cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

የብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እና የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ እንዲሁም የሌሎች መምህራን ትምህርቶች፣ ስብከቶችና ተግሳጾች በተጨማሪም በሀገረ ስብከቱ የሚከወኑ ዓበይት ክንውኖች የሚተላለፉበት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የቴሌግራም ቻናል ነው። የቻናሉ ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በመጋበዝ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ያፋጥኑ።

Show more
Advertising posts
5 663
Subscribers
-1024 hours
-67 days
-6130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

https://youtu.be/MHgkHuVXobk ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን አስከፊ ኑሮ የሚገፉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። ዛሬ አግኝተናቸው የነገሩንን ልብ የሚነካ አኗኗርና የተማጽኖ ድምጽ አሰናድተነዋል። ማኅበረ ቅዱሳን ከ230 ሽህ ብር በላይ ድጋፍ አድርገውላቸዋል።
Show all...
#News || እናቶች ጡታቸው ደርቋል|| የተፈናቃዮች እሮሮ

👏 7
😢 5👍 2
የማኅበረ ቅዱሳን ወልድያ ማዕከል የዘመን መለወጫ በዓልን ከተፈናቃይ ወገኖች ጋር አከበረ፡፡ የማኀበረ ቅዱሳን ወልድያ ወረዳ ማዕከል የ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በወልድያ ከተማ በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ከሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ጋር አክብሯል መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ) መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው በዚሁ መርሐ ግብር የወልድያ ወረዳ ማዕከል ተወካይ አቶ ገደፋው ሙላው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ወረዳ ማዕከሉ የወልድያ ከተማ በጎ አድራጊ ምመናንና ተቋማትን በማስተባበር በዓልን ከእናንተ ጋር ለመዋል በመቻላችን ደስተኞች ነን፤ በቀጣይም መሰል ድጋፋችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ መጋቤ ጥበባት አክሊለ ብርሃን ተመስገን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ በመርሐ ግብሩ ተገኝተው ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡ ምንም እንኳን አሁን በችግር ውስጥ ብትሆኑም መንፈሰ ጠንካሮች መሆን አለባችሁ፡፡ ከእናንተ መካከል እግዚአብሔር ለተለየ ዓለማ የሚመርጠው ይኖራል፡፡ በምንም ምክንያት ማዘንና መተከዝ አያስፈልግም ብለዋል፡፡ ማኀበረ ቅዱሳንም የከተማዋን ነዋሪ አስተባብሮ ይህንን የመሰለ መርሐግብር ማዘጋጀቱ የሚያስመሰግን መንፈሳዊ ተግባር ነው ብለዋል፡፡ ተፈናቃይ ወገኖች በበኩላቸው እስካሁን የከተማው ህዝብ ስለሚደግፈን ብዙ አልከፋንም፡፡ በተለይ አሁን አሁን በዓላት ሲመጡ እንደድሮው ማሰብ ትተናል፡፡ ምክንያም እናንተን የመሰሉ ወገኖቻችን ችግራችንን ተረድተው እየደገፉን ስለሆነ ብለዋል፡፡ ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታላቸው በሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጠው ተፈናቃይ ወገኖች ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከ371 በላይ ተፈናቃዮች በመርሐ ግብሩ መታደማቸውን ከወረዳ ማዕከሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ መረጃው የማኀበረ ቅዱሳን ወለድያ ማዕከል ሚዲያ ክፍል ነው፡፡
Show all...
👏 4👍 1🙏 1
12🥰 2
ሰንበት ት/ቤቶች ከመዘመር ባሻገር መሠረተ ሃይማኖት ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ) መስከረም 2 ቀን 2016 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት) የወልድያ ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ትናንት መስከረም 1 ቀን የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ለሀገረ ስብከቱ ብፁዓን አባቶች የእንኳን አደረሳችሁ መርሐ ግብር አካሂዷል። ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመርሐ ግብሩ ለተገኙ የሰንበት ት/ቤት አባላት አባታዊ መልእክትና የአገልግሎት መመሪያ አስተላልፈዋል። ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማጠናከር የደከሙት ድካም ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የብፁዕነታቸውን ህልም ለማሳካት ሀገረ ስብከቱ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አብራርተዋል። መሪ እቅዱ ለይስሙላ ሳይኾን በትክክል ተግባራዊ እንዲሆን ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የሚያጠናክር የሐዲሳት መጻሕፍት ትርጓሜ መምህር የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኀላፊ አድርጎ ከመመደብ ባሻገር  5 አሠልጣኝ መምህራን በጠቅላይ ቤተክህነት መሠልጠናቸውንና ሥርዐተ ትምህርቱን ለመተግበር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ብፁዕነታቸው ተናግረዋል። የሀገረ ስብከቱና የወረዳዎች የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ለሚስተዋሉ ክፍቶች የመፍትሒ አካል እንድሆኑና አባላቱም እንድያግዟቸው አሳስበዋል። ትልቁ ሥራችን ሰው ማትረፍ ነውና ኹላችንም የጋራ ሥራ ሠርተን፥ የጋራ ውጤት ማምጣት አለብን ያሉት ብፁዕነታቸው በበዓላት ከመዘመር ባለፈ  መሠረተ ሃይማኖት ላይ በማተኮር  በእምነትም በምግባርም መጠንከርና ስለሚዘመረው ጉዳይም በቂ እውቀት ሊኖረን ይገባል ብለዋል። ክርስትናችንን ማስፋት የምንችለው መሠረተ እምነቱን ማወቅ ስንችል ነው ያሉት ብፁዕነታቸው የጸሎተ ሃይማኖትን 12 ቱን አንቀጾች መያዝና ማብራራት መቻል፣ በትምህርተ ሃይማኖት፥ በነገረ ቅዱሳን፣ በምሥጢረ ሥላሴና በምሥጢረ ሥጋዌ ትውልድን ለመቅረጽ መዘጋጀት እንዳለባቸው አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል። በማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያግኙን፤ ይወዳጁ ለሌሎችም ያጋሩ። ~ቴሌግራም፡ https://t.me/NWDnews ~ዩቲዩብ፡ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia ~ድረገጽ፡ https://eotc-nw.org ~ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/EOTCNWD?mibextid=ZbWK
Show all...
ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

የብፁዕ አቡነ ኤርምያስ እና የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ እንዲሁም የሌሎች መምህራን ትምህርቶች፣ ስብከቶችና ተግሳጾች በተጨማሪም በሀገረ ስብከቱ የሚከወኑ ዓበይት ክንውኖች የሚተላለፉበት የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የቴሌግራም ቻናል ነው። የቻናሉ ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በመጋበዝ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ያፋጥኑ።

👍 10
Show all...
እንደቀላል ነገር የሚፈሰው የሰው ልጅ ደም እንዲቆም ጸልዩ|| ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

#ተለቀቀ በወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት መዘምራን በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው #የመሪጌታ_ፀሐይ_ብርሃኑ "#የአዋጅ_ነጋሪ_ቃል" (የደናግል መመኪያ) ዝማሬ በሰንበት ት/ቤቱ የዩቲዩብ ቻናል ተለቀቀ። መስከረም 1/2017 ዓም ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ በተዘጋጀው ልዩ መርሐግብር ይመረቃልና በልዩ የበዓል መርሐግብሩ እንዲገኙ እርስዎም ተጋብዘዋል። #ሰብስክራይብ_እና_ሼር_ያድርጉ https://youtu.be/4MxTCJY82Ts?si=zmsCzXtGJx-wlIq4 https://yt.psee.ly/6ew8ln https://yt.psee.ly/6ew8ln
Show all...
🔴 NEW አዲስ ዝማሬ "ያዋጅ ነጋሪ ቃል " በወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ቤተክርስቲያን ፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት መዘምራን የተዘጋጀ

👏 5👍 1
00:30
Video unavailableShow in Telegram
#ሊለቀቅ_ነው በወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት መዘምራን በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው #የመሪጌታ_ፀሐይ_ብርሃኑ "#የአዋጅ_ነጋሪ_ቃል" (የደናግል መመኪያ) ዝማሬ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በሰንበት ት/ቤቱ የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል። መስከረም 1/2017 ዓም ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ በተዘጋጀው ልዩ መርሐግብር ይመረቃልና በልዩ የበዓል መርሐግብሩ እንዲገኙ እርስዎም ተጋብዘዋል። #ሰብስክራይብ_እና_ሼር_ያድርጉ https://youtube.com/@felegeselam27?si=YZ7g8GJyXYM2mqzk https://youtube.com/@felegeselam27?si=YZ7g8GJyXYM2mqzk
Show all...
12.65 MB
👍 2
8👍 3
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.