጅግ በርካታ ናቸው። 2. እስኪ የነ ዐብደላህ ብኑ ሰላም፣ የነብያችን ﷺ ሚስት ሶፊያን ታሪክ እናገላብጥ። ከነዚያ እንቁ ሶሐብዮች ውስጥ ቀድሞ አይሁድ የነበሩት ብዙ ናቸው። 3. እስኪ የነ ሰልማኑል ፋሪሲ፣ ዐዲይ ብኑ ሓቲምና መሰል ሶሐቦችን ታሪክ እንፈትሽ። አዎ ከነዚያ ወደር የለሽ የኢስላም ጀግኖች ውስጥ ከመስለማቸው በፊት በክርስትና ውስጥ ያለፉ ነበሩ። 4. ከሶሐቦች ጊዜ ወዲህም ታሪክ የሰሩ፣ ለኢስላምና ለሙስሊሞች በዋጋ የማይተመን ውለታን የዋሉ በርካታ ሰለምቴዎች አልፈዋል። ልብ በል ወንድሜ! ልብ በይ እህቴ! ኢስላም መለኮታዊ ሃይማኖት እንጂ የማንም ግላዊ ንብረት አይደለም። ኢስላም ለሰው፣ ለጂኑ ባጠቃላይ የቀረበ አምላካዊ መድህን እንጂ ያሰኘንን የምናስገባበት፤ የደበረንን የምናስወጣበት ያ'ባታችን ግቢ አይደለም። ኢስላም ልክ ቄሶች “ውጉዝ ከመ አሪዮስ!” ብለው እንደሚያባርሩት ሸይኾችም እንዳሻቸው የሚፈርዱበት ቀልደኛ ቀኖና የለውም። ስለዚህ ወንድሜ! እስልምናን ከአባት ከአያት የወረስከው አንተ፣ በኢስላም ላይ ከሰለምቴው የተለየ የባለቤትነት መብት የለህም። ከአላህ ዘንድ ያለህ ደረጃ ከፍ የሚለው በተቅዋህ ብቻ ነው። ለሰለምቴው ኢስላምን የሰጠው የፈጠረው ጌታ እንጂ እኔ ወይም አንተ አይደለንም። እኛ ይህን የጌታ ፀጋ አከፋፋዮች አይደለንም። ምናልባት “በሰለመ በማግስቱ ፈትዋ ካልሰጠሁ ብሎ የሚገላገል ሰለምቴስ ዝም ይባል ወይ?” የሚል ሊኖር ይችላል። ይሄ ሌላ ርእስ ነው። እያወራሁ ያለሁት ሰለምቴነትን ለማነወሪያነት ስለሚጠቀሙ አካላት ነው። የነሱን ስሜት ተከትሎ ስላልፈሰሰ ብቻ “እሱ'ኮ ሰለምቴ ነው?” በማለት ለማንጓጠጥ መሞከር ምን ማለት ነው? እስኪ አስቡት! በሚያጋጥሙ አንዳንድ አለመግባባቶች የተነሳ “እሱ'ኮ መስለሙንም እንጃ!”፣ “እሱ'ኮ የሰለመ ጊዜ ቄሶች በደስታ እንኳን ሄደልን ያሉት ነው”፣ “እሱ'ኮ እንደገና ወደ ክርስትና ሳይመለስ አይቀርም”፣ “እሱ'ኮ ሶላት አይሰግድም"፣ "እሱ'ኮ ውዱእ ሲያደርግ ታይቶ አይታወቅም"፣ "እሱ'ኮ ይሰክራል …” ወዘተ በሚሉ እጅግ ሰቅጣጭና ፀያፍ ውንጀላዎች በሃሰት የሚወ፞ነጀል ሰለምቴ ምን እንደሚሰማው አስቡ። በተጨባጭ የተከሰቱ ሃሰተኛ ውንጀላዎችን ነው በምሳሌነት የጠቀስኩት። ተወንጃዮቹ ልፍስፍስ ቢሆኑ በቀላሉ ወደ ኩ^ፍ^ር ተገፍተው ከኢስላም በሸሹ ነበር። ግና ኢስላም ማለት የነዚህ ዋልጌዎች የግል ንብረት እንዳልሆነ ጠንቅቀው ማወቃቸው በጃቸው። ሰዎቹን ከማወቃቸው በፊት ኢስላምን ማወቃቸው ጠቀማቸው። እንጂ እንደዋዛ አኩርፈው በበረገጉ ነበር። ወላሂ! አንድ ስንት ስራ የሰራ ወንድም ፈፅሞ ይዋሻሉ ብለን በማንገምታቸው ሰዎች በተደጋጋሚ በመወ፞ንጀሉ የተነሳ ብዙ ሰዎች እስልምናውን እስከሚጠራጠሩት የደረሱበት ሁኔታ በተጨባጭ አውቃለሁ። መነሻው ግን የእነዚያ ታማኞች የመሰሉን ሰዎች ክፋት ነበር። በተረፈ ሰለምቴ ሆነው ስንቶችን ቁጭ አድርገው እየገሩ ያሉ ኡስታዞች አሉ?! ሰለምቴ ሆነው ለስንቶች መስለም ሰበብ የሆነ ስራ ላይ በሰፊው የዘመቱ አሉ?! ካረገዙ በኋላ በባሎቻቸው ተከድተው ብዙ ፈተና ቢደርስባቸውም ከነ ችግራቸው በኢስላማቸው ላይ እንደፀኑ ያሉ ስንት ሰለምቴዎች አሉ?! ወንድ ወይም ሴት ተከትለው ስንቶች በሚከ^ፍ^ሩበት ዘመን ለኢስላም ሲሉ ከቤተሰብ የተቆራረጡ፣ ትዳራቸውን የበተኑ ስንት ቆራጥ ሰለምቴዎች አሉ?! ነባር ሙስሊሞች በእርዳታ በቆሎ እምነታቸውን በሚቀይሩበት ምድር ለኢስላም ሲሉ ሁለ ነገራቸውን አጥተው ለእለት ጉርስ የተቸገሩ ስንት ፈተና ያልበገራቸው ሰለምቴዎች አሉ?! ደግሞም አላዋቂ ሰለምቴ እውቀት በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ ያላቅሙ ገብቶ ካገኘን ብቃቱ ካለን በአደብ ማስተማር እንጂ ሰለምቴነቱን ለማሸማቀቂያ መጠቀም፣ ሰለምቴነቱን እንደ ነውር በመቁጠር በየደረሱበት ማማት የለየለት ነውር ነው። መሀይም የሆነ ሰው ሰለምቴም ባይሆን ያላቅሙ እንዲያወራ የተሰጠው የተለየ ፍቃድ ወይም መብት የለውም። ስለዚህ ሰለምቴው በተለየ የሚኮነንበት ምክንያት ምንድነው? ሰለምቴ ሆኖ ከብዙዎቻችን የተሻለ ግንዛቤ ያለው ስንት ሰው አለ? ከውልደት እስከ እርጅና እድሜውን ኢስላም ውስጥ አሳልፎ አሊፍ ትቁም ትጋደም የማያውቅ እልፍ አእላፍ ህዝብስ የለም ወይ? እውቀት'ኮ በመማር እንጂ በውልደት የሚገኝ አይደለም። “ሸንበቆ አስር አመት ውሃ ውስጥ ቢቆይ አዞ አይሆንም” ይባላል። ለውጥ ከአላህ እገዛ ጋር በጥረት እንጂ በምኞትም በጉራም አይገኝም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 01/2012) https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ይድረስ ለበርበሬ ሚዲያ አድሚኖች ✪ «»በዚህ በርበሬ ሚዲያ በሚል ፔጅ ውስጥ ቡዙ ግዜ የሽርክ ቦታዎች እና በነብዩ ሙሀመድ ﷺ ውዴታ ስም ኩራፋት የበዘባትን መውሊድ ሲያስተዋውቅ ይስተዋላል ይህ አካሄዱ እንዳይታወቅ ሁሉንም አካተች ለማምሰልም ይሞክራል እናም ጎቦዝ ተነቃቅተናል ቡዙም አትልፋ። ✪ ምንአልባት ትሉ ይሆናል ያመነበትን ነገር መሰራጨት ይችላል አዎ ይችላል ነገር በሀላባ ህዝብ ስም አይደለም። ሀላባ ውስጥ መውሊድ የሚከበርበት ቦታ ውስን ቦታ ነው አብዛኛው የሀላባ ህዝብ መውሊድ የሚሉትን ነገር አያከብርም ይህ መሆኑን እየታወቀ በህዝብ ስም መነገድ አግባብ አይደለም።ስለዚህ ሽርክ እና ብዳዓ እየስተዋወክ ኡማውን አትበትን። ✪ ሀላባ ሀላባ እየልክ ድፍን የሀላባን ህዝብ መውሊድ አክባሪ አተስመስል። እራስህን ችለህ የራስህን ፍለጎት አውራ ነገር ግን በሽርኽ እና በብዳዓ የሀላባን ህዝብ ወክለህ መውራት አትችልም። ህዝቡን ከቻልክ ከእንድህ አይነት ከአደንዛዥ እፅ(ከጫት) ውስጥ እንድወጣ እንጅ በአንድነት መስራት የለባን ተማርን አወቅን ብለን ከእንደገና ወደ ገሪባነት እንጠራለን ወይ??? ✪ ከዚህ በፊት ከOBN ቴሌቪዥን ተማሰጥራችሁ የኑረላህ አህመድን ቀብር ስተስተዋውቅ ነበርክ በቱርስት ስም ይህ መቃብር በመሰረቱ የሰው ሰይሆን የአህያ መቃብር ነው። መስረጀዎችም የሚያመዝኑት ወደዛ ነው። የአህያ ሆና የሰው ልመለክ አይገባም ይህን ቦታ የሽርክ እና የተለየዩ ወንጀሎች መናኸሪያ መሆኑ እየታወቀ በቱርስት ስም ማስተዋወቅ ሽርክን ለሚፈፅሙ ሰዎች እውቅና መስጣት ነው አላህ ሽርክን አስመልክቶ እንድህ ይላል። لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ ✪ እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ጀነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ ✪ ወዳጆቼ ሽርክ ከበደ ወንጀል ነው ሽርክን እና የሽርክ መዳረሻዎችን ልንጠነቀቅ ይገባል መውሊድ ውስጥ እረሱ ቡዙ የሽርክ መንዙማዎች ይወሳሉ ከነዚህም ውስጥ«#አብሽር ወንድሜ ግባ በቶሎ» «#ማነው ያፋራው «#ያ» ነቢ ብሎ»አሁን ይህ የሽርክ ስንኝ ነው ያአላህ እንጅ የነቢ፣ የኑር፣ሁሴን ፣ያ አብዱልቃድር ጀይላን ፣ልንል አይገባም ከበድ ወንጀል ነው። በነብዩ ሙሀመድﷺ ውዴታ ስም ቡዙ በደሎች እየተፈፀሙ ይገኛሉ  እሳቸውን መውደድ ማለት ፈለገቸውን መከተል እንጅ አመት ተጠብቆ ዲቤ በመደለቅ አይደለም እሳቸውን የእውነት የምንወድ ከሆና ሱናቸውን እንከተል ከዘ ውጭ በስማቸው አንነግድ። ✪ ነብዩ ሙሀመድﷺ ከተወለዱባት መካ ወደ መዲና የተሰደዱት ለተውሂድ ነው ሽርክን በመቃወማቸው ነው የግመል ሽንት የተደፈበቸው ለተውሂድ ስሉ ነው ጥርሳቸው የተሰበረው ለተውሂድ ስሉ ነው እሰቸውም ሶሃቦችም ይህን ሁሉ መከራ እና ስቃይ ያስተናገዱት ለተውሂድ ነው። እኛ ዘሬ በሰቸው ውዴታ ስም የሰቸውን ሱና እየተቀረን እንገኛለን አላህን እንኳን መውደዳችን ነብዩ ሙሀመድንﷺ ከተከተልን ነው የሚረጋገጠው አላህ እንዲህ ይላል፦ قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» ✪ አላህ የሚወደን የነብዩ ሙሀመድﷺ ሱና ስንከተል ብቻ ነው በረስ ፈሊጥ እሰቸውን እንወዳለን ማለት የሳቸውን መንገድ መናቅ ነው ነብዩ ሙሃመድን ከልተከተልን መቀመጫችን የት እንደሆና ግልፅ ነው። ስለዚህ ወንድሞቼ መውሊድ የሙስሊሞችን አንድነት የሚበትን እኩይ ተግበር ነው ተጠንቀቁ። ,ሰሞኑን መውሊድን አስመልክቶ የነሰቸውን ነጥቦች በክፍል ሁለት እንዳስሳለን 🖋አብዱልባስጥ ነኝ
إظهار الكل...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
የዛሬ ቀን ረቢአል አወል 12 ነብዩ ﷺ የሞቱበት ነው። ይህን ቀን አመታዊ የደስታ ቀን አድርጎ መያዝ ሰይጣናዊ መንገድ ነው። በኢስላም የሙት አመት የሚባልም ነገርም የለም። በኢስላም የታዘዝነውን ብቻ እንስራ። ከክስረት እንጠበቃለንና። ነብዩ ﷺ "ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው" ብለዋል።
إظهار الكل...
700ሺ ከሚቀርብ ማትሪክ ተፈታኝ ተማሪ ውስጥ ያለፈው 5% አይሞላም። ከዚህ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያሳለፉት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ናቸው። ቀሪውን አዲስ አበባ እና ጥቂት ትልልቅ ከተማዎች ይይዙታል። እነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ እና ከፍተኛ ቁጥር ያሳለፉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በዩኒቨርሲቲዎች ወይም በማህበራት የተቋቋሙ ተቋማት ናቸው። ስለዚህ የትምህርት ሚኒስቴር ውጤቶች አይደሉም ማለት ነው። ትምህርት ሚኒስቴር አለ ማለት የሚቻለው የገበሬውን ልጅ ከከተማው ልጅ እኩል መወዳደሪያ ሜዳ ሲያመቻች ነበር። መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ግን አሳዛኝ ነው። ለማንኛውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፈተና ጥብቅ ቁጥጥር ባሻገር የትምህርት ስርአቱም ላይ የረባ ስራ እስከሚሰራ ድረስ ክልሎችና ዞኖች ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ማቋቋም ላይ ብታተኩሩ መልካም ነው። አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሀረር፣ ምስራቁ የኦሮሚያ ዞኖች፣ ... እባካችሁ ተንቀሳቀሱ። እንደ ሃገር የትምህርት ትርጉሙ ቀላል አይደለምና ዛሬ ነገ ሳትሉ ተገቢ ትኩረት ስጡት። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

👆👆 👉ቦታው ታውቋል #በጣም_አስቸኳይ_ይደረግ👇👇 Ethiopian Federal Police Oromia Police Commission ድረጊት የተከናወነበት ቦታ ተውቋል…ህገ ወጦቹ ፖሊሶች በህግ እንዲጠየቁ ርብርብ እናድርግ 👉👉ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ #ባሌ_ዞን_ጋሰራ ወረዳ ነው እህታችንን ፖሊስ ጣቢያ ወስደው በዚህ መልኩ ከደበደቧት ቡሃላ እራሷን ስታ እንደ ነበርና ከሁለት ቀን ቡሃላ ከጣቢያው እንደ ወጣች ታውቋል…ራሷን ስትስት ምናልባት ደፍረዋት ሊሆን ይችላል አውሬዎቹ ለህግ ይቀርቡ ዘንድ ሁላችንም ሼር በማድረግ እንተባበር
إظهار الكل...
00:30
Video unavailableShow in Telegram
2.25 MB
👆👆 👉ቦታው ታውቋል #በጣም_አስቸኳይ_ይደረግ👇👇 Ethiopian Federal Police Oromia Police Commission ድረጊት የተከናወነበት ቦታ ተውቋል…ህገ ወጦቹ ፖሊሶች በህግ እንዲጠየቁ ርብርብ እናድርግ 👉👉ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ #ባሌ_ዞን_ጋሰራ ወረዳ ነው እህታችንን ፖሊስ ጣቢያ ወስደው በዚህ መልኩ ከደበደቧት ቡሃላ እራሷን ስታ እንደ ነበርና ከሁለት ቀን ቡሃላ ከጣቢያው እንደ ወጣች ታውቋል…ራሷን ስትስት ምናልባት ደፍረዋት ሊሆን ይችላል አውሬዎቹ ለህግ ይቀርቡ ዘንድ ሁላችንም ሼር በማድረግ እንተባበር
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የልብ ድርቀትን ለማከም ~ 1- ዱዓእ ማድረግ፣ 2- ቁርኣን መቅራት፣ መልእክቱን ተደቡር ማድረግ፣ 3- ዚክር ማብዛት፣ 4- ሞትን ማስታወስ፣ የቀብር ዚያራ፣ 5- ከደጋጎች ጋር መቀማመጥና መጎዳኘት፣ 6- ለደካሞች መልካም መዋል እና 7- ኢስቲግፋር እና ተውበት ማብዛት። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.