cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo Media

እሔ የቴሌግራም መንፈሳዊ ቻናላችን ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ምንማማርበት መንፈሳዊ መድረክ ነው። ለሌሎች ያጋሩ፣ አዳዲሶችም ተቀላቀሉ(join) አድርጉ።

Show more
Advertising posts
2 539
Subscribers
+524 hours
+197 days
+6330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
ከፖለቲካ ጋር የተጣበቀ እምነትና ባህል አገዛዙ ሲወድቅ አብሮ ይወድቃል
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ወድቀናል። የወልድያ ደብረ ሲና አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ አዳሪ ት/ቤት 15 የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ከጀመረ በዚህ አዲሱ ዓመት 5ኛ ዓመቱን መያዙ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የመጨረሻ ጊዜ ቢሆንም ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ ይህንን ማስቀጠል የማንችልበት ደረጃ ደርሰናል። በመሆኑም ይህን ጉባኤ ቤት ለማስቀጠል የሕዝበ ክርስቲያን ድጋፍ አስፈላጊ በመሆኑ የተቻላችሁን በጉባኤ ቤቱ አካውንት 1000350119117 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለመደ ትብበራችሁን ታደርጉልን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ስለ ወይዘሮ ትዕግስት ፍትሃወርቅ ሰሞኑን በብዛት እናወራለን
Show all...
🔥 1
00:15
Video unavailableShow in Telegram
😁
Show all...
4.37 MB
👍 1
መስከረም 10 - "ተቀጸል ጽጌ" ወይም "አጤ መስቀል" የኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ የገባበትን ቀን በማሰብ እንዲሁም የክረምቱን ማለቅ ምክንያት በማድረግ መስከረም 10 ቀን "ተቀጸል ጽጌ" ወይም "አጤ መስቀል" እየተባለ በነገሥታቱ ዘመን በታላቅ ድምቀት ይከበር ነበር። በዚህ ዕለት መሪዎች ለሕዝቡ፤ ሕዝቡም ለመሪዎች አበባ እየተሰጣጠ ‹‹እንኳን አደረሳችሁ›› ይባባላል። በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥትም በዓሉ ደማቅና ልዩ ድባብ ነበረው። በ1906 ዓ.ም ግን አጼ ምኒልክ ታመው አልጋ ላይ ውለው ነበርና በበዓሉ ላይ መገኘት አልቻሉም፡፡ ሆኖም እሳቸውን ተክተው በቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ አልጋ ወራሻቸው ልጅ ኢያሱ ሚካኤል፣ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ፣ መኳንንቱና ምእመናኑ በተሰበሰቡበት ‹‹ተቀጸል ጽጌ፤ ምኒልክ ሐጼጌ›› (አጼ ምኒልክ ሆይ አበባን ተቀበል) እያሉ የንጉሰ ነገሥቱን ስም ጠቅሰው ካህናቱ ሲያሸበሽቡ ሁሉም ሰው የምኒልክን ስም በመስማቱ የናፍቆት እንባ ተናንቆት ያለቅስ ነበር፡፡ በበዓሉም ላይ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ይነበብ ነበር። ‹‹ተቀጸል ጽጌ›› ማለት ‹‹አበባን ተቀዳጅ/ተላበስ›› ማለት ሲሆን፣ በዘመነ አክሱም በስድስተኛው ክ/ዘመን በነበሩት አፄ ገብረ መስቀል ዘመን የክረምት መውጫ በሆነው መስከረም 25 ቀን የሚከበር የወቅት ሽግግር በዓል ነበር፡፡ ለንጉሠ ነገሥቱ የአበባ አክሊል/ጉንጉን ይበረከትለት ስለነበር ‹‹ተቀጸል ጽጌ፤ ገብረ መስቀል ሐፄጌ›› (አፄ ገብረ መስቀል አበባን ተቀዳጅ) እየተባለ ይዘመር ነበር፡፡ ከ15ኛው ክ/ዘመን በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ግማሽ ክፍሉ (ግማደ መስቀል) መምጣቱን ተከትሎ በዓሉ ወደ መስከረም 10 ቀን ዞሯል፡፡ እስከ መጨረሻው ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ (1923 - 1967) ድረስ በዓሉ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት ሲከበር ቆይቷል፡፡ ይህ ሃይማኖታዊ በዓል በነበረዉ የመንግሥት አስተዳደር ለዉጥ ምክንያት ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ ለ20 ዓመታት ያህል ተቋርጦ ነበር። ከ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ወዲህ ደግሞ በዓሉ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዐውደ ምሕረት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አማካይነት የአበባውን በዓል ማክበሩና ለበዓሉ ታዳሚዎችም አበባን ማደሉ ቀጥሏል፡፡
Show all...
👍 1👏 1
#ነገረ #ክርስቶስ #ትምህርት #ላይ #መዘንጋት #የሌለባቸው #ጉዳዮች ፩. አምላክ ሰው የሆነው ሰውን ለማዳን ነው። ለሰው ልጆች ያለው ጥልቅ ፍቅሩን የገለጠበት ነው ሥጋዌ። ፪. አምላክ እንዴት ሰው ሆነ? የሚለውን አለማወቅ ይጎዳል። እንዴት ሰው ሆነ በሚለው ከብዙ ቤተ እምነቶች ጋር የምንለያይበት ስለሆነ ጠንቅቆ ማወቅ መልካም ነው። እንዴት ሰው ሆነ? ሀ. እንበለ ውላጤ ለ. እንበለ ሚጠት ሐ. እንበለ ኅድረት መ. እንበለ ምትሐት ሠ. እንበለ ቱሳሔ ረ. እንበለ ፍልጠት ቀ. እንበለ ቡዓዴ በ. እንበለ ትድምርት ተ. እንበለ ምንታዌ ነ. በተዋሕዶ በተዓቅቦ ነው። እኒህን አለመለየት ከክሕደት አዘቅት ያስገባል። አምላክ ሰው ሲሆን ከአምላክነቱ ተለውጦ ወደሰውነት ተቀይሮ አይደለም። አምላክ ሰው ሲሆን ሰው አምላክ ሆኗል። ሰው አምላክ ሲሆን ከሰውነቱ ተለውጦ ወደ አምላክነቱ ተቀይሮ አይደለም። "ወኢተወለጠ ህላዌ ቃል ኀበ ህላዌ ትስብእት ወኢህላዌ ትስብእት ኀበ ህላዌ ቃል። ዳእሙ ይሄልዉ ክልኤቱ ህላዌያት በበህላዌሆሙ እንበለ ውላጤ" እንዲል (ሃይ.አበ.፵፫፣፭)። በተጨማሪም ሃይ.አበ.36 ላይ "ኢያፍለሰ ፈጣሪ መለኮቶ ለከዊነ ፍጡር። ፈጣሪ ባሕርይውን ፍጡር ወደመሆን አልለወጠውም። ወኢደምሰሰ ትስብእቶ ፍጡረ ለከዊነ ፈጣሪ። የተፈጠረ ሥጋንም ፈጣሪ ወደመሆን አልለወጠውም" ተብሎ ተገልጿል። በተዋሕዶ ሰው ወደ አምላክነት አምላክ ወደ ሰውነት አልተለወጠም። እንበለ ውላጤ መባሉ ለዚህ ነው። ሰውነት ተለውጦ አምላክ ብቻ ሆኗል፣ ክርስቶስን አምላክ ብቻ፣ ረቂቅ ብቻ፣ ምሉእ ብቻ ይባላል ካሉ መለኮት ሥጋን ውጦታል የሚል የአውጣኪ ክሕደት ነው። ክርስቶስን ሰው ብቻ፣ ግዙፍ ብቻ፣ ውስን ብቻ ይባላል ካሉ ይህ የእስልምና ክሕደት ነው። አካልን አዋሕደው ባሕርይን ካላዋሐዱ የካቶሊካውያን፣ የመለካውያን ኦርቶዶክሶች (የግሪክ፣ የሩሲያ፣ የዩክሬንና የመሳሰሉት) ክሕደት ነው። አምላክ ሰው ሲሆን ወደሰውነት ተለውጧል ካሉ የሐራ ጥቃ ክሕደት ነው። አምላክ በሥጋ አደረ የሚለውን ይዘው ኅድረት ካሉ የጳውሎስ ሳምሳጢ ክሕደት ነው። አምላክ ሰው መስሎ ታየ እንጂ ሰው አልሆነም ካሉ የማኒ ክሕደት ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ክርስቶስ የሠራውን ሥራ እየለያዩ ይህ የሥጋ ሥራ ነው፣ ይህ የመለኮት ሥራ ነው እያሉ መለያየትም ክሕደት ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ያለው ሥራ የተዋሕዶ ሥራ ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ያለ አካል የተዋሕዶ አካል ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ያለ ባሕርይ የተዋሕዶ ባሕርይ ነው። ኀደረ፣ ደመረ የሚሉት ቃላት እንደ ጊዜ ግብሩ ተዋሐደ ተብለውም ሊተረጎሙ ይችላሉ። ኩሉ መለኮቱ ኀደረ በሥጋ ሰብእ ሲል ተዋሕዶን ያመለክታል። ነአምን ከመ ተደመረ ኩለንታሁኬ ለቃል ወኩለንታሁ ለትስብእት ሲል ተዋሕዶን ያመለክታል። የእኛ አስተምህሮ ተዋሕዶ በተዓቅቦ ነው። ፍጹም አንድነት ያለመለወጥ ነው። ተዓቅቦን የዘነጋ ተዋሕዶ ውላጤ ነው። ተዋሕዶን የዘነጋ ተዓቅቦ ምንታዌ ነው። ሥጋ አካሉን፣ ባሕርዩን፣ ግብረ ባሕርይውን እንደያዘ ሳይለውጥ የቃልን አካሉን፣ ባሕርዩን፣ ግብረ ባሕርዩን ገንዘብ አደረገ። ቃልም አካሉን፣ ባሕርይውን (ከዊኑን)፣ ግብረ ባሕርይውን ሳይለቅ ባሕርይውን እንደያዘ ሳይለውጥ የሥጋን አካሉን ባሕርይውን፣ ግብረ ባሕርይውን፣ ባሕርይውን ገንዘብ አደረገ። መምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስ እንቲኣሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲኣሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል ያለው ይህንን ነው። #የእግዚአብሔር #ስጦታ በሚለው መጽሐፌ ለአዳም ከተሰጡት ስጦታዎች አንዱ ሀብተ አሚን ነው። በሀብተ አሚን ሥር ነገረ ክርስቶስ የሚለውን በተጨማሪ ማንበብ ትችላላችሁ። © በትረ ማርያም አበባው 🌹የዩቲዩብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው። 🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።
Show all...
ንሕነ ዘክርስቶስ

በዚህ ቻናል ነገረ ሃይማኖትን በሰፊው እንማማርበታለን። ቻናሉ ህዳር ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ. ም ተከፈተ። ©መምህር በትረማርያም አበባው

በሊባኖስ ያላችሁ ኢትዮጵያውን ጥንቃቄ እንዳይለያችሁ።መከካለኛው ምሥራቅ የቀውስ ቀጠና ሆኖአልና።
Show all...
1.16 MB
Photo unavailableShow in Telegram
እሄው ነው የብልግና ፓርቲ ትሩፋት ያለምንም ትክ እና ካሳ የሰዎችን ቤት፣ ሆቴል እና ፎቅ ማፍረስ ሰላም አደራችሁ ውድ ኦርቶዶክሳዊያን
Show all...
💔 3
Photo unavailableShow in Telegram
EOTC TV- አይሞቀው አይበርደው - EOTC TV አይሞቀው አይበርደውም በሚል እንጅ ከተሚማ ( ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል) በላይ "የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተወከለች ተሳተፈች" በማለቱ ስህተቱ ሊነገረው የሚገባ ለአንድ ዓመት በሚልየን የሚቆጠር ገንዘብ የሚሰለቅጠው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሜንስትሪም ሚዲያ ነበር። EOTC TV በዜና መርሐ ግብር ተሚማ ካቀረበው ጋር ተመሳሳይ ዜና አቅርበዋል። ዜና ከመሥራታቸው በፊት ቤተ ክህነቱ ውስጥ ተጎልተው ቢያንስ ለማጣራት ወሬ የማያሸቱ ጋዜጠኞች አሉት። የኦሬየንታል ቤተ ክርስቲያን የተሻለ የዜና ምንጭን ለማመሳከር አይጠቀሙም። ተሚማ ይቅርታ ብሎ ማስተካከያ እንዳደረገው ከEOTC TV ብዙም ይቅርታ አንጠብቅ። ማስተካከያም እንደዚሁ። ማንን ፈርተው? ምዕመኑን ቢፈሩ ቢያከብሩ "ባሕታዊ" ገብረ መስቀልን የመሰሉ "ትንቢት ተገለጠልኝ ... በእንትን አቅጣጫ ላም ታየችኝ" የሚሉ ሕመምተኛ መፈንጫ አያደርጉንም ነበር። እንዲሁም EOTC TV በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውጭ ግንኙነት መምሪያ የሚመለከተውን አካል በሚዲያ ይጠይቃል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። በነጻነት ማሰብ ፣መጠየቅ የሚችል ጋዜጠኞች አሉ ብየ አላምንም። ሚዲያው አይሞቀው አይበርደው። ዲ/ን ዮሴፍ ፍስሐ
Show all...
🙏 4
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.