cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)

MIIDIYAA TUNBII እንኳን ደህና መጣችሁ! ይህ የኢትዮ ቱንቢ ሚድያ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው። የቱንቢ ዋና አጀንዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የሁላችንም ሀገር፣ ባለ ብዙ ፈተና እና ባለ ብዙ ተስፋ ስለ ሆነችው የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ ነው። የመረጃ፣ ማስረጃ፣ የቀጥተኛ ምልከታና መፍትሔ ተኮር ጋዜጠኝነት ቤት።

Show more
Advertising posts
2 074
Subscribers
No data24 hours
-117 days
+8330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አርቲስት አዜብ ወርቁን ያሳሰራት ወንጀሏ የሆነው ጽሑፍ እነሆ! ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት! ✍️✍️✍️…በአዜብ ወርቁ +++++++++++++++++++++++++++ "…የልማት ተነሺ ተብሎ ሰዎች ድንገት ቤታቸው ሲፈርስ ስለገጠማቸው ጉዳት ብዙ የሚያሳዝኑ ታሪኮች ሲነገሩ ሰምቻለሁ። ነገሩ ቢያሳዝነኝም፣ የስሚ ስሚ አይቼ ሳልመረምር አስተያየት ብሰጥ ሚዛናዊ አልሆን ይሆናል፣ እሳሳት ይሆናል በሚል ከማዘን በስተቀር ምንም አላልኩም ነበር፣ አሁን ግን ለልማት ድንገት መፍረስ የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት። "…የማወራው ስለአንድ ሰው ታሪክ ነው፣ ተቆጥሮ ህዝብ ስለሚባለው፣ ሀገር በማቅናት ውስጥ ማህበረሰብ በመስራት ውስጥ አስተዋጽኦ ስላለው አንድ ሰው ነው። የሕይወት ታሪኩ እንዲህ ነው ... "…ገና ጎረምሳ እያለ ከተወለደበት ገጠር ወጥቶ 250 ኪሎሜትር በእግሩ ተጉዞ አዲስ አበባ ገባ። አዲስ አበባ በግለሰቦች ንግድ ቤት ተቀጥሮ ከጽዳት አንስቶ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርቶ ከራሱ አልፎ ወላጆቹን ቤተሰቡን ረድቶ፣ ትዳር መስርቶ፣ ልጆች አፍርቶ፣ የግል ንግድ ከፍቶ ሲኖር ቆይቶ የዛሬ 60 ዓመት አካባቢ ከፈረንሳይ ኤምባሲ ወረድ ብሎ ከሃይዌዩ ድልድይ ስር የግንብ ግድግዳ ላይ “ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ” የሚለው ጽሑፍ በደማቁ በቀይ ቀለም ከተጻፈበት ፊትለፊት ወደ ቤላ በሚወስደው ቀኝ መታጠፊያ መንገድ ላይ መሬት ገዝቶ ቆንጆ ቤት ሠርቶ ኑሮውን መሰረተ። "…12 ልጆችን አሳድጎ፣ አስተምሮ ለወግ ለመዓረግ አበቃ፣ የልጅ ልጅ አየ። አሁን የ 94 ዓመት አዛውንት ነው። ጠንካራ፣ ደግ፣ ሠራተኛ፣ ተጫዋች፣ ቀልድ ዐዋቂ፣ ሰው ሁሉ የሚወደው፣ ሰውን ሁሉ የሚወድ፣ ሃይማኖቱን አክባሪ እምነቱን አጥባቂ ነው። የግቢ አትክልት ይወዳል። ግቢው በወይን፣ በአቩካዶ፣ በኮክ፣ በአፕል፣ በቡና ዛፍ የተሞላ የሚያምር ግቢ ነው። የአትክልት ፍቅሩ ለራሱ ቤት ብቻም አይደለም፤ ሰፈር ውስጥ እየዞረ በሰው ቤት በዘመድ ቤትም ችግኝ ከቤቱ እየወሰደ ይተክላል። "…ይህ ጠንካራ ሰው በቅርቡ በህመም አልጋ ላይ ዋለ። “በቂ ኖሬያለሁ ሆስፒታል እንዳትወስዱኝ በኖርኩበት ባረጀሁበት ቤት አስከሬኔ ይውጣ” አለ። ልጆቹ ቃሉን አከበሩለት ቤቱ ውስጥ እንዳለ ሀኪም እያየው በልጆቹ፣ በልጅ ልጆቹ በቤተዘመድ በጎረቤት ተከቦ እንዲያስታመሙት አደረጉ። ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የአዲስ ዓመት ዋዜማ በሰፈሩ አንድ ዜና ተሰማ። ከወረዳ የመጡ ሰዎች እየዞሩ ለልማት እየመዘገቡ ነው የሚል። "…የአዲስ ዓመት በዓል ማግስት መስከረም 2 መጥተው በ20 ቀን ውስጥ ቤታችሁ ለልማት ሊፈርስ ስለሆነ ለመስከረም 3 ጠዋት ለስበሰባ ኑ የሚል መልእክት በቃል ብቻ ተነገረ። እንዲህ ያለ ዱብ እዳ ሲሰማ ለሕግ ጉዳይ መዋሉ ቢቀር እንኳን ህልም ይሆን እንዴ ብሎ ድጋሚ ዓይቶ ለማረጋገጥ የሚያስችል ብጣቂ ወረቀት አልተሰጠም። ልክ እንደ ክፉ መርዶ ነጋሪ በር አንኳኩተው በቃል ትእዛዝ ሰጥተው ሄዱ። "…መስከረም 3 በስብሰባው ላይ ስልክም ሆነ ማንኛውም ድምጽ እና ምስል መቅጃ ይዞ መግባት ባልተፈቀደበት ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢዎቹ ቤታችሁ ለልማት ይፈርሳል የሚለው መርዶ ተነገራቸው። • ለምን? ~ ለጫካ ፕሮጀክት ልማት። • መቼ? ~ እስከ መስከረም 20። "…ተሰብሳቢው ደነገጠ። “ልጆቻችንን ትምህርት ቤት አስመዝገበናል፣ ዩኒፎርም አሰፍተናል፣ የደከመ ታማሚ ቤታችን ስላለ ጊዜው አይበቃንም፣ የዕለት ጉርሴ ከቤት ኪራይ የማገኘው ብቻ ነው፣ ምን ልሁን? የሚሉ አዛውንቶች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ጮኸው አልቅሰው ተናገሩ። ሁለት ሳምንት አላችሁ ተባሉ። • ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃል?? "…በየቤቱ ያለ እቅድ፥ ያለ ኑሮ... ለቅሶ፣ ጽኑ ታማሚ፣ ሰርግ፣ አራስ፣ የደረሰች ነፍሰጡር....ቤቱ ይቁጠረው። ሁለት ሳምንት ለምን ይበቃል? ምንድነው ጥድፍድፉ? ልማት ታስቦ እንደሆነም እኮ በረጅም ጊዜ እቅድ ላይ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ሊቀመጥ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ሰው ነው። "…ነዋሪው እንዴት ይነሳ? ወዴት ይሂድ የሚለው እንጂ ትግበራ ከተጀመረ በኋላ በመጨረሻው ሰዓት ለነዋሪው በቀናት ውስጥ ትነሳለህ ብሎ በቃል መንገር እንዴት? ሰው ያነሰ ቅድሚያ ነው የሚሰጠው? ልማቱ ለሰው ነው አይደል?? "…ይህ ቤተሰብ የመራ፣ ሀገር ያቀና፣ ስንቱን ያስተማረ፣ የዳረ፣ አስታሞ በክብር የቀበረ፣ የተጣላን አስታራቂ የሐገር ሽማግሌ፣ አልጋ የያዘ መንቀሳቀስ፣ መንቃት የማይችል፣ ፈጣሪው ጋ እስኪሄድ ቀኑን የሚጠብቅ አረጋዊ እስከ መስከረም 20 ይነሳ ቤቱ ይፈርሳል ተባለ። "…እንዴት ይሄድ? የት ይሂድ? በኖረበት ሰፈር ባቋቋምው እድር፣ በሚወደው አብሮ በኖረው የሰፈር ሰው ላይሸኝ? የሀገር ትርጉም ሲነገር “አባት የሞተ እንደሁ በሀገር ይለቀሳል” አልተባለም ነበር እንዴ? እና ለአባት የሚለቅሰበት፣ ለቅሶ የሚቀመጡበት ሀገር የለም?? "…ልማት ማንም አይጠላም፣ ማማር፣ መታደስ ማንም አይጠላም። የሰው ልጅን ግራ ሲያጋባ ለድንገተኛ ስጋት ሲዳርግ፣ ሰው ሁሉ የኔስ ተራ መቼ ይሆን እያለ በጭንቀት እንዲኖር ሲገደድ፣ ክብርን ሲነካ፣ ሰውነትን ሲያፈርስ ግን አዎን ልማት ይጠላል!! "…ይሄን ጽሑፍ የምታዩ የልማት ደጋፊ ነን ባዮች ኮመንት ላይ መጥታችሁ፣ "እና ሀገር አይልማ? ሀገር ሲለማ አይናችሁ የሚቀላ፣ የልማት አደናቃፊዎች" ትሉ ይሆናል። እውነቱ ግን የልማት አደናቃፊ እናንተ ናችሁ። "…እንደግፈዋለን የምትሉት ልማት በሰዎች እንዲጠላ፣ ሰው እንዲያለቅስበት፣ የምትታትሩ ዛሬን እና ሆዳችሁን ብቻ የምታዩ፣ ከሆዳችሁ ውጪ ሌላ ነገር የመደገፍ አቅም የሌላችሁ ሰባራ ሸንበቆዎች የልማት ጠላቶቹ ናችሁ። "…ድንገት እንደ ሱናሜ አደጋ ቤታችሁ የፈረሰባችሁ ወገኖቼ፡ እስቲ ተናገሩት እንዴት ሆናችሁ? እንዴት አለፋችሁት? "…እስቲ እውነተኛ ታሪካችሁን፣ ስሜታችሁን፣ ትኩስ ትዝታችሁን አጋሩን ታሪክ ይጻፍ። ለሚመለከተው አካልም ሰውን ሳያፈርስ፣ ቤት አላልኩም ሰውን ሳያፈርስ ሰዉም ተቀብሎት ሊሠራ እንደሚችል ትክክለኛ ጥቆማ እና ድጋፍ ይሁነው። +++++++++++++++++++++++++++ የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! ያስተዋውቁ! https://t.me/tunbi_media 🎥💻📺🎙 YouTube በዩቲዩብ ዝግጅቶቻችንን 👁👁👂🏽👂🏽ይታደሙ! www.youtube.com/@TunbiMedia_ በራምብል rumble.com/c/c-3688912 በቲክቶክ tiktok.com/@ethiotunbi
Show all...
ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)

MIIDIYAA TUNBII እንኳን ደህና መጣችሁ! ይህ የኢትዮ ቱንቢ ሚድያ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው። የቱንቢ ዋና አጀንዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የሁላችንም ሀገር፣ ባለ ብዙ ፈተና እና ባለ ብዙ ተስፋ ስለ ሆነችው የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ ነው። የመረጃ፣ ማስረጃ፣ የቀጥተኛ ምልከታና መፍትሔ ተኮር ጋዜጠኝነት ቤት።

👍 21
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር አርቲስት አዜብ ወርቁ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አርቲስቷ በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደምትገኝ የፖሊስ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመጣለን። አርቲስቷ ሰሞኑን "ልማት የሰውን ልጅ ሲያፈርስ በዓይኔ አየሁት!" የሚል ጽሁፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች ካጋራች በኋላ ጽሁፉ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበርና በኋላም ከማህበራዊ ገጿ ጽሁፉን ማንሳቷን ማስታወቋ አይዘነጋም። ምንጭ ዘሀበሻ
Show all...
🔥 9
Photo unavailableShow in Telegram
ለታጋቾች ማስለቀቂያ ብር ለመክፈል የሄዱ ግለሰቦች እራሳቸው በታጣቂዎች መታገታቸው ተሰማ‼️ ከሳምንት በፊት በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ 38 ሰዎች በጉዞ ላይ እያሉ በሸኔ ታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል፡፡ ታጣቂዎቹ ታጋቾችን ለመልቀቅ ከ250ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድረስ የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎም አንዳንድ የታጋች ቤተሰቦች ገንዘቡን ለመክፈል ወደ ተባሉበት ቦታ ማቅናታቸውን የሚገልጹት የመረጃ ምንጮች ገንዘብ አቀባዮቹ በቦታው ሲደርሱ ግን እራሳቸው በታጣቂዎቹ መታገታቸውን ነው የገለጹት ፡፡ ‹‹ካሉበት ቦታ ሆነው ስልክ ደውለው እኛም ታግተናል›› አሉን የሚሉት አንድ ምንጭ የታገቱትን አስፈትተው ይመጣሉ ብለን ተስፋ ስናደርግ እነሱም መያዛቸው ሌላ ጭንቀት ፈጥሮብናል ይላሉ፡፡ ታጋቾችን ለማስለቅ የሚያስችል ገንዘብ አሁን ላይ እንደሌላቸው የሚገልጹት እነዚህ የታጋች ቤተሰቦች የቀደሙትንም ለማስፈታት በገበያ ቦታ፣ በእድርና በመሰል ማህበራዊ አደረጃጀቶች በኩል ጥረት ተደርጎ ገንዘቡ እንደተሰበሰበ ገልጸዋል፡፡ መንቀሳቀስና መስራት ውድ እየሆነ መጥቷል፤ መንግስትም የህግ የበላይነት የሚባለውን መሰረታዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል በማለትም አካባቢው ላይ የሚታይ ስጋት አሁንም እንዳለ ነው ያስታወቁት፡፡ በሌላ በኩል ታግተው ከነበሩ 38 ሰዎች ውስጥ 5 ያህል ታጋቾች ማምለጣቸውንም እነዚህ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ምንጮች አሁን ላይ ያመለጡት ታጋቾች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ግን ተጨማሪ መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ የሸኔ ታጣቂ ቡድኖቹ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ከጎቤሳ ከተማ ወደ ተለያዩ ከተሞች በመጓዝ ላይ የነበሩ አጠቃላይ 8 የህዝብ ማመላለሻዎችን ጋለማ በሚባል ጫካ ውስጥ በማስቆም 38 ሰዎችን በመምረጥ ማገታቸው የሚታወስ ነው። አዲስ ማለዳ #አዩዘሀበሻ 🥳🥳🥳🥳🥳🥳🎉🎉 ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን join በማድረግ በቀላሉ መረጃ ይከታተሉ👇👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
Show all...
👍 9 1
"በየቀኑ ለቤተ ክርስቲያን ችግርና መከራ ለመፍትሔው የራሳችንን ድርሻ ካልተወጣን ስትፈርስ በተባባሪነት መቆማችንን ማወቅ ይገባል"
Show all...
👍 23 3
https://youtube.com/live/7Crfz2PB42k?feature=share +++++++++++++++++++++++++++ የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! ያስተዋውቁ! https://t.me/tunbi_media 🎥💻📺🎙 YouTube በዩቲዩብ ዝግጅቶቻችንን 👁👁👂🏽👂🏽ይታደሙ! www.youtube.com/@TunbiMedia_ በራምብል rumble.com/c/c-3688912 በቲክቶክ tiktok.com/@ethiotunbi
Show all...
ሳንጋብዛቸው እና ሳናውቀው የሚሰርጹብን ዋና ዋናዎቹ የዓለማችን ማዕቀፈ ዕሳቤዎች! #ከመምህር_ፋንታሁን_ዋቄ ጋር

#ፋንታሁን_ዋቄ #ዮሴፍ_ከተማ #Fantahun_Wakie #Yosef_Ketema #ማዕቀፈ_እሳቤ #World_View #orthodox_etrnal_life #Orthodox_world_view #ወቅታዊ_ጉዳይ @tunbimedia_ ዛሬ በፍኖት አእምሮ!

👍 14 1
በጎንደር 2 የአቋቋም ተማሪዎች ሲሞቱ 5 የአቋቋምና የቅኔ ተማሪዎች ቆስለዋል ! መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት በትናንትናው ዕለት በነበረ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ተኩስ ሁለት ንጹሐን የአቋቋም ደቀ መዛሙርት መሞታቸውን እንዲሁም ሦስት የአቋቋምና ሁለት የቅኔ ደቀ መዛሙርት በጽኑዕ መቍሰላቸውን አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ በጎንደር ከተማ ውስጥ ጉባኤ ዘርግተው የሚያስተምሩ መምህር ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ገልጸዋል። የተገደሉት ተማሪዎችም አንዱ ቤዛዊት ማርያም ፣ አንዱ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን የአቋቋም ትምህርት በመማር ላይ የሚገኙ ሲሆን በጽኑዕ የቆሰሉት ተማሪዎች ሁለቱ አማኑኤል ቤተክርስቲያን የአቋቋም ትምህርት ሁለቱ በደብረ መዊዕ ርዕሰ አድባራት አበራ ጊዮርጊስ የቅኔ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ መሆናቸውን መምህሩ አክለው ገልጸዋል። ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በደቀ መዛሙርቱ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለመምህራኖቻቸው ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የአብነት ተማሪዎች መጽናናትን ይመኛል። መረጃው የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ነው።
Show all...
👍 9
https://youtu.be/qIE-L24LY5w?si=zZIcBNHjHYf_gQHf +++++++++++++++++++++++++++ የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! ያስተዋውቁ! https://t.me/tunbi_media 🎥💻📺🎙 YouTube በዩቲዩብ ዝግጅቶቻችንን 👁👁👂🏽👂🏽ይታደሙ! www.youtube.com/@TunbiMedia_ በራምብል rumble.com/c/c-3688912 በቲክቶክ tiktok.com/@ethiotunbi
Show all...
#የአማራ_ሕዝብ_ትግል_አደገኛው_ወጥመድ_በሁለቱ_ምሁራን_ዕይታ!

Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UC23wkdfU9V0lCxWLYCPocFQ/join

#ዶክተር_አሰፋ_ነጋሽ #ፋንታሁን_ዋቄ #Dr_Asefa_Negash #fantahun_wakie Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UC23wkdfU9V0lCxWLYCPocFQ/join

#ethiopia #ቤተክርስቲያን #ሲኖዶስ #eotc_one_holy_synod #amhara #fano #አማራ #አማራ_ፋኖ #ሻይ_ቡና #shay_buna #amhara #oromiya #ebc #tigray #somali #afar #fano #addisababaethiopia #amharic #abiyahmedali #ukraine #russia #amharicnews #shay #shorts #amharicmusic #yosef #getachewreda #sergegnawegoch #ሠርገኛ #ወጎች #ሰሎሞን #ሹምዬ #ethiopiannews #gurage #wolega #southafrica #europeanunion #europeanparliament #ofc #gebeyanu #usa #endf #አብይ #አህመድ #አሊ #solomon #shumiye #debretsion #addisababa #shay #buna #wolega #shorts #ola #shene #eritrea #War #invasionofukraine #nama #williamruto #joebiden #antonyblinken #jawarmohammed #mereragudina #demekemekonnen #ብልጽግና #ፓርቲ #prosperity #party #oromiya region #amhara region #wolkait #kenya #abelbirhanu #ebc #ebs #fetadaily #fanatv #artstv #ethioforumኢትዮፎረም #ኢትዮ_ቱንቢ #Ethio_Tunbi_Media

👍 6 2
“የፋኖ ኃይሎች ተቀብለው ሲያነጋግሩን የፌዴራል መንግሥት ግን እስካሁን ሊያናግረን አልፈለገም” የሰላም ካውንስሉ ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ በአማራ ክልል ያለውን ጦርነት በድርድር ለመፍታት በሚል ከወራት በፊት የተቋቋመው የሰላም ካውንስል ለሪፖርተር ጋዜጣ ቆይታ መረጃ ሰጥቷል። በዚህም እስካሁን ያደረገውን ጥረት የዘረዘረ ሲሆን ካውንስሉ የፋኖ ኃይሎችን አግንቼ ማነጋገር ችያለሁ ብሏል። በፋኖ በኩል ድርድርን በመርህ ደረጃ ይቀበሉታል ብሏል። ካውንስሉ የፋኖ ኃይሎች እውነተኛ ድርድር የሚደረግ ከሆነ ለሰላም ቁርጥኛ መሆናቸውን የገለጸው ካውንሱ የፋኖ ኃይሎች መንግሥት እውነተኛ ድርድር ማድረግ ሳይሆን የሚፈልገው ጊዜ መግዛትና ጦርነቱን መቀጠል ነው ብለው እንደሚያምኑም ተገንዝቢአለሁ ብሏል። ካውንስሉ ድርድር የሁለቱም ወገኖች ፍላጎት እና ዝግጁነት ሲኖር ብቻ እውን የሚሆን እንደመሆኑ በተመሳሳይ የፌዴራል መንግሥቱንም ለማነጋገር ጥረት ማድረጉን አስታውቋል። ይሁንና በፌዴራል መንግሥት በኩል ስለ ድርድር እና ሰላምን ስለ ማውረድ በሚዲያ ተደጋግሞ ቢነገርም እስካሁን ለካውንስሉ ጥያቄ መልስ እንዳልተሰጠ ገልጿል። ካውንስሉ የፌዴራል መንግሥቱ እስካሁን ሊያነጋግረው እንዳልፈለገ እና አሁንም በር ማንኳኳቱን እንደቀጠለ አረጋግጧል። አንድ ጊዜ ብቻ የሰላም ሚኒስቴር አነጋግሮናል ያለው የካውንስሉ መረጃ፣ ሚኒስቴሩ የኛን ጥሪ እንደሚደግፍ ነግሮናል ብሏል። ይሁንና የፌዴራል መንግሥቱ ቁንጮ ካውንስሉን ለማነጋገር እስካሁን አለመፍቀዳቸው እሰካሁን ለሥራው አለመሳካት አንዱ ችግር መሆኑን ተናግሯ። ለሰላም የሚደረገው ጥረት እንዲሳካ ከፋኖ ኃይሎች በተጨማሪ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደርን ጨምሮ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰቡን ማነጋገር እንደቻለ እና መንግሥትን ማነጋገር እና አቋሙን በተጨባጭ ማወቅ ግን እስካሁን አለመቻሉን ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጠው ቃል ያስረዳል። ካውንስሉ በተለይ በአማራ ክልል እየደረሰ ካለው ጥፋት አንፃር ተገቢውን ትኩረት እንዳልሰጡት ለዲፕሎማሲ ማኅበረሰቡ ነግሬቸዋለሁም ብሏል። +++++++++++++++++++++++++++ የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! ያስተዋውቁ! https://t.me/tunbi_media 🎥💻📺🎙 YouTube በዩቲዩብ ዝግጅቶቻችንን 👁👁👂🏽👂🏽ይታደሙ! www.youtube.com/@TunbiMedia_ በራምብል rumble.com/c/c-3688912 በቲክቶክ tiktok.com/@ethiotunbi
Show all...
ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)

MIIDIYAA TUNBII እንኳን ደህና መጣችሁ! ይህ የኢትዮ ቱንቢ ሚድያ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው። የቱንቢ ዋና አጀንዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የሁላችንም ሀገር፣ ባለ ብዙ ፈተና እና ባለ ብዙ ተስፋ ስለ ሆነችው የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ ነው። የመረጃ፣ ማስረጃ፣ የቀጥተኛ ምልከታና መፍትሔ ተኮር ጋዜጠኝነት ቤት።

👍 5
https://www.youtube.com/live/CFiFMF9wxL8?si=dqzDZNPbVYb7evk0 https://youtu.be/tozcJiJ8M04?si=9UM_YxjonCHqe8aU +++++++++++++++++++++++++++ የቱንቢን ትክክለኛ የቴሌግራም ገጽ ይቀላቀሉ! ያስተዋውቁ! https://t.me/tunbi_media https://t.me/tunbi_media 🎥💻📺🎙 YouTube በዩቲዩብ ዝግጅቶቻችንን 👁👁👂🏽👂🏽ይታደሙ! www.youtube.com/@TunbiMedia_
Show all...
ተስፋና ሥጋት በአዲሱ ዓመት! የአቡነ አብርሃም ተቃርኖ እና ተማጽኖ! #ቀሲስ_አስተርአየ #ቀሲስ_ሳሙኤል መ/ር #ፋንታሁን

#መልአከ_በርሃን_አስተርአየ_ጽጌ #መጋቤ_ጥበብ_ሳሙኤል_ግዛው #መምህር_ፋንታሁን_ዋቄ #ዮሴፍ_ከተማ Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UC23wkdfU9V0lCxWLYCPocFQ/join

#fantahun_wakie #ፋንታሁን_ዋቄ Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UC23wkdfU9V0lCxWLYCPocFQ/join

#ethiopia #ቤተክርስቲያን #ሲኖዶስ #eotc_one_holy_synod #ሻይ_ቡና #shay_buna #amhara #oromiya #ebc #tigray #somali #afar #fano #addisababaethiopia #amharic #abiyahmedali #ukraine #russia #amharicnews #shay #shorts #amharicmusic #yosef #getachewreda #sergegnawegoch #ሠርገኛ #ወጎች #ሰሎሞን #ሹምዬ #ethiopiannews #gurage #wolega #southafrica #europeanunion #europeanparliament #ofc #gebeyanu #usa #endf #አብይ #አህመድ #አሊ #solomon #shumiye #debretsion #addisababa #shay #buna #wolega #shorts #ola #shene #eritrea #War #invasionofukraine #nama #williamruto #joebiden #antonyblinken #jawarmohammed #mereragudina #demekemekonnen #ብልጽግና #ፓርቲ #prosperity #party #oromiya region #amhara region #wolkait #kenya #abelbirhanu #ebc #ebs #fetadaily #fanatv #artstv #ethioforumኢትዮፎረም #ኢትዮ_ቱንቢ #Ethio_Tunbi_Media

👍 14 4
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.