cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

Show more
Advertising posts
18 257
Subscribers
+324 hours
+57 days
+22430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✅ የቢዳዓ ባልተቤቶች እንደ ጊንጥ ናቸው አል ኢማሙል በርበሃሪይ – ረሒመሁላሁ — ስለቢዳዓ ባልተቤቶች ሲነግረን እንዲህ ይላል : – يقول البربهاري – رحمه الله – : " مثل أصحاب البدع مثل العقارب ، يدفنون رؤوسهم وأبدانهم في التراب، ويخرجون أبدانهم، فإذا تمكنوا لدغوا. وكذلك أهل البدع، هم مختفون بين الناس، فإذا تمكنوا بلغوا ما يريدون " طبقات الحنابلة ( 2/44 ) " የቢዳዓ ባልተቤቶች እንደ ጊንጥ ናቸው , አንገታቸውና ሰውነታቸውን አፈር ውስጥ ይደብቃሉ , ጅራታቸውን ያወጡና ሲመቻቸው ይነድፋሉ ። የቢዳዓ ባልተቤቶችም ልክ እንደዚሁ በሰዎች ውስጥ ይደበቃሉ ሲመቻችላቸው የሚፈልጉበት ይደርሳሉ " ። 🔹 ይህ ኢማም በሶስተኛው ክ/ዘመን የነበረ ሲሆን አሁን ስላለው ሁኔታ የሚናገር ይመስላል ። የቢዳዓ ሰዎችን ማንነትና ምንነት በመዘርዘር ከገለፁና ከእነርሱ ጋር ሊኖረን የሚገባውን ግብረገብነት የሰለፎችን መርህ በማስቀመጥ ግንባር ቀደሙን ከሚዙ አኢማዎች አንዱ ነው ። አላህ ካለ ሸርሑ ሱና የሚለው ኪታቡን በቅርቡ እንጀምራለን ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 9
👉 የኸድርና የነብዩላሂ ሙሳ ታሪክ ክፍል አንድ ቁርኣን ላይ ትኩረት ከተሰጣቸው አስተማሪ ታሪኮች ውስጥ የነብዩላሂ ሙሳና የኸድር ታሪክ ነው ። በዚህ ታሪክ ውስጥ ትልቁ አስተማሪ ነገር ማንም ቢሆን በእውቀት ጥግ ደርሻለሁ ማለት እንደሌለበት አላህ ከባሮቹ ውስጥ ለሚሻው ሰው ጥበቡ ባስፈረደው የእውቀት አይነት ለየት እንደሚያደርገው ። በዚህ ታሪክ ውስጥ ነብዩላሂ ሙሳ ረሱልና ከዛም ከፍ ባለ ደረጃ ዑሉል ዐዝም ከሚባሉት ውስጥ ናቸው ። ኸድር ደግሞ በቀደምት የኢስላም ሊቃውንቶችና እስካለንበት ዘመን ባሉ ተከታይ የኢስላም ሙሁራኖች እንደተረጋገጠው ነብይ መሆናቸው ነው ። በመሆኑም ኸድር ማለት ከነብያቶች ውስጥ አንዱ ናቸው ። ይህ ማለት በደረጃ ነብዩላሂ ሙሳ ይበልጣሉ ማለት ነው ። ምክንያቱም የረሱልነት ደረጃ ከነብይነት ደረጃ የሚበልጥ መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ ። ነብዩላሂ ሙሳ ደግሞ ከረሱልም በላይ አምስቱ ዑሉል ዐዝም የተባሉት ውስጥ ናቸው ። ነገር ግን የጥመት አንጃ የሆኑት ሱፍዮችና ሺዓዎች ይህን አስተምሮ በማስተባበል ኸድር ወልይ ነው አሉ ። እዚህ ጋር ቢቆሙ አንድ ነገር ነበር ነገር ግን ከዚህም አልፈው ሄዱ ። ወልይ ከነብይም ከረሱልም ከዑሉል ዐዝም ይበልጣል አሉ ።‼ ለዚህህ ስህተታቸው መነሻው ደግሞ አላህ ነብዩላሂ ሙሳን ኸድር ጋር ሄደህ ተማር ማለቱ ነው ። ይህ ማለት ኸድር አላህ ዘንድ በደረጃ ከሙሳ ከፍ ያለ ስለሆነ ነው ልዩ እውቀት ሰጥቶት ከሱ ተማር ያለው አሉ ። በመሆኑም የኸድር እውቀት የውስጥ እውቀት ( ዒልመል ባጢን) ነው የሙሳ እውቀት ደግሞ የውጭ እውቀት ( ዒልመ ዛሂር ) ነው የሚል ፍልስፍና ውስጥ ገቡ ። ከዚህ በመነሳት በእነርሱ እምነት የነብያት ተከታዮች የውጪውን እውቀት ነው የሚያውቁት የወልይ ተከታዮች ደግሞ የውስጡን ነው የሚያውቁት በመሆኑም የነብያት ተከታዮች የሸሪዓን ሚስጥር አያውቁም ላዩን ነው የሚከተሉት እኛ ደግሞ የሸሪዓን የውስጥ ሚስጥር ስለምናውቅ የውስጡን ነው ምንከተለው አሉ ። በዚህም ነብዩን ጨምሮ ሶሓቦችንና አጠቃላይ ቁርኣንና ሐዲስን የሚከተሉ የኢስላም ሊቃውንቶችን አላዋቂ መሀይማን አደረጉ ። ይህ እምነታቸው ነው ዛሬ ላይ እየታየ ያለውን የኩፍርና የሽርክ ተግባር እንዲፈፅሙ ያደረጋቸው ። ምነው ሲባሉ እናንተ ስለማታውቁ ነው ኩፍር የሚመስላችሁ ነገር ግን የሙታን መንፈስ ማምለክ ፣ በቀብር ላይ ጠዋፍ ማድረግ ፣ ወደ እነርሱ የተለያዩ ቁሩባን በማቅረብ እነርሱን መለማመን ፣ እርዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ ድረሱልኝ ፣ አሽሩኝ … ወዘተ ማለት ተውሒድ ነው አሉ ።‼ ይህ በተሳሳተ መነሻ ላይ የተመሰረተ የተሳሳተ እምነት ነው ። የዚህ ማሳያው እንደሚከተለው ነው : – 1ኛ – ኸድር ነብይ እንጂ ወልይ አይደለም ። የነብይነትና የወልይነት ደረጃ አይገናኝም ። የነብይነት ደረጃ በጣም የላቀ ነው ። 2ኛ – አንድ ሰው ሄደህ ከእገሌ ተማር መባሉ ያ አካል ከሱ መብለጡን አያሳይም ። ይበልጣል ቢባልም በዛ በሚያስተምረው ጉዳይ ነው ሊሆን የሚችለው ። ይህን ወደ ታሪኩ ስንገባ በግልፅ የምናየው ይሆናል ። 3ኛ – የነብዩላሂ ኸድር እውቀት ለራሱ የተሰጠው እንጂ ሸሪዓ ሆኖ ሊሰራበት አይደለም ። ሸሪዓ ቢሆን እንኳን ለነብዩ ተከታዮች ከዛ በፊት የነበሩ ነብያቶች ሸሪዓ ከቁርኣንና ሐዲስ ወይም ከነብዩ ሸሪዓ ጋር ከተጋጨ አይሰራበትም ሸሪዓም አይሆንም ። ሱፍዮችና አሕባሾች እያጨማለቁት ላለው ኩፍርና ሽርክ የነብዩላሂ ሙሳና የኸድር ታሪክ በፍፁም መረጃ ሊሆን አይችልም ። ምክንያቱም በባጢል ላይ የተመሰረተ ነገር ባጢል ነውና ። አላህ ለነብዩላሂ ሙሳ ከኸድር እንዲማሩ የፈለገው እሱ ዘንድ ካለው እውቀት ለሳቸውም ይሁን ለኸድር የተሰጠው በጣም ኢምንት መሆኑን ለማሳየት ነው ። ለዚህ ማሳያ በታሪኩ ላይ ከባህር ላይ የምትጠጣዋን ወፍ ምሳሌ እንዳደረገው ሁሉ ። የነብዩን ሸሪዓ በፍልስፍና ውድቅ ያደረጉና ኩፍርና ሽርክ ያነገሱ ሱፍዮችና አሕባሾች ታሪኩ በእነርሱ ላይ እንጂ ለእነርሱ መረጃ አይሆናቸውምና በደንብ እንወቀው ። አላህ ካለ ሠዒድ ኢብኑ ጁበይር ከዐብዱላሂ ኢብኑ ዓባስ ዐብዱላሂ ከኡበይ ኢብኑ ካዕብ ይዘው ባስተላለፉትና ኢማሙል ቡኻሪይ በዘገቡት ሐዲስ ላይ እንደተዘገበው ሙሉ ታሪኩን የምናይ ይሆናል ። በሱረቱል ካህፍ ላይ ይህ ታሪክ ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን በአቀማመጥ ሐዲሱ ላይ የመጣው ይበልጥ ቀለል ስለሚል የሐዲሱን እናያለን ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 14
ግማሽ ቃል እንኳን ቢሆን… ——— አንድ የስሜት ባለ ቤት የሆነ ሰው ለአዩብ አስ-ሲክቲያኒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አላቸው:- “አንድ ጥያቄ ልጠይቀህ? አላቸው፣ በእጃቸው ጭምር አይሆንም ግማሽ ቃል እንኳን ቢሆን እያሉት ዘወር አሉበት።” [ሲየር አዕላም አንኑበላእ ሊዘሀቢይ 11/285] : ሰለፎቻችን በዲኑ ላይ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ ከኛ በላይ ያላቸው ከመሆናቸውም ጋር ከቢድዐህ ባለቤቶች አንዲትም ቃል በል እንዲያውም ግማሽ ቃል እንኳ ቢሆን ላለመስማት በዚህ ደረጃ ይርቁ (ይጠነቀቁም) ነበር። ታዲያ የቢድዐህ ባለቤቶች ብዥታቸውን የሚረጩባቸው ሚዲያዎችና መድረኮች የሚያነፈንፉ እዚህ ግባ የሚባል እውቀት የሌላቸው ምስኪን ወንድምና እህቶች ደግሞ ምን ይባላሉ?!፣ አላህን ፍሩ!! ነው የምንላቸው፣ እውነተኛ ሰለፊይ ነኝ ካላችሁ ከኢኽዋንና ከሙመይዐህ ማህበራዊ ሚዲያ ስር ውጡ!! ✍🏻ኢብን ሽፋ #join ⤵️ ቴሌግራም https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Show all...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

👍 7👌 1
🟢“ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ ” ለነሲሃ ቲቪ ተፃፈው የተባለው “በመውሊድ ስንጨፍር በካሜራ ቅረፁን” አይነት ደብዳቤ አሳዛኝም አስተማሪም ነው። 👉አሳዛኙ በሱና ማማ ከፍ ካሉ በኋላ ወድቆ ለሙብተዲዕ መሳለቂያ መሆን እጀግ ያሳዝናል። እነ አጅሬ "ነሲሃዎች" ከዚህ በፊትም በርካታ የተጠለፉባቸው ወጥመዶች በደብዳቤ የጀመሩ ናቸው። ከሱፊዮችና መሰሎቻቸው ጋር በተለያዩ የሙጃመላ መድረኮች ላይ ስለሚተዋወቁ ነው የተናቁት ። “ ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ ” እንደሚባለው ነው። በሱና ላይ የነበራቸው አቋም እንደቀለጠ ከጀይላን ጀምሮ ወዳጅም ጠላትም ነገራቸው ። ከዚህም በከፋ ጉዳይ እንደለመዱት እንተባበር ይሉ ይሆናል። 👉አስተማሪው 1️⃣አቋም በወረደ ልክ በጠላት መደፈርና ውርደት ይመጣል ።የአላህ እርዳታም ይርቃል። عَنْ ثَوْبَانَ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " يُوشِكُ الْأُمَمُ أَنْ تَدَاعَى عَلَيْكُمْ كَمَا تَدَاعَى الْأَكَلَةُ إِلَى قَصْعَتِهَا ". فَقَالَ قَائِلٌ : وَمِنْ قِلَّةٍ نَحْنُ يَوْمَئِذٍ ؟ قَالَ : " بَلْ أَنْتُمْ يَوْمَئِذٍ كَثِيرٌ، وَلَكِنَّكُمْ غُثَاءٌ كَغُثَاءِ السَّيْلِ، وَلَيَنْزِعَنَّ اللَّهُ مِنْ صُدُورِ عَدُوِّكُمُ الْمَهَابَةَ مِنْكُمْ، وَلَيَقْذِفَنَّ اللَّهُ فِي قُلُوبِكُمُ الْوَهْنَ ". فَقَالَ قَائِلٌ : يَا رَسُولَ اللَّهِ، وَمَا الْوَهْنُ ؟ قَالَ : " حُبُّ الدُّنْيَا وَكَرَاهِيَةُ الْمَوْتِ ". أخرجه أبو داود (4297) وصححه الألباني ሰውባን አሉ ፥ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ)አሉ፦" የጥመት ህዝቦች (ለጥቃት) ሊጠራሩባችሁ ይቀርባሉ ፤ ልክ በላተኞች ተሻምተው ወደ ሚበሉት ማዕድ እንደሚጠራሩት ።" ጠያቂ እንዲህ አለ ፥ ያኔ በቁጥር አናሳ በመሆናችን ነውን ? ነቢዩ (ﷺ) አሉ ፦ " እንዲያውም የኔ ብዙ ናችሁ ፤ ነገር ግን እንደ ጎርፍ ግሳንግስ ደካማ ናችሁ ፤ አላህም በእርግጥ ከጠላቶቻችሁ ልብ ውስጥ ለእናንተ የነበራቸውን ክብር ነቅሎ ያስወጣል ፤ አላህም በእርግጥ በልባችሁ ውስጥ ውርደትን ይጥልበታል ።" ጠያቂ እንዲህ አለ ፥ ከምን የመጣ ውርደት ነው ? ነቢዩም (ﷺ) አሉ ፦ "የዱንያ ውዴታ እና ሞትን መጥላት (አኺራን መርሳት) ።” 2️⃣ለጠላት ማባበያና ማቀራረቢያ አንዴ በር የከፈተ ዲኑን እና ክብሩን ለአደጋ አጋልጧል። ከዕብ ኢብኑ ማሊክ ከገሳን ንጉስ የመጣለትን ማባበያ ደብዳቤ ምን ነበር ያደረገው ⁉️ ✍  ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊያ) http://t.me/Abuhemewiya
Show all...
🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍

የጠራ እውቀት ከተቃና አቐምና ተግባር ጋር የተረዘቀ ታድሏል !!

👍 6
07_مَتْن_الآجُرُّومِيَّة_فِي_النَّحْو.mp36.67 MB
👍 3
كتب وأبحاث للشيخ أبي حازم -حفظه الله تعالى ونفع به-: الآيات البينات في كشف حقيقة الموازنات بين الحسنات والسيئات - الطبعة الثالثة. #كتب_وأبحاث
Show all...
الآيات_البينات_في_كشف_حقيقة_الموازنات_3.pdf9.87 MB
19 شَرْح الأُصُول الثَّلَاثَة.mp323.29 MB
👍 4
👉  መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ       የሽርክ አንጋሾች ህብረተሰቡን የሽርክና የቢዳዓ መርዛቸውን ሶደቃና ድሀን መርዳት በሚል በወሰን ማለፍ ስንኞች በጥብጠው ለማጠጣት ይታትራሉ ። ለመሆኑ የተራቡትን ለማብላት የተቸገሩትን ለመርዳት አመት መጠበቅ ከየት የመጣ አስተምሮ ነው ። የነብዩ ታሪክ ለዲኑ የከፈሉት ዋጋ ለሙስሊሙ ለማስረዳት አመት መጠበቅ ከየት የመጣ ፈሊጥ ነው ? ምእራባዊያን የነብዩን ዲን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዲደርስ ለማድረግ ባጀት የሚመድቡ ይመስለሀል ወይስ አስተምሯቸውን አጥፍቶ ሙስሊሞችን በዝንባሌና ስሜት ባህር ሊያንሳፉፏቸው ?      መውሊድ የፈለክኸው ስም ብትሰጠው የኢስላም መገለጫ አይደለም ። እኛ መውሊድ ማክበር ክልክል ነው የምንለው ነብዩ ስላልሰሩትና ስላላዘዙበት ብቻ አይደለም ። ይልቁም የሽርክና ቢዳዓ መናኻሪያ ስለሆነና አላህ የሚታመፅበት በመሆኑ እንጂ ። የመውሊድ አክባሪ የስሜት ተከታዮች ለዚህ የጥመት ተግባራቸው ማጣፊያ የሚያነሱዋቸው ብዥታዎች በመሻኢኾች ምላሽ የተሰጠበት ቢሆንም የሀገራችን የዚህ ተግባር እንባ ጠባቂ አክቲቪስቶች ለሚያነሷቸው የተወሰኑ ማምታቻዎች አላህ ካለ መልስ የሚሰጥ ይሆናል ።       እነዚህ አካላት ይህን ፀረ ኢስላም የሆነ ተግባር በማህበረሰቡ ልቦና ቦታ እንዲኖረው ለማድረግ ዶክመንተሪ በመስራት ድሀ የሚረዳበት ዘመድ የሚጠየቅበት ሙስሊሞች የሚዘያየሩበትና የሚደጋገፉበት ነው በማለት ከልካዮቹን የእነዚህ መልካም እሴቶች አፍራሽ አድርገው ለመሳል ይሞክራሉ ።     ይሁን እንጂ መውሊድ ማክበርን የሚቃወሙ ሊቃውንቶች ኢስላምን ወደ ጥንቱ የነብዩና የሶሓቦች አስተምሮ በመመለስ በቁርኣንና ሐዲስ የሰለፎችን ግንዛቤ ሚዛን በማድረግ መተግበር አለብን ነው የሚሉት ። በዚህ መርህ ደግሞ ከላይ በዶክመንተሪ የሚታዩት እሴትች እንደየአቅሙና ችሎታው የእለተእለት ተግባር እንዲሆኑ እንጂ አመት እየጠበቁ ለሚሰራ ኢስላምን ለሚንድ ተግባር ሽፋን መስጫ እንዲሆኑ አይፈቅድም ። በመሆኑም የዚህ አይነቱን ኢስላም የማያውቀው ተግባር በስም ማሽሞንሞን እውነታውን ሊቀይረው አይችልም ። መውሊድ ማክበር ምንም ቢባል ቢዳዓ ነው ኢስላም አያውቀውም ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 14
የመውሊድ ምግብ መብላት ➪➩➪➩➪➩➪➩➪➩➧ ⁉️ጥያቄ፦ አንድ ሰው መውሊድ እንደማይቻል እያወቀ ግን በአሉን ሳያከብር ምግቡን ቢበላ ምን ችግር አለው? ↪️ መልስ፦ እንደሚታወቀው በኢስላም ሸሪዓ የመውሊድ በአል የሚባል ነገር አንዳንድ መሀይማን የፈበረኩትና የፈጠሩት እንጅ ከሶሀቦች አንስቶ እስከ ታቢዕዬችም ድረስ የማይታወቅ መጤ ቢድዓ ነው።ለዛም ነው ይህ ቢድአ ከታየበት ጊዜ አንስቶ የዲኑ ሊቃውንቶች በቦታና በጊዜ ሳይገደቡ ሲያጥላሉትና ከሰዎችም ሲያስጠነቅቁት የነበረው። ☑️ ታዲያ በዚህ መጤ በአል ላይ አንዳንዶች ስለ ረሱል - ﷺ - የውልደት ታሪክና በዛ ዙሪያ የተዘጋጁ ግጥሞች በማቅረብ ቢያሳልፉትም አብዛህኞቹ ግን ለዚሁ ቀን ተብሎ ከደሀውም ጭምር ከተለያዩ ሰዎች በግዴታነትም ይሁን በውዴታነት ገንዘብ ሰብስበው ምግብ እያዘጋጁ ለታዳሚው የሚያቀርቡበት ቀን ነው። ታዲያ እዚሁ በአል ላይ በርካታ ሀራም የሆኑ ነገራቶች (ለምሳሌ የወንድና የሴት መቀላቀል ፣ ዘፈኖችና ጭፈራዎች) ከመፈፀማቸውም በላይ ሽርክያቶችም ጭምር (ለምሳሌ ነብዩን - ﷺ - ድረሱልን ማለት ፣ መጣራት ፣ መለመንና ቦታው ላይ በአካል እንደተሳተፉ ማሰብ እና ሌሎችም) በሰፊው የሚስተናገዱበት በአል ነው። ☑️ ታዲያ በዚህ አይነቱ የሽርክ መነሀሪያ ላይ የሚዘጋጀውን ምግብ መመገብም ሆነ ቦታው ላይ መገኘትና መሳተፍ ብሎም በየትማውም ስራ ላይ ማገዝ ቢድዓቸውን ህያው በማድረግ ላይ እንደማገዝና እንደመተባበር ፣  አሏህንም ከማመፅ ጭምር ነው። ምክንያቱም አሏህ እንዲህ ይላልና: "በመልካምና አሏህን በመፍራት ተባበሩም ፣ በወንጀልና በጠላትነት ላይ አትተባበሩም"              ሱረቱል ማኢዳህ፣ 4                  •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈• 🗂 ምንጭ📗 አልቢዳያ ወንኒሀያ ለኢብኑ ከሲር ፣ 13 /137 📘 መጅሙዑል ፈታዊ ለኢብኑ ባዝ ፣ 9/74 📕 አልበያን ለአኽጧኢ በዕዱል ኩታብ ለሸይኽ ፈውዛን ፣ 270-268 📱👇👇👇👇👇 https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy
Show all...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

👍 22
👉    86 ገፅ ፅፈናል ‼        ነሲሐዎች ከአመታት በፊት መጅሊሱን በአዋጅ ለማፅደቅ ከኢኽዋን ሱፍይና አሕባሽ ጋር እንዲደመሩ ጥሪ በተደረገላቸው ጊዜ ለሙስሊሞች ይጥቅማል ብለን 86 ገፅ ፅፈን ለኮሚቴው አቅርበናል ። ነገር ግን አንድ ገፅ እንኳን መፃፍ ያልቻሉ አካላት በዚህ ይወቅሱናል በጣም ይገርማል እያሉ መጅሊሱ እነርሱ በፃፉትና ለሙስሊሞች ይጠቅማል ባሉት የሚመራ በማስመሰል በሙሪዶቻቸው አማካይነት ዳንኪራ ሲያስደልቁ ነበር ። በዚህ 86 ገፅ ውስጥ ምን እንዳለ የሚያውቁት የፃፉትና እንደጠዋትና ማታ አዝካር የሸመደዱት ሙሪዶቻቸው ናቸው የሚያውቁት ። ለኮሚቴው የቀረበው ፁሑፍ ግን ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ነው የተጣለው ።       መጅሊሱ እየተመራ ያለው በፍልስፍናና በሰው ሰራሽ ህግ ነው ። አቡበከር አሕመድ ዲሞክራሲ ከተከበረ እምነቴ ተከብሮልኛል ብሎ እንዳወጀው ማለት ነው ። ‼ ይህ ኢኽዋኖች የሙስሊሞቹን ናላ እያዞሩበት ያለው መጅሊስ የሚመሩት አካላት መርሀቸው ዲሞክራሲ ያደረጉ መሆኑ የመጅሊሱ ወንበር ላይ በወጡ ማግስት የፈለገ መውሊድ ያውጣ የፈለገ ጫት ይቃም ይህን መከልከል ነገር መፈለግ ነው ብለው በሰጡት መግለጫ ግልፅ አድርገዋል ። ይህ እንግዲህ የሽርክና የቢዳዓ መናኻሪያ የሆነውን መውሊድ መከልከል መርሀቸውን የሚፃረር እንደሆነ ሲገልፁ ነው ። በአሁኑ የመጅሊስ አመራሮች መግለጫ ግን ሓሚድ ሙሳ በግልፅ ቃል በቃል መርሀችን መሆኑ እንዲታወቅ እንፈልጋለን ብሎ ከማስቀመጡ በፊት በውስጥ ታዋቂ ነበር የሚታወቀው ። የ86 ገፅ ባለቤቶቹ ነሲሓዎች በመጅሊሱ ውስጥ ሆነው ቁርኣንና ሐዲስን የሚቃረን ሽርክና ቢዳዓን የሚያነግስ መመሪያ ሲወጣና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ በመግለጫ ሲገለፅ አይቶና ሰምቶ ተስማምቶ ከማሳለፍ ውጪ ሚና የላቸውም ። እያሉ የሞቱ በስማቸው ሽርክና ቢዳዓ እንዲነግስ የፈቀዱ በሰለፍያ ስም ወጣቱን ለሱፍይና አሕባሽ ግብኣት የሚያደርጉ ናቸው ። የኩፍር ንግግር እየሰሙ, የሽርክ ተግባር እያዩ አላየንም አልሰማንም ብለው አውቀው የተኙ ናቸው ። ከዚህ የሚከፋው ኢኽዋኖች እንደ በግ እየጎተቱ ወስደው በሚፈልጉት መድረክ ላይ አብረው እንዲቀረፁ እያደረጉ ከኛ ጋር ናቸው ብለው ሲያስተዋውቁ ይህን እንደ ስልጣኔ በመቁጠር ከኋላቸው እያለከለኩ መሮጣቸውን መቀጠላቸው ነው ። በ86 ገፅ ሽምደዳ ናላቸው የዞረ ሙሪዳቸው ግድፈታቸውን ላለማየትና ላለመስማት ምሎ ቃል የገባ ይመስላል ። ባይሆንማ ኖሮ የአዩሁድ ርዝራዦች የኢስላምን መርህ ለመናድና እስልምናና ሙስሊሞችን ለማራራቅ የጀመሩትን ኩፍርና ሽርክ በግልፅ የሚለፈፍበትን መውሊድ ከሙስሊሞች በሚሰበሰብ ገንዘብ ባጀት መድቦ ሲከበር ዝም ሲሉ እንዳላየ ሆነው አብረው ለመስለሓ በሚል ሲተሻሹ እያየ ዝም አይልም ነበር ። ኧረ ለመሆኑ ያ የቀራችሁት ኪታብ የት ሄደ ? ኪታ ተውሒድ ፣ አል ኢርሻድ ፣ ዐቂደቱል ዋሲጢያ ፣ መሳኢሉል ጃሂሊያና ከሽፉ ሹቡሃት የመሳሰሉት የት ደረሱ ? ወይስ የመጅሊስ አመራሮች 86 ገፆቹን ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ሲከቱ እናንተም የቀራችሁትን ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ከተታችሁት ? ከዚህ በላይ እየአንዳንዱ አንቀፅ ተውሒድን ከማስረፅና ሽርክን ከማውገዝ የማይለየው ቁርኣንስ የት ደረሰ ? አሕባሹ በመርሁ ላይ ሆኖ ሱፍዩ በመርሁ ሆኖ ትላንት ተውሒድ ተውሒድ እያላችሁ መውሊድን ስታወግዙ የሽርክና ቢዳዓን እንዲሁም መዕሲያን ወደነዚህ አዳራሽ ነው እያላችሁ ደም ስራችሁ ተገታትሮ ስታደርጉት የነበረው ዳዕዋ ምነው ከዳችሁ ? ለማንኛውም እኛ 86 ገፅ አይደለም 86 ሺ ገፅ ብትፅፉም ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ እንደሚከተት እናውቅ ስለነበረ ነው በሱና ተርኪያ ( መተው በሚባለው ሱና ) የሰራነው ። በባጢል ላይ የተመሰረተ አንድነት ባጢል መሆኑ ግልፅ ነው ። መርህ ያለገናኘው ስብስብ መጨረሻው ድብድብ ነው የሚሆነው ። ድብድቡ በመርህ ቢሆን ጥሩ ነበር ነገር ግን በብርህ ነው የሚሆነው ። ለማንኛውም እኛ አላህ እንዲመሰክርልን የምንለምነው ከእነዚህ ሸሪዓን ከሚወጉ የመጅሊስ አመራሮች ወደ አላህ የጠራን መሆናችንን ነው ። ነሲሓዎች መዝሀባቸው የባጢኒዮች ( ሸሪዓ ውስጣዊና ውጫዊ ትርጉም አለው) የሚሉና በውጫዊው መስራት ኩፍር ነው ውስጣዊው ደግሞ የሚያውቁት የኛ መሪዮች ናቸው እንደሚሉት ካልሆኑ በስተቀር እየሰሩት ያለው ተግባር በምንም መመዘኛ ለእስልምና መስላሃ የለውም ። ጥሪያችን ለነሲሓ ሙሪዶች ሞት መጥቶ ከንቅልፋች ከመቀስቀሳችሁ በፊት ንቁ የሚል ነው ። አላየንም አልሰማንም ብትሉም ምላሳችሁ ተይዞ የሰራ አካላታችሁ ይመሰክርባችኋል ። በእስልምና ሀጢያትህን አስምርልሀለሁ የሚል የነፍስ አባት የለም ። ማንም ለማንም አይጠቅምም ። ከነ አቡበከርና ካሚል ሸምሱ ጋር እየዞረ መድረክ የሚያሞቀው ሸይኻችሁ እንኳን ለናንተ ሊሆን ለራሱም ጥያቄ ይጠብቀዋል ። ነፍሳችሁን ወደ አላህ በመመለስ ከሽርክና የቢዳዓ አካላት በመራቅና በማስጠንቀቅ አድኑ የሚል ነው ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 12
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.