cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ

የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው። 📞 0974163424 ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1 ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ። ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)

Show more
Advertising posts
52 584
Subscribers
-2224 hours
-1907 days
-69530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
210👍 147🥰 67🙏 56👏 8🤩 3
Photo unavailableShow in Telegram
373🙏 100👍 71🥰 29🎉 21👏 15
Photo unavailableShow in Telegram
226👍 146🥰 39🙏 32🕊 17👏 7
➕➕ የእግር እብጠት➕➕ 🖲 ሁለት እግር አንድ ላይ የሚያብጥ ከሆነ አንዳንዴ ጥሩ ምልክት አይደለም፣ 🖲 ለወራት የሚቆይ ተቅማጥ ፣ የጉበት ችግር፣ የኩላሊት በሽታ፣ እና የልብ ድክመት ሲኖር፣  ከተለያዩ ተጓዳኝ ምልክቶች ጋር ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል። 🖲 እብጠቱ በኩላሊት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ፣ በእግር ላይ እብጠት ከመጀመሩ በፊት፣ የአይን ዙሪያ እብጠት ይኖራል 🖲 በልብ ህመም ምክኒያት የሚመጣ የእግር እብጠት፣ እንደ ደረጃው ራስ መሳት፣ አቅም ማነስ፣ ሳል እና አየር ማጠር ሊኖረው ይችላል 🖲 የእግር እብጠት በጉበት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ ደሞ፣ ሆድ ማበጥ እና የአይን ቢጫ መሆን ሊከሰት ይችላል። 🖲 አንዳንዴ ደሞ፣ የከፋ የጤና ችግር በሌለበት ሁኔታም፣ አንድ ሰው ላይ የእግር እብጠት ሊያጋጥም ይችላል። 🖲 ለምሳሌ፣ ነብሰጡር ሴት ላይ እርግዝናው እየገፋ ሲሄድ፣ ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል፣ 🖲 ውፍረት የሚታይበት ሰው በቀን ውስጥ ረጅም ሰአት የሚቆም ከሆነም፣ እግር ሊያብጥ ይችላል። 🖲 አብዛኛውን ግዜ እድሜያቸው ከ 50 በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ፣ ከደም ስር ድክመት ጋር በተያያዘ ሁኔታ፣ ሁለቱም እግር ላይ እብጠት ሊፈጠር ይችላል። ⭕️ ታዲያ አንድ ሰው ላይ የሚታይ የእግር እብጠት ፣ በምን ምክኒያት እንደመጣ እንዴት መለየት ይቻላል 👉የእግር እብጠትን በተመለከተ ከነህክምናው ሰፋ ያለ መረጃ ዩቲዩብ ላይ አስቀምጫለሁ። ▶️የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። 👇👇👇👇👇 https://youtu.be/KeBT-mfwqiQ
Show all...

👍 179 51🥰 22🙏 21🤩 13
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
262🙏 112👍 59🥰 29👏 16👌 9🕊 9🎉 8🤩 6
ዶ/ር ሐይለልዑል ለሚሰራው ድንቅ የበጎ አድራጎት ስራ ድምፅ እንሁነው።
Show all...
👍 22 2🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዉድ ተከታዮች ዛሬ እገዛቹ ያስፈልገኛል በፌስቡክ የስራ ፈጠራ ዉድድር ተዘጋጅቷል ።በዉድድሩ ተሳታፊ ስለሆንኩኝ ከታች ባስቀመጥኩት ሊንክ እየገባችሁ "አንዴ እናዉራ" የሚለዉ ምስል ላይክ 👍 በማድረግ ይምረጡ አመሰግናለሁ🙏 👇👇👇 https://www.facebook.com/100002028524680/posts/pfbid02n9vd4WoU6biznHeXBFcu4DvEmrRCgMcxwVmQQU4tfMcsAb5maWnudgTS7gESQ2YHl/?app=fbl
Show all...
👍 89👏 4
➕➕ የነርቭ ህመም ➕➕ 🖲የነርቭ ህመም፣  በአንድ የህመም ምልክት ብቻ የሚገለፅ ህመም አይደለም፣ እንደ ቦታው እና እነደ ነርቭ ጉዳቱ ደረጃ፣ በተለያየ አይነት የህመም ምልክቶች ይገለፃል። 🖲መቆጥቆጥ፣ ማቃጠል፣ መለብለብ ፣መደንዘዝ ፣መዛል ፣ እና ከአቅም ማጣት ጀምሮ እስከ ራስ መሳት ድረስ ሁሉ ያሉ የህመም ምልክቶች ፣በነርቭ ህመም ተጠቂዎች ሊገለፁ ይችላሉ። 🖲ነርቭ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ፣ አንዳንዴ፣ በህክምና እንኳን መመለስ ስለማይቻል ፣ ብዙ ሰዎችን ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት ይዳርጋል። 🖲ጉዳቱ አነስተኛ ከሆነ ደሞ፣ እንደ ተጎዳው ነርቭ  እና፣ ጉዳቱን እንዳስከተለው በሽታ፣ በህክምና ፣ ወደነበረበት መመለስም ይቻላል። 🖲አንድ ሰው ላይ፣ ባጋጣሚ ከሚደርስ አደጋ አንስቶ በቂ ክትትል በሌላቸው ስር ሰደድ በሽታዎችም ጭምር የነርቭ ህመም ሊጀምር ይችላል። 🖲አንድ ጤናማ ሰው ላይ ያለ የነርቭ አካል አፈጣጠር በአቀማመጡ በሁለት ይከፈላል፣  ማእከላዊ የነርቭ አካል እና ውጫዊ የነርቭ አካል። 🖲ማእከላዊ የነርቭ አካል ማለት፣ አይምሮ እና ሀብለ ሰረሰር ናቸው። ውጫዊ የነርቭ አካሎች ደሞ፣ ከአይምሮ እና ከ ሀብለ ሰረሰር የሚነሱ የነርቭ መስመሮች ናቸው። 🖲አይምሮ ውስጥ ያሉ የነርቭ ህዋሶች በከፍተኛ ደረጃ ሲጎዱ ራሳቸውን መልሶ የማደስ ብቃታቸው አነስተኛ ስለሆነ አይምሮ ላይ የሚደርስ ጠንከር ያለ የነርቭ ጉዳት ሲኖር ዘላቂ ለሆነ ወይም በህክምና ለማይመለስ የአካል ጉዳት ሊዳርግ ይችላል። 🖲ከአይምሮ እና ከሀብለሰረሰር ውጪ ያሉ የነርቭ መስመሮች ደሞ፣ እንደ ጉዳት ደረጃቸው ራሳቸውን የማደስ የተወሰነ አቅም አላቸው። 🖲አብዛኛውን ግዜ፣ ቀለል ያለ እና መካከለኛ የጉዳት ደረጃ የደረሰባቸው ከሆነ በግዜ ሂደት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚያገግሙ ይሆናሉ። 🖲ነገር ግን፣ አንዳንዴ እነዚህ የነርቭ መስመሮች ላይ የሚደርሰው አደጋ ከፍተኛ ከሆነ፣ ጉዳቱ የነርቭ መስመሮቹ ራሳቸውን ከሚያድሱበት አቅም በላይ ስለሚሆን ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት ሊዳርጉ ይችላሉ። 🖲የነርቭ ህመም በተለያዩ አደጋዎች እና የውስጥ ደዌ በሽታዎች ምክኒያት ሊከሰት ይችላል፣ የነርቭ ህመሙ በአደጋ ምክኒያት ሲጎዳ፣ ነርቩ ሊጨፈለቅ፣ በከፍፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሊቆረጥ ይችላል። 🖲ስርሰደድ በሽታዎችን ተከትለው የሚመጡ የነርቭ ህመሞች፣ ለምሳሌ፣ የስኳር በሽታን ተከትሎ የሚመጣ የነርቭ ህመም፣ ከእይታ ድክመት ጀምሮ እንደ ደረጃው በብዙ መንገድ ሊገለፅ ይችላል፣ 🖲ነገር ግን አብዛኛውን ግዜ ፣ ከጉልበት በታች በሁለቱም እግር ላይ የሚሰማ የመለብለብ እና የማቃጠል ስሜት በተለይ ከመሀል እግር ጀምሮ ወደላይ ከፍ እያለ የሚሄድ የህመም አይነት ይሰማቸዋል። 🖲ከዚህ ውጪ ፣ ለምሳሌ፣ በአልኮል ጥገኝነት፣ በቫይታሚን ቢ እጥረት፣ በመመረዝ፣ በታይሮይድ ህመም እና በተለያዩ ኢንፌክሽኖችም ጭምር የሚመጡ ሌሎች አሳሳቢ የሆኑ የነርቭ ህመም አይነቶችም አሉ። ⭕️የነርቭ ህመምን በተመለከተ፣ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ፣ የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ መመልከት ትችላላችሁ። መልካም ግዜ!! 👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/ASL4flPnaU4
Show all...

👍 105 35🥰 23🙏 16
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.